am_tn/isa/28/03.md

16 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አጠቃላይ መረጃ፡-
ኢሳይያስ የሰማሪያ ሕዝበና ከተማ አክሊል እንደሆኑ አድርጎ መናገሩን ይቀጥላል፡፡ (ኢሳይያስ 28፡1-2 ተመልከት)
# የኤፍሬም ሰካራሞች ትዕቢት አክሊል በእግር ይረገጣል
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የጠላት ሠራዊት አበባን በእግራቸው እንደሚያደቅቁ የሰማሪያን ትዕቢተኛ ሰካራሞች ያደቅቋቸዋል፡፡' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
# የኤፍሬም … ትዕቢት አክሊል … በወፍራሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች
"አክሊል' ከአበባ የተሠራ ዘውድ ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ከለምለሙ ሸለቆ በላይ የተቀመጠችውን፣ የእስራኤልን ዋና ከተማ፣ የሰማሪያ ከተማን ይወክላል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# የረገፈች … ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች
ይህ ከመከር በፊት የበሰለች በለስን እንዳየና ፈጥኖ እንደሚበላ ሰው የጠላት ወታደሮች የሰማሪያን ውበት እንደሚያዩና ፈጥነው እንደሚበዘብዟት ይናገራል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)