# ከፉብን፣ አሰቃዩንም በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት አንድ ነገር ነው። ግብፃውያን የጭካኔ ተግባር እንደ ፈጸሙባቸው አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet) # አደረገብን እዚህ ጋ “እኛ” የሚያመለክተው በግብፅ ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤል ሕዝብ ነው። ተናጋሪው በግብፅ ቢኖርም ባይኖርም ራሱን ከሕዝቡ አንዱ አድርጎ ይጨምራል። (See: Inclusive “We”) # ድምፃችንን ሰማ እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው እና ጩኸቱን ወይም ጸሎቱን ነው። አ.ት፡ “ጩኸታችንን ሰማ” ወይም “ጸሎታችንን ሰማ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት) # ስቃያችንን፣ ልፋታችንን እና መጨቆናችንን “ግብፃውያን ያሰቃዩን የነበረውን፣ ስንሠራው የነበረውን በጣም ከባድ የሆነውን ሥራ እና ግብፃውያኑ ይጨቁኑን የነበረውን”