"first commit"

This commit is contained in:
Bruce McLean 2017-09-06 06:45:44 -04:00
commit 9ccdc8c7be
54 changed files with 2708 additions and 0 deletions

30
LICENSE.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,30 @@
# License
## Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 International (CC BY-SA 4.0)
This is a human-readable summary of (and not a substitute for) the [license](http://creativecommons.org/licenses/by-sa/4.0/).
### You are free to:
* **Share** — copy and redistribute the material in any medium or format
* **Adapt** — remix, transform, and build upon the material
for any purpose, even commercially.
The licensor cannot revoke these freedoms as long as you follow the license terms.
### Under the following conditions:
* **Attribution** — You must attribute the work as follows: "Original work available at https://door43.org/." Attribution statements in derivative works should not in any way suggest that we endorse you or your use of this work.
* **ShareAlike** — If you remix, transform, or build upon the material, you must distribute your contributions under the same license as the original.
**No additional restrictions** — You may not apply legal terms or technological measures that legally restrict others from doing anything the license permits.
### Notices:
You do not have to comply with the license for elements of the material in the public domain or where your use is permitted by an applicable exception or limitation.
No warranties are given. The license may not give you all of the permissions necessary for your intended use. For example, other rights such as publicity, privacy, or moral rights may limit how you use the material.
Use of trademarks: unfoldingWord is a trademark of Distant Shores Media and may not be included on any derivative works created from this content. Unaltered content from http://unfoldingword.org must include the **unfoldingWord** logo when distributed to others. But if you alter the content in any way, you must remove the **unfoldingWord** logo before distributing your work.
Attribution of artwork: All images used in these stories are © Sweet Publishing ([www.sweetpublishing.com](http://www.sweetpublishing.com)) and are made available under a Creative Commons Attribution-Share Alike License ([http://creativecommons.org/licenses/by-sa/3.0](http://creativecommons.org/licenses/by-sa/3.0)).

68
content/01.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,68 @@
# 1. ፍጥረት #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-01.jpg)
ከዚህ ቀጥሎ የምንመለከተው እግዚአብሔር የሁሉምነገር ጀማሪ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር ዓለምንንና በውስጧ የሚገኙትን ነገሮች በስድስትቀናት ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር ምድርን ከፈጠረበኋላ ምድር ጨለማና ባዶ ነበረች፤ በውስጧምንም ነገር ገና አልተፈጠረም ነበር፡፡ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ በውሆች ላይሰፍፎ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-02.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር ‹‹ብርሃን ይሁን›› አለ ብርሃንም ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አይቶ ‹‹ቀን›› ብሎ ጠራው፡፡ እግዚአብሔርም ቀኑን ከጨለማ ለይቶ ጨለማውን ሌሊት ብሎ ጠራው፡፡ እግዚአብሔርም በመጀመሪያው ቀን ብርሃንን ፈጠረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-03.jpg)
በሁለተኛው ቀን እግዚአብሔር ከምድር በላይ ያለውን ጠፈር ፈጠረ፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር ውሃን ከጠፈር ለየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-04.jpg)
