36 lines
2.7 KiB
Markdown
36 lines
2.7 KiB
Markdown
# አያያዥ ሃሳብ፡
|
|
|
|
ኤርምያስ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን የያህዌ መልዕክት ማድረሱን ይቀጥላል፡፡
|
|
|
|
# የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል
|
|
|
|
ብዙውን ጊዜ አርምያስ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ ሀሳብን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡
|
|
|
|
# እነርሱ አሞኝተዋችኋል!
|
|
|
|
"ነቢያቱ እውነት ያልሆነውን ነገር እንድታምኑ አድርገዋል!"
|
|
|
|
# ከአይምሯቸው የፈለቀውን ቅዠት
|
|
|
|
እዚህ ስፍራ "አይምሮ" የሚለው የሚያመለክተው የሀሰተኛ ነቢያትን ሀሳብ ነው፡፡ "እነርሱ የሚገምቱት ቅዠት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
|
|
|
|
# ከያህዌ አፍ ያልሆነ
|
|
|
|
እዚህ ስፍራ "አፍ" የሚያመለክተው ያህዌ የተናገረውን ነው፡፡ "ያህዌ ያልተናገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
|
|
|
|
# እነርሱ ሳያቋርጡ ይናገራሉ
|
|
|
|
"ሳያቋርጡ" የሚለው ቃል ይህ ሁሌም የሚናገሩት ነገር እንደሆነ አጋኖ በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)
|
|
|
|
# በእናንተ ላይ ጥፋት አይመጣም
|
|
|
|
"በእናንተ ላይ ምንም ክፉ ነገር አይደርስም"
|
|
|
|
# ነገር ግን በያህዌ ምክር ላይ ማን ተገኝቷል?የእርሱን ቃል ማን አይቷል ማንስ ሰምቷል? ለእርሱ ቃል ማን ልቡን ሰጥቶ ሰምቷል?
|
|
|
|
እነዚህ ጥያቄዎች የዋሉት ካህናቱ እና ሀሰተኛ ነቢያቱ ያህዌን ባለመታዘዛቸው ለመገሰጽ ነው፡፡ "ማንም ያህዌን አላማከረውም፡፡ ማንም ያህዌ የተናገረውን አልተረዳም፡፡ ማንም የያህዌን ትዕዘዞች አልታዘዘም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)
|
|
|
|
# ለእርሱ ቃላት ትኩረት ስጡ፣ አድምጡም
|
|
|
|
እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ነገር ይገልጻሉ፡፡ በአንድ ሀረግ ሊጠቃላሉ ይችላሉ፡፡ "ሙሉ ለሙሉ ለቃሉን ታዘዙ"
|