# አጠቃላይ መረጃ የያህዌ ባርያ በእያንዳንዱ መስመር ተጓዳኝ ሐሳብን በመጠቀም ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡ # ትጠራላችሁ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ይጠሯችኃል›› # ዕጥፍ ይኖራችኃል ምናልባት፣ ዕጥፍ የርስት ድርሻ ሊሆን ይችላል፡፡ # በድርሻቸው ደስ ይላቸዋል… እነርሱ… ምድራቸው የእነርሱ ይሆናል ይህም የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ይህን በሁለተኛ ሰው ደረጃ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በድርሻችሁ ደስ ይላችኃል… እናንተ… ምድራችሁ… የእናንተ ይሆናል››