# አጠቃላይ መረጃ ኢሳይያስ በግጥም መልክ የያህዌን ቃል ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡ # ብርቱ ሰው ‹‹ብርቱ ሰው›› ወይም፣ ‹‹ብርቱ የሆነ ሰው›› - ይህ የሚመለከተው ታዋቂና ሌሎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ሰዎችን ሊሆን ይችላል፡፡ # ገለባ ገለባ በቀላሉ የሚቃጠል ደረቅ ሣር ነው፡፡ # ሥራውም እንደ ብልጭታ ይህ የሰውን ሥራ ወይም ክፉ ሥራን ገለባ ላይ ወድቆ ከሚነድ ነገር ጋር ያመሳስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሥራው እሳት እንደሚያስነሣ ብልጭታ ይሆናል››