በሦስተኛው ቀን እግዚአብሔር ውሃውን ከደረቁ መሬት እንዲለይ አደረገ፡፡ እግዚአብሔርም ደረቁን መሬት ‹‹ምድር›› ውሃውንም ‹‹ባሕር›› ብሎ ጠራው፡፡ እግዚአብሔርም የፈጠረው ነገር መልካም እንደ ሆነ አየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-05.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር ምድር ሁሉንም ዓይነት ዛፎችንና ተክሎችን ታብቅል አለ፣ እንዲሁም ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም የፈጠረው ነገር መልካም እንደ ሆነ አየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-06.jpg)
በአራተኛው የፍጥረት ቀን እግዚአብሔር ፀሐይን፣ ጨረቃንና ክዋክብትን ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር ቀንና ሌሊትንም ወቅቶችንና ዓመታትንም እንዲለዩ አደረገ፡፡ እግዚአብሔርም የፈጠረው ነገር መልካም እንደ ሆነ አየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-07.jpg)
በአምስተኛው ቀን እግዚአብሔር በውሃ ውስጥ የሚኖሩትንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር ያ መልካም እንደ ሆነ አየ የተፈጠሩትንም ባረካቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-08.jpg)
በስድስተኛውም ቀን፣ እግዚአብሔር ‹‹በምድር ላይ ሁሉም ዓይነት እንስሳት ይሁኑ›› አለ፡፡ እግዚአብሔር እንዳለውም ሆነ፡፡ አንዳንዶቹ የእርሻ ከብቶች፣ አንዳንዶቹ በምድር የሚሳቡ፣ አንዳንዶቹ የዱር እንስሳት ነበሩ፡፡ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-09.jpg)
እግዚአብሔር ‹‹ሰዎችን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር እነርሱም በምድር ሁሉና በእንስሳት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-10.jpg)
ስለዚህ እግዚአብሔር ከምድር አፈር ወስዶ ሰው አድርጐ አበጀና የሕይወትን እስትንፋስ ሰጠው፡፡ የዚህም ሰው ስም አዳም ተባለ፡፡ እግዚአብሔር አዳም በሚኖርበት ስፍራ አትክልት ተከለና እንዲያለማው እዚያው አስቀመጠው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-11.jpg)
በአትክልቱም መካከል እግዚአብሔር ሁለት የተለዩ ዛፎችን ተከለ፤ የሕይወት ዛፍና መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችል የእውቀት ዛፎች ነበሩ፡፡ እግዚአብሔርም አዳምን በአትክልቱ ስፍራ ካለው መልካምንና ክፉን መለየት ከሚያስችለው የእውቀት ዛፍ በቀር በአትክልቱ ውስጥ ካለው ከየትኛውም ዛፍ መብላት እንደሚችል ተናገረው፡፡ ነገር ግን ክፉውንና መልካሙን መለየት ከሚያስችለው ዛፍ ቢበላ እንደሚሞት ተናግሮት ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-12.jpg)
እግዚአብሔር ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም እንዳይደለ ተናገረው፡፡ ከእንስሳቱ አንዳቸውም የአዳም ረዳት ሊሆኑ አልቻሉም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-13.jpg)
እግዚአብሔርም በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ሴት አድርጎ ሠራትና ወደ አዳም አመጣት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-14.jpg)
አዳምም ባያት ጊዜ እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህች እኔኑ ትመስላለች ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል፡፡ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-15.jpg)
እግዚአብሔር ወንድና ሴትን በራሱ መልክ ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ አላቸውም ‹‹ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆችም ይኑሩአችሁ ምድርንም ሙሉአት›› እግዚአብሔርም የሠራው ነገር በጣም ጥሩ እንደ ነበር አየ፡፡ በሁሉም ነገር ተደሰተ ይህ ሁሉ በስድስት ቀን ሆነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-01-16.jpg)
በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ፈጸመ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሲሠራው ከነበረው ሥራ ሁሉ አረፈ፤ ሰባተኛውንም ቀን ባረከው ቀደሰውም፡፡ ምክንያቱም በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ አርፏልና፡፡ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በውስጧም የሚገኙትን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 1-2፡፡_

52
content/02.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,52 @@
# 2. ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-01.jpg)
አዳምና ሚስቱ እግዚአብሔር በሠራላቸው የአትክልት ስፍራ ሲኖሩ በጣም ደስተኞች ነበሩ፡፡ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ ይሁን እንጂ ራቁታቸውን መሆናቸው እንዲተፋፈሩ አላደረጋቸውም፤ ምክንያቱም ኃጢአት በዓለም አልነበረም፡፡ እነርሱም በአትክልቱ ስፍራ እየተመላለሱ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገሩ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-02.jpg)
