am_tn/psa/045/008.md

1.6 KiB

ከርቤ፣ አደስ፣ እና ጥንጁት

እነዚህ ሰዎች ሽቶ ለመሥራት የሚጠቀሙባቸው መዓዛ ያላቸው እጽዋት ናቸው። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)

በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶች

የዝሆን ጥርስ ከእንስሳ የሚገኝ ነጭና ጠንካራ ነገር ነው። ይህ ሐረግ የሚገልጸው ሰዎች ግድግዳዎቹንና ቁሳቁሶቹን በዝሆን ጥርስ ስላስዋቡት ቤተ መንግሥት ነው።

ባለ አውታር የሙዚቃ መሣሪያዎች ደስ አሰኝተውሃል

“ባለ አውታር የሙዚቃ መሣሪያዎች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ባለ አውታር የሙዚቃ መሣሪያ በመጠቀም የሚጫወቱትን ሙዚቃ ነው። አ.ት፡ “የባለ አውታሩ ሙዚቃ ደስ አሰኝቶሃል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የተከበሩ ሴቶች

እነዚህ ሴቶች የንጉሡን ፈቃድ የሚቀበሉ ሚስቶቹ ናቸው።

ንግሥቲቱ

ይህ ንግሥት ልትሆን ያለችውን ሴት ማመላከቻ ነው። አ.ት፡ “ንግሥቲቱ ሙሽራህ” ወይም “ንግሥት የምትሆነው ሙሽራህ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)

ኦፊር

ይህ በጥሩ ወርቁ የተመሰከረለት የቦታ ስም ነው። ስፍራው አይታወቅም። (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)