# አጠቃላይ መረጃ የሌዋውያን ዝርዝሮችን በየወገናቸው ይቀጥላል። ( ስሞችን እንዴት እንደሚተረጉሙ ፡ይመልከቱ) # የቀአት ልጆች አራት ነበሩ “ቀአት 4 ወንዶች ልጆች ነበሩት” # አሮን እጅግ ቅዱስ የሆነውን ነገር ለመለየት ተመርጧል ይህ በገቢራ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “እግዚአብሔር እጅግ የተቀደሱ ነገሮችን እንዲቀድስ አሮን መረጠ” ( ገቢራዊን እና ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ) # ለዘላለምም በስሙ በረከትን መስጠት እዚህ “በስሙ” የሚለው እንደ እርሱ ተወካይ የመናገርን ስልጣን ያመለክታል ፡፡ ኣት: - “እንደ እግዚአብሔር ወኪል በመሆን ሰዎችን ለዘላለም ይባርክ” ( የባህሪ ስምን ፡ ይመልከቱ) # ወንዶች ልጆቹ ሌዋውያን እንደ ሆኑ ተቆጠሩ የአሮን ወንዶች ልጆች እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የሌዋውያን ነገድ ነበሩ ፣ ነገር ግን የሙሴ ልጆችም እንደ ሌዋውያን ተቆጥረዋል ፡፡ ይህ በገቢራዊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል ፡፡ ኣት: - “ሕዝቡ የሙሴን ልጆች የሌዊ ነገድ ክፍል እንደሆኑ አድርገው ይመለከቱ ነበር” ( ገቢራዊን እና ተብሮአዊን ፡ይመልከቱ)