# ወደ ተርሴስ ተሻገሩ "ጉዞአችሁን ወደ ተርሴስ አድርጉ፡፡' ተርሴስ፣ የጢሮስ ሰዎች ለንግድ ጉዞ የሚያደርጉባት ሩቅ ቦታ ነች፡፡ ከጢሮስ ላመለጡ ብቸኛ የድኅንነት ቦታ ነች፡፡ # በቀድሞ ዘመን ተመሥርታ የነበረችው፣ … ደስተኛይቱ ከተማ፣ ይህ ደረሰባትን እግዚአብሔር በጢሮስ ላይ ለመሳለቅ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በአሳብ ገላጭ አረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ለመደላደል … በጥንታዊቷ የጢሮስ ከተማ በሙሉ ደስታ የምትኖሩ በእርግጥ ይህ ይደርስባችኋል' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት) # ደስተኛይቱ ከተማ በዚህ ስፍራ "ከተማ' የሚለው ሕዝቡን ይወክላል፡፡ አት፡- "በጢሮስ ከተማ የሚኖር ደስተኛ ሕዝብ' (ምትክ ስም ተመልከት) # ለመደላደል እግሮችዋ ወደ ሩቅ ወደ እንግዳ ሥፍራዎች የወሰዷት በዚህ ስፍራ "እግር' መላውን የሰው ማንነት ይወክላል፡፡ አት፡- "ለመኖርና ገንዘብ ለማትረፍ ወደ ሩቅ ስፍራዎች የሄዱ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት) # ወደ ሩቅ … የወሰዷት በዚህ ስፍራ "የወሰዷት' የሚለው የጢሮስን ሕዝብ የምትወክለውን የጢሮስን ከተማ ያመለክታል፡፡ (ምትክ ስም ተመልከት)