# ወደ አባቴ ቤት እርሱን ላከው "አልዓዛር ወደ አባቴ ቤት እንዲሄድ ንገረው" ወይም "እባክህ፣ ወደ አባቴ ቤት እርሱን ላከው" # የአባቴ ቤት ይህ በቤት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ "ቤተሰቤ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) # እርሱ ያስጠነቅቃቸው ዘንድ "አልዓዛር እንዲያስጠነቅቃቸው" # ይህ የከፍተኛ ጭንቅ ስፍራ "በስቃይ የምንጨነቅበት ይህ ስፍራ" ወይም "በአስጨናቂ ስቃይ ውስጥ የምንገኝበት ይህ ስፍራ"