am_tn/psa/045/016.md

1.2 KiB

በአባቶቻችሁ ቦታ ልጆቻችሁ ይሆናሉ

ይህ ማለት እርሱ ነገሥታት የነበሩ አባቶቹን እንደተካቸው የንጉሡ ወንዶች ልጆች ንጉሥ በመሆን ይተኩታል ማለት ነው።

በምድር ሁሉ ላይ ገዦችን ታደርጋለህ

“በምድር ሁሉ ላይ” የሚለው በብዙ ሀገሮች እንደሚያስተዳድሩ አጽንዖት ለመስጠት እንጂ ግነት ነው። አ.ት፡ “በብዙ ሀገሮች ላይ ገዢዎች እንዲሆኑ ታደርጋቸዋለህ” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)

ትውልድ ሁሉ ስምህን እንዲያስታውስ አደርጋለሁ

እዚህ ጋ በውስጠ ታዋቂነት “እኔ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጸሐፊውን ነው። “ስም” የሚለው ቃል የንጉሡን ጸባይና ምስክርነት ያመለክታል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በየትውልዱ የሚኖሩ ሰዎች ስለ ታላቅነትህ እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)