ነገር ግን ተንኮለኛ እባብ በአትክልቱ ውስጥ ነበር፡፡ ሴትየዋንም ጠየቃት ‹‹እግዚአብሔር በእርግጥ በአትክልቱ ውስጥ ካለው ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ እንዳትበሉ ብሎችኋልን? አላት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-03.jpg)
ሴቲቱም፣ ‹‹እግዚአብሔር ክፉንና መልካሙን ከሚያሳውቀው የእውቀት ዛፍ በስተቀር ከማንኛውም የዛፍ ፍሬ መብላት እንደምንችል ተናግሮናል፡፡ ነገር ግን ያንን ፍሬ ብትበሉ ወይም ብትነኩት እንኳ ትሞታላችሁ›› አለን፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-04.jpg)
እባቡም ለሴቲቱ መልሶ፣ ‹‹ይህ እውነት አይደለም አትሞቱም ከፍሬው በበላችሁ ጊዜ ዓይናችሁ እንደሚከፈትና መልካምና ክፉን በማወቅ እንደ እግዚአብሔርእንደምትሆኑ እግዚአብሔርስለሚያውቅ ነው አትብሉት ያላችሁ›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-05.jpg)
ሴቲቱ የዛፉ ፍሬ ለመብል መልካም፣ ለዓይን የሚያስደስትና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፡፡ ከእርሷም ጋር ለነበረው ለባሏም ሰጠችው፡፡ እርሱም ከዛፉ ፍሬ በላ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-06.jpg)
ወዲያውም የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፡፡ ራቁታቸውን መሆናቸውንም ተገነዘቡ፤ ቅጠልም እንደ ልብስ ሰፍተው ገላቸውን ለመሸፈን ሞከሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-07.jpg)
ሰውዬውና ሚስቱም የእግዚአብሔር ድምፅ በአትክልቱ መካከል ሲመላለስ ሰምተው ሁሉም ከእግዚአብሔር ፊት ተሸሸጉ፡፡ እግዚአብሔርም አዳምን ጠርቶ ‹‹የት ነህ? አለው፡፡ አዳምም ‹‹በአትክልቱ ስፍራ ስትመላለስ ሰማሁ ራቁቴን ስለ ሆንኩ ፈራሁ ተሸሸግሁም›› ብሎ መለሰ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-08.jpg)
እግዚአብሔርም ‹‹ራቁትህን መሆንህን ማን ነገረህ? ከርሱ እንዳትበላ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን? አለው፡፡ አዳምም፣ ‹‹ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ›› አለው፡፡ እግዚአብሔር ሴቲቱንም ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው? አላት፡፡ እርሷም፣ ‹‹እባብ አሳሳተኝና በላሁ›› አለች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-09.jpg)
እግዚአብሔር እባቡን እንዲህ አለው፤ ‹‹የተረገምህ ነህ፣ በደረትህ ትሳባለህ አፈርም ትበላለህ አንተና ሴቲቱ ጥለኞች ትሆናላችሁ የአንተ ልጆችና የእርሷም ልጆች እንዲሁ ጥለኞች ይሆናሉ የሴቲቱ ዘር ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም ተረከዙን ታቆስላለህ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-10.jpg)
እግዚአብሔር ሴቲቱንም አላት ‹‹በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፣ ፍላጎትሽ ወደ ባልሽ ይሆናል እርሱም የበላይሽ ይሆናል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-11.jpg)
እግዚአብሔርም አዳምን እንዲህ አለው፡፡ ‹‹የሚስትህን ቃል ሰምተህ አትብላ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ ፍሬ በልተሃልና ምድር ካንተ የተነሣ ተረግማለች፡፡ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ምግብህን ጥረህ ግረህ ከእርሷ ታገኛለህ፡፡ ከዚያም ትሞታለህ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ፡፡›› አዳምም ሚስቱን የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ሔዋን ብሎ ጠራት ትርጓሜውም ሕይወት ሰጪ ማለት ነው፤ እግዚአብሔርም ከእንስሳ ቆዳ አዘጋጅቶ አዳምንና ሔዋንን አለበሳቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-02-12.jpg)
እግዚአብሔርም ሰው መልካምንና ክፉን ለይቶ በማወቅ ረገድ አሁን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል አሁን ደግሞ እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ቀጥፎ እንዳይበላና ለዘላለምም እንዳይኖር አዳምና ሔዋንን ከውቡ የአትክልት ስፍራ አስወጣቸው፡፡ ከዚያም ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅና ማንም ከዚህ የሕይወት ዛፍ ቀጥፎ እንዳይበላ ኃይለኞች መላእክትን በአትክልቱ ስፍራ አኖረ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ዘፍጥረት 3_

68
content/03.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,68 @@
# 3. የጥፋት ውሃ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-01.jpg)
ከረጅም ጊዜ በኋላ ብዙ ሕዝቦች በዓለም ይኖሩ ነበር፡፡ እነርሱም በጣም ክፉዎችና ኃይለኞች ሆኑ፡፡ ክፋትም በጣም እየበዛ በመምጣቱ እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ በሚያጥለቀልቅ የጥፋት ውሃ አጠፋለሁ ሲል ወሰነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-02.jpg)
ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አገኘ፡፡ ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፡፡እግዚአብሔርም ሊልክ ስላቀደው የጥፋት ውሃለኖኅ ነገረው፡፡ ኖኅ ግዙፍ መርከብ እንዲሠራ እግዚአብሔርነገረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-03.jpg)
