# አጠቃላይ መረጃ ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡ # ስለ ስሜ ስል ቁጣዬን አዘገያለሁ እዚህ ላይ፣ ‹‹ስም›› የያህዌን ማንነት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ማንነቴ ስል ቁጣዬን አዘገያለሁ›› # ስለ ክብሬ ስል እናንተን ከማጥፋት እታቀባለሁ ይህ የዐረፍተ ነገሩ ክፍል ከመጀመሪያው ክፍል ጋር በመሠረቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ # እነሆ፣ እንደ ብር ባይሆንም፣ አንጥሬሃለሁ፤ በመከራ እቶን አንጽቼሃለሁ እነርሱ የከበሩ ማዕድኖች የሆኑ ይመስል እቶን ደግሞ እነርሱን የሚያነጻ እሳት ይመስል ያህዌ ሕዝቡን በመከራ ውስጥ እንደሚያነጻ ይናገራል፡፡ # ስሜን ለውርደት እንዴት አሳልፌ እሰጣለሁ? ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው ስሙን ለውርደት አሳልፎ እንደማይሰጥ አጠንክሮ ለማመልከት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማንም ስሜን እንዲያዋርድ አልፈቅድም››