# አያያዥ ሀሳብ፡ ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል # አጠቃላይ መረጃ፡ እዚህ ስፍራ ያህዌ ሶስት ጥያቄዎች የጠየቀው ኢዮብ እንደ ያህዌ እንዳልሆነ ትኩረት ለመስጠት ነው፤ ምክንየቱም ኢዮብ የዱር/ያልተገራ ፈረስን ሊቆጣጠር አይችልም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ) # አንገቱን በጋማ ትሸፍናለህን? ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንገቱን በጋማ ልትሸፍን አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ) # አንገቱን በጋማ ልትሸፍን የፈረስ "ጋማ" የተገለጸው የፈረስን አንገት እንደሚሸፍን ልብስ ተደርጎ ነው፡፡ "ጋማው አንገቱን እንደ ልብስ ይሸፍናል" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) # በአንገቱ ላይ የወረደው ጋማ በፈረሱ አንገት ላይ የሚገኘው ረጅም ፀጉር # በእውኑ አንተ እንደ አንበጣ እንዲፈናጠር ልታደርገው ትችላለህን? ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንተ እንደ አንበጣ እንዲዘል ልታደርገው አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ) # ትልቅ አንበጣ በጣም በፍጥነት እና በጣም ሩቅ ሊዘል የሚችል ትልቅ የአንበጣ አይነት # ማሽካካት/ማንኮራፋት ፈረሶች በአፍኝጫቸው የሚያወጡት በጣም ጉልህ ድምጽ