# ከእናንተ ጋር ይሆናል ወደ አባቶቻችሁም ምድር መልሶ ያገባችኋል እዚህ “እናንተ” “የእናንተ” ብዙና የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ያመለክታል (“እናንተ” አጠቃቀም ይመልከቱ) # ከእናንተ ጋር ይሆናል እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደሚረዳና እንደሚባረካቸው የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው አት እግዚአብሔር ይረዳችኋል ወይም እግዚአብሔር ይባርካችኋል (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ) # ወደ አባቶቻችሁም ምድር ወደ ዘራችሁም ወይም ትውልዳችሁም ምድር # ለአንተ ከወንድሞችህ አንድ እጅ እብልጬ ዐምባ ሰጠሁህ ተገቢ ትርጉሞች 1 ከወንድሞቹ ይበልጥ ብዙ ክብርና ሥልጣን ለዮሴፍ መሰጠቱ እርሱ በአካል ከሌሎች የበላይ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ለአንተ ከሌሎች ለሚትበልጠው የተራራውን ዐምባ ሰጠሁህ” ወይም 2)ያዕቆብ ለዮሴፍ ወንድሞች ከሚሰጠው መሬት በላይ ለዮሴፍ እንደሚሰጠው ይገልጻል:: አት “ለአንተ ለወንድሞችህ ከሰጠሁት በላይ ridge ሰጠሁህ የተራራውን ዐምባ ሰጠሁህ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ) # ለአንተ እዚህ አንተ በነጠላ የተገለጸና ዮሴፍን ያመለክታል (አንተ አጠቃቀም ይመልከቱ) # በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራዊያን እጅ የወሰድኳትን ዐምባ እዚህ ሰይፍ እና ቀስት በጦርነት መዋጋትን ያመለክታሉ፡፡ አት “የተዋጋሁትና ከአሞራዊያን እጅ የወሰድሁት ምድር” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)