እግዚአብሔርም ለኖኅ መርከብ እንዲሠራ ነገረው፡፡ የመርከቢቱም ርዝመት 140 ሜትር ወርዷ 23 ሜትር ከፍታዋ 13.5 ሜትር ይሁን አለ፡፡ ኖኅ የሚሠራት መርከብ ከእንጨት የተሠራች ሆና ባለ ሦስት ፎቅ፤ ብዙ ክፍሎች ጣራና መስኮት ያሉአት ነበረች፤ መርከቢቱም ኖኅንና ቤተ ሰቡን፣ ሁሉንም ዓይነት የምድር ላይ እንስሳት ከጥፋት ውሃ እንድትጠብቅ ነገረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-04.jpg)
ኖኅም እግዚአብሔርን በመታዘዘ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸውም ኖኅና ሦስቱ ልጆቹ መርከቢቱን ሠሩ፡፡ መርከቧ በጣም ትልቅ ነበረችና ሲሠራ ብዙ ዓመታት ፈጀ፡፡ ኖኅ ስለሚመጣው የጥፋት ውሃ ለሕዝቡ እያስጠነቀቀ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ይነግራቸው ነበር ይሁን እንጂ አላመኑትም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-05.jpg)
እግዚአብሔር ኖኅንና ቤተ ሰቡን በቂ ምግብ ለራሳቸውና ለእንስሳቱ እንዲያከማቹ አዘዘ ሁሉም ነገር ዝግጁ በሆነ ጊዜ ወደ መርከቢቱ ለመግባት ለኖኅ፣ ለሚስቱ፣ ለሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ለሚስቶቻቸው ጊዜው መድረሱን ነገረው፡፡ ስምንት ሰዎችም ወደ መርከቢቱ ገቡ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-06.jpg)
እግዚአብሔር ከጥፋት ውሃው እንዲጠበቁ የሁሉንም ተባእትና እንስት እንስሳት ወፎችን ጨምሮ ወደ ኖኅ ላከ፡፡ ለመሥዋዕት የሚያገለግሉ ሰባት ተባእትና ሰባት እንስት ከሁሉም ዓይነት እንስሳ ወደ ኖኅ መርከብ ላካቸው፡፡ ሁሉም ወደ መርከቡ እንደ ገቡ እግዚአብሔር ራሱ የመርከቡን በር ዘጋ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-07.jpg)
ከዚያም ዝናቡ መዝነብ ጀመረ፣ ዘነበ፣ ዘነበ፣ ዘነበ ያለማቋረጥ ለ40 ቀንና ሌሊት ዘነበ፣ ከምድርም ምንጭ ይፈልቅ ነበር፡፡ በመላው ዓለም ያለው ሁሉም ነገር በውሃ ተሸፈነ፤ ረጃጅም ተራሮች እንኳ ሳይቀሩ በውሃ ተሸፈኑ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-08.jpg)
በመርከቡ ከነበሩት ሰዎችና እንስሳት በቀር በምድር ይኖር የነበረ ነገር ሁሉ ሞተ፤ መርከቢቱም በውሃው ላይ ተንሳፍፋ በውስጧ የሚገኙትን ነፍሳት ሁሉ ከሞት አዳነች (አተረፈች)፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-09.jpg)
ዝናቡ መዝነቡን ካቆመ በኋላ መርከቢቱ ለአምስት ወራት ያህል በውሃው ላይ ተነሳፈፈች፡፡ በዚህም ጊዜ ውሃው መቀነስ ጀመረ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን መርከቢቱ በተራራው አናት ላይ አረፈች፤ ይሁን እንጂ ዓለም አሁንም በውሃ ተሸፍና ነበር፡፡ ከሦስት ወራት በኋላ የተራራ ጫፎች መታየት ጀመሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-10.jpg)
ከአርባ ቀናት በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ ደርቆ እንደ ሆነ እንዲያይ ቁራ የተባለን ወፍ/አሞራ ላከ፡፡ ቁራው እዚህም እዚያም እየበረረ ደረቅ መሬት ቢፈልግም ሊያገኝ አልቻለም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-11.jpg)
በኋላም ኖኅ ርግብ የተባለች ወፍ ላከ፡፡ ይሁን እንጂ የምታርፍበት መሬት ማግኘት ስላልቻለች ወደ ኖኅ ተመልሳ መጣች፡፡ ከሳምንት በኋላ ኖኅ እንደ ገና ርግቧን ላካት፡፡ እርሷም የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ተመለሰች ውሃው ይቀንስ ስለ ነበር ተክሎችም ደግሞ መብቀል ጀመሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-12.jpg)
ኖኅ ሌላ አንድ ሳምንት ጠብቆ ርግቢቷን ለሦስተኛ ጊዜ ሰደዳት፤ በዚህ ጊዜ የምታርፍበት ስፍራ ስላገኘች ተመልሳ አልመጣችም፡፡ ውሃው ይደርቅ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-13.jpg)
ከሁለት ወራት በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አንተ ቤተ ሰብህና እንስሳቱ በሙሉ ከመርከቧ ውጡ አለው፡፡ ቤተ ሰቡ ከመርከቢቱ ወጡ፡፡ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆችን ወለዱ ምድርንም ሞሉአት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-14.jpg)
ኖኅም ከመርከቢቱ ከወጣ በኋላ መሠዊያ ሠራና ከእያንዳንዱ እንስሳ ለመሥዋዕት ሊቀርቡ የሚችሉትን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም በመሥዋዕቱ ተደሰተ ኖኅንና ቤተ ሰቡን ባረካቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-15.jpg)
እግዚአብሔርም አለ፡፡ ‹‹ሰዎች ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ዳግም ምድርን ፈጽሞ ላልረግማት ቃል እገባለሁ፡፡ ምንም እንኳ ሰዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ኃጢአተኞች ቢሆኑም ዓለምን ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አላጠፋም›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-03-16.jpg)
እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ምልክት ይሆን ዘንድ የመጀመሪያውን ቀስተ ደመና ሠራ፡፡ ሁልጊዜ ቀስተ ደመናው በሰማይ ላይ ይታያል፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ቀስተ ደመና አማካይነት ለሕዝቡ የገባውን ኪዳን ያሳታውሳል፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 6-8_

