am_tn/1ki/15/18.md

2.8 KiB

በአገልጋዮቹ እጅ ላይ አስቀመጣት

ነገሮችን በእጆቻቸው ላይ ማስቀመት የሚወክለው እነዚያን ነገሮች ለእነርሱ መስጠትን ነው፡፡ እነርሱ እንዲያደርጉ የሚፈልገውን በእርሷ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል፡፡ የዚህ ሀሳብ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ይህን ለአገላጋዮቹ አደራ ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

እንዲህ አለ

ይህ ማለት በአገላጋዮቹ አማካይነት ተናገረ ማለት ነው፡፡ አሳ ለአገልጋዮቹ ለቤን ሀዳድ ምን እንደሚናገሩ እና እንደሚያደርጉ ነገራቸው፡፡ የዚህ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "አሳ ለአገልጋዮቹ ለቤን ሀዳድ እንዲነግሩት ነገራቸው" ወይም "አሳ በአገልጋዮቹ በኩል ለቤን ሀዳድ እንዲህ ሲል መልዕክት ላከ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

በእኔ እና በአንተ መሃል ቃል ኪዳን ይኑር

በሁለት ሰዎች መካከል ቃል ኪዳን መኖር የሚያመለክተው ሁለቱ ሰዎች በመሃላቸው ቃል ኪዳን እንዳለ ነው፡፡ "እርስ በእርሳችን ቃል ኪዳን ይኑረን" ወይም "የሰላም ስምምነት እናድርግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ፣ እኔ

"እኔ፣ ከአንተ ጋር ለመተማመኛ ስምምነት እፈልጋለሁ"

ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ቃል ኪዳን አፍርስ

ቃል ኪዳንን ማፍረስ የሚወክለው አንድ ሰው ሊያደርግ ቃል የገባውን መሰረዝን እና አለማድረግን ነው፡፡ "ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር የገባኸውን ኪዳን አፍርስ" ወይም "ለእስራኤል ንጉሥ ለባኦስ ከእርሱ ጋር ኪዳን ባደረግከው መሰረት ታማኝ አትሁንለት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ቃል ኪዳን አፍርስ

x