# ሊዋጅ አይቻልም ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ሊዋጀው አይችልም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ) # እርሻውን ባይዋጅ እርሻውን የሚዋጅበት ጊዜ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት ከኢዩቤልዩ ዓመት በፊት እርሻውን ባይዋጅ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ) # በኢዩቤልዩ ዓመት “በመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የሚመለስበትና ባሪያዎች ነጻ የሚወጡበት ዓመት” ይህ አይሁዳዊያን መሬትን ለባለመሬቱ የሚመልቱበትና ለባሪያዎች ነጻነትን የሚያውጁበት ዓመት ነው:: በዘሌዋዊያን 25:13 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: # ለእግዚአብሔር እንደተሰጠ ይቆጠር ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “አንድ ሰው ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ይሰጠዋል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)