# ይሁም ሁሉ የሃገሩ ስም በሃገሩ ለሚኖሩ ሕዝቦች ወካይ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ይህ ማስፋፊያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በይሁዳ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች በሙሉ” (ምትክ ስም እና ግነትና ማስፋፊያ የሚለውን ይመልከቱ) # ሰሌምያ … ሳዶቅ … ፈዳያ … ሐናን … ዘኩር … መታንያ እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞችን እንዴት መተርጎም ይቻላል የሚለውን ይመልከቱ) # የታመኑ ሆነው ተገኙ ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርጽ መጻፍ ይችላል፡፡ “የታመነ” የሚለው ረቂቅ ቃል በግስ መልክ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እምነቴን ልጥልባቸው የምችል ሰዎች አውቅ ነበር” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) # ይህን አስመልክቶ አምላኬ አስበኝ “አምላኬ ይህን በተመለከተ አስበኝ”