# ፀብ አለመግባባት፤ ግጭት # በሕዝቦች ላይ ራስ አደረገኝ ‹‹ራሱ›› የሚወክለው መሪን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የብዙ ሕዝብ መሪ አደረግኸኝ›› # ባዕዳን በፊቴ ዝቅ አሉ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እግዚአብሔር ባዕዳን በፊቴ ዝቅ እንዲሉ አደረገ›› # የሌላ አገር ሰዎች እየተንቀጠቀጡ መጡ ‹‹መንቀጥቀጥ›› የሚያመለክተው መፍራታቸውን ነው፡፡ ትርጒሙ ውስጥ ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሌላ አገር ሰዎች ፍርሃታቸውን ለማሳየት እየተንቀጠቀጡ መጡ››