40
content/04.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,40 @@
# 4. የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከአብርሃም ጋር #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-01.jpg)
ከጥፋት ውሃው ከብዙ ዓመታትበኋላ ሕዝቦች በዓለም ላይ እንደገና በዙ፡፡ሁሉም አንድ አይነትቋንቋ ይናገሩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ምድርን ከመሙላትይልቅ በአንድነት ተሰብስበውከተማ ሠሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-02.jpg)
እነርሱም በጣም ትምክህተኞችና እግዚአብሔር ለተናገራቸው ነገር ያልተጠነቀቁ ነበሩ፡፡ እንዲያውም ወደ ሰማይ ሊደርሱ ረጅም ሕንጻ መገንባት ጀመሩ፡፡ እግዚአብሔርም እነዚህ ሰዎች ክፉ መሥራታቸውንና በዚህም መቀጠላቸውን አየ፡፡ ከዚህም የከፋ ኃጢአት ማድረግ ይችሉም ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-03.jpg)
ስለዚህም እግዚአብሔር ቋንቋቸውን ወደ ብዙ የተለያዩ ቋንቋዎች ለወጠና ሕዝቡን በዓለም ሁሉ በተናቸው፡፡ ሊሠሩት የጀመሩት ከተማ ስም ባቢሎን ይባላል፡፡ የስሙም ትርጓሜ የተደባለቀ ወይም ግራ የተጋባ ማለት ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-04.jpg)
ከመቶ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር አብራም የተባለውን ሰው ተናገረው፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው አገርህንና ቤተ ሰብህን ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፡፡ በዚያም እባርክሃለሁ፣ ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ ስምህንም ታላቅ አደርገዋለሁ፣ የሚባርኩህን እባርካለሁ፣ የሚረግሙህንም እረግማለሁ ባንተ ምክንያትም የምድር ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-05.jpg)
አብራምም እግዚአብሔርን ታዘዘ ሚስቱን ሦራንና አገልጋዮቹን ሁሉና ንብረቱንም ሁሉ ይዞ እግዚአብሔር ወዳሳየው የከነዓን ምድር ሄደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-06.jpg)
አብራም ከነዓን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ‹‹በዙሪያህ ያለውን ሁሉ ተመልከት የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘሮችህ ውርስ አድርጌ እሰጣችኋለሁ›› አለው፡፡ አብራምም በምድር ተቀመጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-07.jpg)
ከዕለታት አንድ ቀን አብራም መልከ ጼዴቅ የተባለውን ታላቁን የእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት ተገናኘው፡፡ መልከ ጻዴቅም አብራምን ባረከው እንዲህም አለው ‹‹የሰማይና የምድር ጌታ ታላቁ እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ›› አብራምም ለመልከ ጼዴቅ ካለው ሁሉ አሥራት ሰጠው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-08.jpg)
ብዙ ዓመታት ቢያልፉም አብራምና ሦራ አሁንም ያለ ልጅ ይኖሩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ለአብራም እንደ ገና ተስፋ ሰጠው ልጅ እንደሚኖረውና ዘሮቹ እንደ ሰማይ ክዋክብት እንደሚበዙ ተናገረው፡፡ አብራምም በእግዚአብሔር ተስፋ አመነ፡፡ አብራምም በእግዚአብሔር ተስፋ በማመኑ ምክንያት ጻድቅ ሆኖ ተቈጠረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-04-09.jpg)
እግዚአብሔርምከአብራም ጋር ቃልኪዳን አደረገ፡፡ ቃልኪዳን በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡ እግዚአብሔርም አብራምን‹‹ከገዛ አብራክህ ልጅእሰጥሃለሁ›› አለው፡፡‹‹ለዘሮችህም የከነዓንን ምድር እሰጣለሁ፡፡›› አብራምግን በዚያን ጊዜ ያለ ልጅ ነበር፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 11-15_

44
content/05.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,44 @@
# 5. የተስፋው ልጅ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-01.jpg)
ከዐሥር ዓመታት በኋላ አብራምና ሦራ ከነዓን ደረሱ፣ እስከዚህ ድረስ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ ስለዚህም የአብራም ሚስት ሦራ እንዲህ አለችው ‹‹እግዚአብሔር ልጆች እንዳይኖሩኝ ስለከለከለኝና እኔም ስላረጀሁ አገልጋዬ አጋር ይህችትልህ አግባት ለኔም ልጅ ትውለድለኝ›› አለችው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-02.jpg)
ስለሆነም አብራም አጋርን አገባት፡፡ አጋርም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ አብራምም ‹‹እስማኤል›› ሲል ስም አወጣለት፤ ይሁን እንጂ ሦራ በአጋር ቀናችባት፤ እስማኤል ዐሥራ ሦስት ዓመት ሲሆነው እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-03.jpg)
እግዚአብሔርም አብራምን‹‹እኔ ኤልሻዳይ አምላክ ነኝ ካንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ›› አለው፡፡ አብራምምበግምባሩ መሬት ላይ ተደፋ እግዚአብሔርም አብራምንአለው ‹‹አንተ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ፡፡ የከነዓንን ምድር ለአንተና ለዘሮችህ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ እኔም ለዘላለም አምላካቸው እሆናለሁ አንተም በቤተ ሰብህ የሚገኘውን ወንድ ሁሉ ግረዘው›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-04.jpg)
