am_tn/pro/08/01.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

በምዕራፍ 8 ጥበብ ሰዎች እንዴት ጥበበኛ መሆን እንዳለባቸው እንደምታስተምር ሴት ተደርጋ ተነግራለች፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡-

በምዕራፍ 8 ውስጥ ብዙ ጥቅሶች ትይዩነት አላቸው፡፡ (ትይዩነት የሚለውን ይመልከቱ)

በውኑ ጥበብ አትጮኽምን?

ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው አንባቢዎች ቀድመው የሚያውቁትን ነገር ለማስታወስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ ትጣራለች” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በውኑ ጥበብ አትጮኽምን?

እዚህ ላይ ጥበብ እንደ ሴት ቀርባለች፡፡ አንድ ቋንቋ እንዲህ ዓይነት ተለዋጭ ዘይቤ መጠቀም የማይፈቅድ ከሆነ የሚከተሉት ሌሎች አማራጮች ናቸው፡- 1) “ጥበብ እንደ ሴት የምትጮኽ አይደለችምን?” 2) “ጥበብ የምትባል ሴት እየጮኸች አይደለምን?” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አታደርግምን? Does not Understanding raise her voice?

እዚህ ላይ “ማስተዋል” ትርጉሙ ከ“ጥበብ” ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ድምፅዋን ከፍ አደረገች

“ተናገረች”

ወደ ከተማይቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ

በጥንት ጊዜ ከተሞች ብዙ ጊዜ በር የተገጠመላቸው የውጭ የግንብ አጥር ነበራቸው፡፡

ትጣራለች

ይህ እንደ ሴት የተመሰለችውን ጥበብን ያመለክታል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)