# አያያዥ ሀሳብ፡ ያህዌ ለጎግ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ # አጠቃላይ መረጃ፡ እነዚህ ሀረጎች የጎግን ሰራዊት የሚተባበሩ የተለያዩ አገራትን ይዘረዝራሉ፡፡ # በመንጋጋይ መንጠቆ አስገባለሁ እዚህ ስፍራ "በመንጋጋህ መንጠቆ" የሚለው የሚወክለው እግዚአብሔር ጎግን አንደሚቆጣጠር ነው፡፡ ሰዎች በእንስሳት አፍ ሉጋም የሚያስገቡት ወደሚፈልጉት ስፍራ ለመንዳት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) # በሙሉ ትጥቅ…ሰይፍ በመያዝ… በጋሻ እና የብረት ኮፍያ እነዚህ ሀረጋት ለጦርነት የተዘጋጀን ሰራዊት ይገልጻሉ፡፡ # ጎሜር ከጥቁር ባህር በስተ ሰሜን የሚኖሩ ህዝቦች # የቴርጋማን ቤት ይህ በሕዝቅኤል 27፡14 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