1.2 KiB
1.2 KiB
ፍሬየ
ጥበብ የምታፈራውና የምታመጣው ነገር
ቡቃያየ
ጥበብ ካመጣችው ነገር የሚገኘው ትርፍ ወይም ጥቅም
እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ
በትክክለኛው መንገድ መኖር በትክክለኛው መንገድ እንደመራመድ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በትክክል እኖራለሁ” ወይም “ትክክል የሆነውን ነገር አደርጋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ወደ ፍትህ በሚወስዱ ጎዳናዎች
ይህ “የጽድቅ መንገድ” የሚለውን ትርጉሙ ምን እንደሆነ የበለጠ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ፍጹም ፍትህ የሆነውን አደርጋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
መዛግብት
በታም ውድ የሆኑ ነገሮች የሚቀመጡበት፡፡ ጥበብ የተከታዮቿን መዛግብት በውድ ነገሮች የምትሞላ ሴት ተደርጋ ተገልጻለች፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)