# ደሞዝ … ትርፍ እነዚህ ቃላቶች ብዙውን ጊዜ የሚያመለክቱት ሰራተኛ የሚከፈለውን ገንዘብ ነው፡፡ እዚህ ላይ ትክክለኛውን ነገር የመስራት ወይም ደግሞ ትክክለኛ ያልሆነውን ነገር የመስራት ውጤት ይወክላሉ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) # ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ “ጥበብ ያለበትን ምክር የሚታዘዝ ሰው ረጅምና ደስተኛ ሕይወት ይኖረዋል” # ተግሳጽን የማይቀበል ሰው ግን ይስታል ይህ በገቢር ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥበብ የተሞላበት ምክር የማይቀበል ሰው ግን ጥሩ ሕይወት አይኖረውም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)