# ንፁሕ ያልሆነ እዚህ ሥፍራ ላይ እግዚአብሔር አንድን ሰው በመንፈሣዊ ሕይወቱ ተቀባይነት እንደሌለውና ወይም የረከሰ እንደሆነ የሚቆጥረውን ሰው ልክ ሰውነቱ ንፁህ እንዳልሆነ ተደርጎ ይገለፃል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) # ከሞተ ሰው ሬሣ የተነሣ ይሄ ማለት የሞተ ሰው ሬሣ ነክተዋል ማለት ነው፡፡የዚህን ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ የበለጠ ማብራራት ትችላላችሁ፡፡“የሞተ ሰው ሬሣ ከመንካታችን የተነሣ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) # ፋሲካን ጠብቁ “ጠብቁ”የሚለው ቃል በአግባቡ አስቡት ማለት ነው፡፡ “ፋሲካን በአግባቡ አስቡት”ወይም “ፋሲካን አክብሩት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)