# ከዚያ አብራም እንዲያቀርብ በተነገረው እንስሳት ላይ ምን አደረገ? አብራም እንስሳቱን አርዶ ለሁለት በመክፈል አንደኛውን በሌላኛው ፊት በትይዩ አስቀመጣቸው # ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ አብራም ምን ሆነ? ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ አብራም አንቀላፋ፣ ድንጋጤና ታላቅ ጨለማም ወደቀበት # እግዚአብሔር አምላክ የተናገረው የአብራም ዘሮች ለምን ያህል ጊዜ ባሪያዎች እንደሚሆኑና እንደሚጨቆኑ ነበር? ዘሮቹ ለአራት መቶ አመታት ባሪያዎች እንደሚሆኑና እንደሚጨቆኑ እግዚአብሔር አምላክ ለአብራም ነገረው