# የሚቃጠል መሥዋዕቱ የሚቀርበው ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ ከሆነ፣ እንስሳው ምን መሆን እንዳለበት እንዲነግራቸው ነበር ያህዌ ለሙሴ የነገረው? እንስሳው እንከን የሌለበት ተባዕት በግ ወይም ፍየል እንዲሆን ያህዌ ለሕዝቡ ተናገረ፡፡ # ተባዕት በጉ ወይም ፍየሉ መታረድ የነበረበት ከመሠዊያው በየት በኩል ነው? በጉ ወይም ፍየሉ መታረድ የነበረበት ከመሠዊያው በስተ ሰሜን በኩል ነው፡፡ # የበጉን ወይም የፍየሉን ደም የአሮን ልጆች መርጨት የነበረባቸው የት ላይ ነበር? የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን መርጨት ነበረባቸው፡፡