am_tn/psa/045/014.md

1.6 KiB

የተጠለፈበትን ልብስ ለብሳ ወደ ንጉሡ ትወሰዳለች

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የተጠለፈበትን ልብስ እንደ ለበሰች ሰዎች ወደ ንጉሡ ይወስዷታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ጥልፍ

የተለያየ ቀለም ያሏቸውን ክሮች ወደ ጨርቅነት ለመስፋት የተዘጋጀ ንድፍ

አጅበው የሚከተሏትን ደናግል ወደ አንተ ያመጣሉ

እዚህ ጋ፣ “አንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ንጉሡን ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች እርሷን አጅበው የሚከተሏትን ደናግል ያመጡልሃል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ደስታና ሐሴት ይመሯቸዋል

ይህ ሐረግ “ደስታና ሐሴት”ን ሌሎች እንዲደሰቱ የሚመራቸው ዓይነት ሰው ተደርጎ ተገልጿል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ደስታና ሐሴት እነርሱን ይመሯቸዋል” ወይም “በደስታና በሐሴት ወደፊት ይሄዳሉ” (ሰውኛ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ደስታና ሐሴት

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ቃላት ትርጉማቸው አንድ ሆኖ ሳለ የደስታው ጥልቅነት ላይ አጽንዖት የሚሰጡ ናቸው። አ.ት፡ “በታላቅ ደስታ” (See: Doublet)