# አያያዥ ሃሳብ፡ ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል # ድሆች ዘይት ያዘጋጃሉ ከወይራ ዘይት ለእነርሱ ዘይት ይጨምቃሉ # በክፉ ሰዎች አጥር ውስጥ እዚህ ስፍራ "አጥር" የሚለው የሚወክለው በአጠቃላይ ቤቱን ነው፡፡ "በእነዚያ ክፉ ሰዎች ቤት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ) # በክፉዎች ወይን መጭመቂያ ይረግጣሉ ወይን ለማዘጋጀት ይህንን እንደሚያደርጉ መግለጽ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ "ወይን ለማዘጋጀት የወይን ፍሬ ይረግጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ) # እነርሱ ራሳቸው በጥም ይሰቃያሉ "ከጥማት የተነሳ ይሰቃያሉ" ወይም "ተጠምተዋል"