# በመልካም ቀናቶቼ/በአጨዳ ቀናቶቼ ኢዮብ ጠንካራ እና ወጣት ስለነበረበት ጊዜ የተናገረው እነዚያን ጊዜያት አዝመራ እንደሚታጨድበት ጊዜ አድርጎ ነው፡፡ "ወጣትና ጠንካራ በነበርኩበት ወቅት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) # የእግዚአብሔር ወዳጅነት በጎጆዬ በነበሩበት ወቅት "ወዳጅነት" የሚለው ረቂቅ ስም "ወዳጅ" በሚለው ስም ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጎጆ" የሚለው ቃል የኢዮብን ቤት ይወክላል፡፡ "እግዚአብሔር የእኔ ወዳጅ በነበረበት እና እኔን በሚጠብቅበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ) # መንገዴ በቅባት/ወተት እና የወተት ተዋጽኦ በተሸፈነበት ጊዜ "መንገዴ በቅባት በተጥለቀለቀ ጊዜ" ኢዮብ ይህንን አጋኖ የተጠቀመው ብዙ ላሞች እንደመበሩት እና ላሞቹ ለእርሱ እና ለቤተሰቡ ከሚያስፈልገው ያለፈ ብዙ ቅባት ይሰጡት እንደነበረ ለመግለጽ ነው፡፡ "ላሞቼ እጅግ የበዛ ቅባት ይሰጡኝ በነበረ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚለውን ይመልከቱ) # ደግሞም አለቱ የዘይት ፈሳሽ ይሰጠኝ ነበር "ደግሞም አለቱ የዘይት ፈሳሽ ይሰጠኝ ነበር፡፡" ኢዮብ ይህንን አጋኖ የተጠቀመው ብዙ የወይራ ተክል እንደነበረው እና ብዙ የወይራ ዘይት ያመርት እንደነበር ለመግለጽ ነው፡፡ አለቱ አገልጋዮቹ ከወይራ ፍሬ ዘይት ይጨምቁበት የነበረበት ስፍራ ነው፡፡ "አገልጋዮቼ እጅግ ብዙ የወይራ ዘይት ይጨምቁ በነበረበት ጊዜ" ወይም "ዘይት እንደ ወንዝ ዘይት ከሚጨመቅበት አለት ይፈስ በነበረበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚለውን ይመልከቱ)