# አጠቃላይ መረጃ ኢሳይያስ ለይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ # ይሰጣል "እግዚአብሔር ይሰጣል' # ከምድር የተትረፈረፈ እንጀራ በዚህ ስፍራ "እንጀራ' የሚለው ምግብን በአጠቃለይ ይወክላል፡፡ አት፡- "የምትመገበውን የተትረፈረፈ ፍሬ ምድር እንደትሰጥ ያደርጋታል' (ተለዋጭ ስም ተመልከት) # በዚያም ቀን "በዚያን ጊዜ' # በመንሽና በመንሽ ሹካ የተለየውን መንሽ እና መንሽ ሹካ ነፋሱ ሊበላ የሚችለውን ብቻ በመተው ገለባውን እንዲወስደው እህልን ወደ አየር ለመወርወር የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "በመንሽና በመንሽ ሹካ ትለያለህ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)