እግዚአብሔርም ‹‹ሚስትህ ሦራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች እርሱም የተስፋው ልጅ ይሆናል ስሙን ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ ኪዳኔንም ከእርሱ ጋር አደርጋለሁ፡፡ እርሱም ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፡፡ እስማኤልንም ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤ ይሁን እንጂ ኪዳኔ ከይስሐቅ ጋር ይሆናል›› አለው፡፡ እግዚአብሔርም የአብራምን ስም ‹‹አብርሃም›› ሲል ለወጠለት ትርጓሜውም ‹‹የብዙዎች አባት›› ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር የሦራንም ስም ‹‹ሣራ›› ሲል ለወጠላት ትርጓሜውም ‹‹የብዙዎች እናት›› ማለት ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-05.jpg)
በዚያኑ ዕለት አብርሃም በቤተ ሰቡ የሚኙትን ወንዶች ሁሉ ገረዘ፡፡ ከዓመት በኋላ አብርሃም 100 ዓመት ሲሆነውና ሣራ 99 ዓመት በሆናት ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት እግዚአብሔርም እንዳላቸው ‹‹ይስሐቅ›› ሲሉ ስም አወጡለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-06.jpg)
ይስሐቅ ወጣት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር የአብርሃምን እምነት እንዲህ ሲል ፈተነው፤ ‹‹አንዱን ልጅህን ውሰድና ለኔ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ›› አለው፤ እንደ ገና አብርሃም እግዚአብሔርን ታዘዘና ልጁን ሊሠዋው አዘጋጀ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-07.jpg)
አብርሃምና ይስሐቅ መሥዋዕት ወደሚደረግበት ስፍራ መጓዝ እንደ ጀመሩ ይስሐቅ አባቱን ‹‹አባቴ ሆይ ለመሥዋዕት ማቅረቢያ እንጨቱ ይኸውና በጉ ግን የታለ? ሲል ጠየቀ፡፡ አብርሃምም ‹‹ልጄ ሆይ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል›› ሲል መለሰለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-08.jpg)
ወደ መሥዋዕት ማቅረቢያ ቦታ እንደ ደረሱ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን አስሮ በመሠዊያው ላይ አጋደመው፡፡ አብርሃምም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ፤ እግዚአብሔር ‹‹ተው በልጁ ላይ ምንም ጉዳት አታድርስበት እንደምትፈራኝና አንድያ ልጅህን ሳስተህ ለኔ እንዳልከለከልከኝ አሁን አውቄአለሁ አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-09.jpg)
በአቅራቢያው አብርሃም በቊጥቋጦ ውስጥ የታሰረ በግ አየ፡፡ እግዚአብሔር በይስሐቅ ፋንታ ለመሥዋዕት የሚሆን በግ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ አብርሃምም በደስታ በጉን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-05-10.jpg)
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፣ ‹‹አንድያ ልጅህን ሳይቀር ያለህን ሁሉ ልትሰጠኝ ፍቃደኛ ነበርህና ልባርክህ ቃል እገባለሁ፡፡ ዘሮችህ ከሰማይ ክዋክብት ይልቅ ይበዛሉ እኔን ስለ ታዘዝከኝ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ባንተ ይባረካሉ፡፡››
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 16-22፡፡_

32
content/06.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,32 @@
# 6. እግዚአብሔር ለይስሐቅ ሚስት አዘጋጀለት #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-06-01.jpg)
አብርሃም በጣም ባረጀ ጊዜ ይስሐቅ ዕድሜው ለአቅመ አዳም ደረሰ፡፡ ስለዚህ አብርሃም ከአገልጋዮቹ አንዱን ወደ ዘመዶቹ ምድር ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት እንዲያመጣለት ላከው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-06-02.jpg)
የአብርሃም ዘመዶች ወደሚኖሩበት ምድር ከረጅም ጒዞ በኋላ ደረሰ፡፡ እግዚአብሔርም የተላከውን የአብርሃምን አገልጋይ ወደ ርብቃ መራው፡፡ ርብቃ የአብርሃም ወንድም የልጅ ልጅ ነበረች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-06-03.jpg)
ርብቃ ቤተ ሰቦቿን ትታ ከአገልጋዩ ጋር ወደ ይስሐቅ ቤት ለመሄድ ተስማማች፡፡ እንደ ደረሰችም ይስሐቅ አገባት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-06-04.jpg)
ከረጅም ጊዜበኋላ አብርሃምሞተና እግዚአብሔርከአብርሃም ጋርየገባው የተስፋ ቃል ኪዳን ሁሉ ወደ ይስሐቅተላለፈ፡፡ እግዚአብሔርለአብርሃም ሊቈጠር የማይችል ዘር እንደሚኖረው ተስፋ ሰጥቶት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የይስሐቅ ሚስት ርብቃ ልጆች ልትወልድ አልቻለችም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-06-05.jpg)
ይስሐቅ ለርብቃ ጸለየላትና እግዚአብሔር መንታ ልጆችን እንድታረግዝ ፍቃዱ ሆነ፡፡ ሁለቱ ልጆች በርብቃ ማኅፀን ሳሉ እርስ በርሳቸው ይታገሉ ነበር፡፡ ርብቃም በማኅፀንዋ እየሆነ ያለው ምን እንደሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-06-06.jpg)
