# ወለድ ይህ ቃል ተበዳሪው ለተበደረው ገንዘብ የሚከፍለውን ገንዘብ ያመለክታል። ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ አዳዲስ ትርጉሞች በዚህ ምንባብ ያለውን “የትኛውም ወለድ” የሚለውን “እጅግ የበዛ ወለድ” ብለው ይተረጉሙታል። # እንደ ሥርዓቴ ይሄዳል ሥርዓቶቹ ሰውየው የሚሄድባቸው መንገዶች የሆኑ ይመስል እግዚአብሔር ሥርዓቶቹን ስለሚታዘዝ ሰው ይናገራል። አ.ት፡ “ሥርዓቶቼን ይታዘዛል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)