# ያስብህ ‹‹ያስብህ›› የተባለው እግዚአብሔር ስለሚረሳ አይደለም፡፡ ያስታውስህ ወይም ያስብልህ ለማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ያስታውስህ›› # እርሱ ይህ ቃል የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ # ሴላ ይህ ቃል እንዴት እንደሚዘምሩ ወይም የሙዚቃ መሣሪያቸውን እንደሚጫወቱ ለሕዝብ የሚናገር የሙዚቃ አገላለጽ ነው፡፡ አንዳንድ ትርጒሞች የዕብራይስጡን ቃል ይጽፋሉ፤ አንዳንድ ትርጒሞች ያንን አያደርጉም፡፡ መዝሙር 3፥2 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ # ይስጥህ ‹‹ይለግሥህ›› # የልብህን መሻት ‹‹ልብ›› የሰውን ሁለንተና ይወክላል፡፡ ‹‹መሻት›› የሚለውን ስም ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምትሻውን›› ወይም፣ ‹‹የምትፈልገውን›› # ዕቅድህን ሁሉ ያሳካልህ ‹‹ዕቅድ›› የሚለውን የነገር ስም ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያቀድኸውን ሁሉ ለማሳካት ይርዳህ››