am_tn/isa/28/05.md

28 lines
1.9 KiB
Markdown

# የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ይህንን በኢሳይያስ 1፡9 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
# ውብ ዘውድና የውበት አክሊል ይሆናል
እንደ እውነተኛ ንጉሣቸው ለብሰውት ለሚያከብሩት ሕዝብ እግዚአብሔር ውብ ዘውድ እንደሚሆን ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# ውብ ዘውድና የውበት አክሊል
የሁለቱም ትርጉም አንድ ነው፡፡ አት፡- "ውብ ዘውድ' (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)
# ሕዝብ፣ በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍትህ መንፈስ፣ … ብርታትም
እንደ "ፍትህ' እና "ብርታት' ያሉ የነገር ስሞች በቅጽልነት እንዲገለጹ ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ዳኞችን ጻድቃን እንዲሆኑ ያደርጋል እንዲሁም ብርቱዎች ያደርጋቸዋል' (የነገር ስም ተመልከት)
# የፍትህ መንፈስ
የፍትህ መንፈስ ያለው ሰው የፍትሃዊነት ባሕርይ ያለውና ጻድቅ ሰው ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
# በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥ
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር የዳኝነት ሥልጣን ያለው ሰው ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
# በበራቸው ጠላቶቻቸውን ወደ ኋላ ለሚመልሱ ብርታትን
በዚህ ስፍራ "ወደ ኋላ ለሚመልሱ' የሚለው በጦርነት ለሚያሸነፉ የሚል ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ጠላቶች ከተማቸውን ሲያጠቁ ጠላቶቻቸውን ያሸንፉ ዘንድ እግዚአብሔር ወታደሮቹን ብርቱዎች ያደርጋቸዋል' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)