እግዚአብሔርም ርብቃን አላት፣ ‹‹በማኅፀንሽ ካሉት ከሁለቱ ልጆች ሁለት ሕዝቦች ይወጣሉ እነርሱም እርስ በርሳቸው ይታገላሉ ታላቁም ታናሹን ያገለግላል›› አላት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-06-07.jpg)
የርብቃ ልጆች በተወለዱ ጊዜ ታላቁ ልጅ ቀይና ፀጉራም ሆኖ ወጣ ‹ኤሳው› ሲሉትም ስም አወጡለት፤ ታናሹም ልጅ የኤሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ ስሙንም ‹ያዕቆብ› ሲሉ አወጡለት፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 24፡1-25፤ 26፡፡_

44
content/07.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,44 @@
# 7. እግዚአብሔር ያዕቆብን ባረከ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-01.jpg)
ልጆቹም እንዳደጉ ያዕቆብ ከእናቱ ጋር በቤት መቆየትን ይወድ ነበር፡፡ ኤሳው ግን አደን ማደን ይወድ ነበር፡፡ ርብቃ ያዕቆብን ትወድደው ነበር፣ ይስሐቅ ግን ኤሳውን ይወድደው ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-02.jpg)
ከዕለታት አንድ ቀን ኤሳው ከአደን ተመልሶ ሲመጣ በጣም ተርቦ ነበር፡፡ ኤሳው ያዕቆብን ‹‹እባክህ ካዘጋጀኸው ምግብ ትንሽ ስጠኝ›› አለው፡፡ ያዕቆብም በመጀመሪያ የብኩርናህን መብት ስጠኝ ሲል መለሰለት፡፡ ስለዚህም ኤሳው የብኩርናውን መብት ለያዕቆብ ሰጠው ከዚያም ያዕቆብ ከሠራው ምግብ ሰጠው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-03.jpg)
ይስሐቅ በረከቱን ለኤሳው ሊሰጠው ፈለገ፡፡ነገር ግንይህን ከማድረጉበፊት ርብቃና ያዕቆብ ይስሐቅን አታለሉት፡፡ ያዕቆብ ኤሳውንመስሎ ወደ ይስሐቅ ቀረበ፡፡ ይስሐቅ አርጅቶነበር ማየትም አይችልም ነበር፡፡ ስለዚህም ያዕቆብ የኤሳውን ልብሶችለብሶ የፍየልለምድ በአንገቱናበእጁ አድርጎ ወደ ይስሐቅ በመቅረብ ይስሐቅን አታለለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-04.jpg)
ያዕቆብ ወደ ኤሳው መጣና እንዲህ አለው፣ ‹‹እኔ ኤሳው ነኝ መጥቻለሁና ልትባርከኝ ትችላለህ›› ይስሐቅ የፍየሉን ፀጉር ዳሰሰና የልብሱንም ጠረን አሽትቶ ኤሳው እንደ ሆነ አሰበና ባረከው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-05.jpg)
ያዕቆብ የብኵርና መብቱንና በረከቱን አታልሎ ስለ ወሰደበት ኤሳው ያዕቆብን ጠላው አባታቸው ከሞተ በኋላ ሊገድለውም አሰበ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-06.jpg)
ነገር ግን ርብቃ የኤሳውን እቅድ ሰማች፡፡ ስለዚህም እሷና ይስሐቅ ከዘመዶቹ ጋር እንዲኖር ወደ ሩቅ አገር ያዕቆብን ሰደዱት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-07.jpg)
ያዕቆብ ለረዥም ዓመታት ከርብቃ ዘመዶች ጋር ኖረ፡፡ በዚያም ጊዜ ትዳር መስርቶ 12 ወንዶች ልጆችና 1 ሴት ልጅ ወለደ፡፡ እግዚአብሔርም በጣም አበለጸገው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-08.jpg)
በከነዓን ከኖረበት ከሃያ (20) ዓመታት በኋላ ያዕቆብ ከቤተ ሰቡ፣ ከሠራተኞቹና ከመንጋው ሁሉ ጋር ወደ ከነዓን ምድር ለመመለስ ወሰነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-09.jpg)
ኤሳው አሁንም ሊገድለኝ ያስብ ይሆናል ብሎ በልቡ ስላሰበ ያዕቆብ ፈራ፡፡ ስለዚህም የእጅ መንሻ እንዲሆነው የብዙ ከብቶች መንጋ ስጦታ አድርጎ ለኤሳው ላከለት፡፡ ከብቶቹን ያመጡለት የያዕቆብ አገልጋዮች ኤሳውን ‹‹አገልጋይህ ያዕቆብ እነዚህን ከብቶች ልኮልሃል እርሱም በቅርቡ ይመጣል›› አሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-07-10.jpg)
ኤሳው ግን ቀድሞውኑ ያዕቆብን ይቅር ብሎት ስለ ነበር ዳግም ለመገናኘት ደስተኞች ነበሩ፡፡ ያዕቆብ በከነዓን ምድር በሰላም ኖረ፤ ከዚያም ይስሐቅ ሞተ ያዕቆብና ኤሳው ቀበሩት እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባለት የቃል ኪዳኑ ተስፋ አሁን ከይስሐቅ ወደ ያዕቆብ ተላለፈ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 25፡27-33፡20፡፡___

64
content/08.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,64 @@
# 8. እግዚአብሔር ዮሴፍንና ቤተ ሰቡን አዳነ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-01.jpg)
ከብዙ ዓመታት በኋላ ያዕቆብ ባረጀ ጊዜ የከብቶቹን መንጋ የሚጠብቁት ወንድሞቹ እንዴት እንዳሉ እንዲያያቸው የሚወደው ልጁን ዮሴፍን ላከው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-02.jpg)
አባታቸው ያዕቆብ ዮሴፍን ከወንድሞቹ ሁሉ አብዝቶ ይወድደው ስለ ነበረና አለቃቸው እንደሚሆን ሕልም አልሞ ስለ ነበር የዮሴፍ ወንድሞች ጠሉት፡፡ ዮሴፍም ወደ ወንድሞቹ በመጣ ጊዜ ጠልፈውት ለባሪያ ነጋዴዎች ሸጡት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-03.jpg)
የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ቤት ከመመለሳቸው በፊት የዮሴፍን ቀሚስ ቀድደው በፍየል ደም ነከሩት፡፡ ከዚያም በደም የተነከረውን የዮሴፍን ቀሚስ ለአባታቸው አሳዩት፡፡ እርሱም የዱር አውሬ ዮሴፍን ገድሎታል ሲል አሰበ፤ ያዕቆብም በጣም አዘነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-04.jpg)
