# የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ናቡከደነፆር የሚለው ሰራዊቱን ያመለክታል፡፡ “የባቢሎን የንጉስ ናቡከደነፆር ሰራዊት” # የግብፅን ምድር “ምድር” የሚለው ህዝብን ያመለክታል፡፡ “የግብፅ ህዝቦች” ወይም “ግብፃውያን” # ሚግዶልም ኤርምያስ 44፡1 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት # በሚምፎስና በጣፍናስ እነዚህን ስሞች ኤርምያስ 2፡16 እንዴት እንደተረጎመው ተመልከት፡፡ # ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና “ሰይፍ” የሚለው ቃል የጦር መሳሪያ የያዙ ሰራዊቶችን ያመለክታል፡፡ የጠላት ሰራዊ ህዝቡን መግደሉን እንደ ሰይፍ ህዝቡን እንደበላ መስሎ ይናገራል፡፡ “ጠላቶቻችሁ በዙሪያችሁ ያሉህዝቦችን ሁሉ ይገድላሉ”