# አንተን የሚያመልኩ እዚህ ስፍራ "አምልኮ" የሚለው የሚያመለክተው መጮህን እና መለከት/ቀንዶችን መንፋትን ነው፡፡ ይህ በእስራኤላውያን ክብረ በዓል የተለመደ ድርጊት ነበር፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) # ይሄዳሉ/ይራመዳሉ እዚህ ስፍራ የሰዎች ኑሮ የተገለጸው እንደሚሄዱ/እንደሚራመዱ ተደርጎ ነው፡፡ "ይኖራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) # በፊትህ ብርሃን ጸሐፊው ያህዌ ለእነርሱ ሞገስን እንደሚሰጥ የገለጸው፣ የያህዌ ፊት በእነርሱ ላይ ብርሃንን እንደሚያበራ አድርጎ ነው፡፡ "በእነርሱ ላይ ሞገስህን እንደምታደርግ ይወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) # በስምህ እዚህ ስፍራ "ስም" የሚወክለው ጠቅላላ ሰውነትን ነው፡፡ " በአንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) # በጽድቅህ አንተን ከፈ ከፍ ያደርጋሉ "ጽድቅ" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ ሁልጊዜም ትክክል የሆነውን ስለምታደርግ እነርዱ ከፈ ከፍ ያየርጉሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ "ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)