# የጢሮስ ሴት ልጅ ጸሐፊው በጢሮስ ስለሚኖሩ ሰዎች ሲናገር እንደ ጢሮስ ልጆች ይቆጥራቸዋል። አ.ት፡ “የጢሮስ ሕዝብ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # የንጉሥ ሴት ልጅ ይህ ንጉሡ የሚያገባትን ሴት ማንነት የሚያመላክት ነው። አ.ት፡ “የንጉሡ ሙሽራ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information) # ሁለንተናዋ ያሸበረቀ “በጣም ውብ”። ይህ የሴቲቱን ገጽታ ያመለክታል። # ልብሷ በወርቅ የተሠራ ነው ልብሷ በወርቅ ያጌጠ ወይም የተጠለፈ ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው በወርቃማ ክር የጠለፈውን ልብስ ትለብሳለች” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)