# ዲዮጥራጢስ የሚወደው ምንድነው? ዲዮጥራጢስ የሚወደው በማኅበረ ምዕመኑ መካከል ዋነኛ መሆንን ነው # ዲዮጥራጢስ ለዮሐንስ ያለው አመለካከት ምን ዓይነት ነው? ዲዮጥራጢስ ዮሐንስን አይቀበለውም # ዮሐንስ ወደ ጋይዮስና ወደ ማኅበረ ምዕመኑ ከመጣ የሚያደርገው ምንድነው? ዮሐንስ ከመጣ የዲዮጥራጢስን ክፉ ሥራዎች ያሳስባል # ዲዮጥራጢስ፣ ስለ ጌታ ስም የወጡትን ወንድሞች ምን ነበር የሚያደርገው ? ዲዮጥራጢስ ወንድሞችን አይቀበልም # ስለ ጌታ ስም የወጡትን ወንድሞች የሚቀበሉትን ዲዮጥራጢስ ምን ያደርጋቸው ነበር? ወንድሞችን እንዳይቀበሉ ይከለክላቸው ነበር፣ ከማኅበረ ምዕመኑ ያባርራቸውም ነበር