የባሪያ ነጋዴዎቹ ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት፡፡ በዚያን ጊዜ ግብፅ በአባይ ወንዝ አጠገብ የምትገኝ ታላቅና ኃያል አገር ነበረች፡፡ የባሪያ ነጋዴዎቹ ዮሴፍን ባርያ አድርገው ለሀብታም የመንግሥት ባለ ሥልጣን ሸጡት፡፡ ዮሴፍ ጌታውን በደንብ አድርጎ አገለገለው፡፡ እግዚአብሔርም ዮሴፍን ባረከው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-05.jpg)
የጌታው ሚስት ከዮሴፍ ጋር ለመተኛት ሞከረች፡፡ ዮሴፍ ግን በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አልሠራም ሲል እምቢ አላት፡፡ እሷም ስለ ተናደደችበት በሐሰት ከስሳው ተይዞ ወደ እሥር ቤት ተወሰደ በእሥር ቤትም ቢሆን ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ስለ ተገኘ እግዚአብሔር ባረከው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-06.jpg)
ምንም እንኳ ዮሴፍ ንጹሕ ሰው ቢሆንም ከሁለት ዓመት በኋላ አሁንም በእሥር ቤት ነበር፡፡ አንድ ሌሊት ግብፃውያን ‹ንጉሣችን› የሚሉት ፈርዖን በጣም የታወከባቸውን ሁለት ሕልሞች አለመ፡፡ ከአማካሪዎቹ አንዳቸውም የሕልሙን ትርጕም ሊነግሩት አልቻሉም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-07.jpg)
እግዚአብሔር ለዮሴፍ ሕልም የመተርጐም ችሎታ ሰጥቶት ነበር፤ ስለዚህ ፈርዖን ዮሴፍን ከእሥር ቤት ወደ ራሱ አስመጣው፡፡ ዮሴፍ ሕልሙን ተረጐመለትና እንዲህ አለው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሰባት የጥጋብ ዓመታትን ይልካል፣ ቀጥሎም ሰባት የረሀብ ዓመታት ይሆናሉ›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-08.jpg)
ፈርዖንም በዮሴፍ በጣም ተገረመ፣ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ከእርሱ ቀጥሎ ሁለተኛ ባለ ሥልጣን አድርጎ ሾመው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-09.jpg)
ዮሴፍም ሕዝቡን በሰባቱ የመልካም ምርት ዓመታት በርካታ እህል በጎተራው እንዲያከማቹ ነገራቸው፡፡ የሰባቱ የረሀብ ዓመታት በመጡ ጊዜ ዮሴፍ ከጎተራው ለሕዝቡ እህል በመሸጡ በቂ የሚበላ ምግብ አገኙ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-10.jpg)
የረሀቡ አስከፊነት በግብፅ ብቻ ሳይሆን፣ ያዕቆብና ቤተ ሰቡ በሚኖሩበት በከነዓን ምድር ደግሞ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-11.jpg)
ያዕቆብ ልጆቹ እህል እንዲሸምቱ ወደ ግብፅ ላካቸው፡፡ የዮሴፍ ወንድሞች ለእህል ሸመታ ሄደው ፊቱ በቆሙ ጊዜ ዮሴፍ መሆኑን አላስተዋሉትም ዮሴፍ ግን አውቋቸዋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-12.jpg)
ዮሴፍ ወንድሞቹን ከፈተናቸው በኋላ ተለውጠው እንደ ሆነ ለማየት እንዲህ አላቸው፣ ‹‹አትፍሩ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ ለባርነት ስትሸጡኝ ክፉ ልታደርጉብኝ ሞከራችሁ ነገር ግን እግዚአብሔር ክፉውን ለመልካም አደረገው መጥታችሁ በግብፅ ኑሩ እኔም ለእናንተና ለቤተ ሰቦቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን አቀርብላችኋለሁ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-13.jpg)
የዮሴፍ ወንድሞች ወደአገራቸው ተመልሰው ዮሴፍ በሕይወት መኖሩን ለአባታቸውለያዕቆብ በነገሩት ጊዜ ያዕቆብበጣም ደስ አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-14.jpg)
ምንም እንኳ ያዕቆብ ሽማግሌ ቢሆንም ከመላው ቤተሰቡ ጋር ወደ ግብፅ ሄዶ በዚያ ኖሩ፡፡ ያዕቆብ ከመሞቱ በፊት ልጆቹን እያንዳንዳቸውን ባረካቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-08-15.jpg)
እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባቸው የቃል ኪዳን ተስፋዎች ወደ ይስሐቅ ተላለፉ፤ ከዚያም ወደ ያዕቆብ፣ ቀጥሎም ወደ ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆቹና ቤተ ሰቦቻቸው ተላለፈ፡፡ የዐሥራ ሁለቱ ልጆች ዘሮቻቸው ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ሆኑ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 37-50፡፡___

64
content/09.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,64 @@
# 9. እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-01.jpg)
ዮሴፍ ከሞተ በኋላ ዘመዶቹ በሙሉ በግብፅ ቆዩ፡፡ እነርሱና ዘሮቻቸው ለብዙ ዓመታት እዚያ መኖራቸውን ቀጠሉ፤ ብዙ ልጆችንም አፈሩ፤ እነርሱ እስራኤላውያን ተብለው ተጠሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-02.jpg)
ከመቶዎች ዓመታት በኋላ የእስራኤላውያን ቊጥር እየበዛ መጣ፡፡ ግብፃውያንም ዮሴፍንና እነርሱን ለመርዳት ያደረገውን ሁሉ ዘነጉ፡፡ እስራኤላውያን እየበዙ በመምጣታቸው ግብፃውያን ፈሯቸው፡፡ ስለዚህ በዚያን ጊዜ ግብፅን ያስተዳድር የነበረው ፈርዖን እስራኤሎችን ለግብፃውያን ባሪያዎች አደረጓቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-03.jpg)
ግብፃውያን እስራኤላውያንን የግንብ ሥራ እንዲሠሩ፣ ከተማውን ሁሉ እንዲገነቡ በማድረግ በኃይል ያስገድዷቸው ነበር፡፡ ከባድ ሥራ ሕይወታቸውን አስቸጋሪ አደረገው፡፡ እግዚአብሔር ግን ባረካቸው ብዙ ልጆችም ነበሯቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-04.jpg)
ፈርዖን እስራኤላውያን ብዙ ሕፃናት እንዳሏቸው አየ፤ ስለዚህ ፈርዖን ከእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሲወለዱ አባይ ወንዝ ውስጥ በመወርወር እንዲገድሉ ሕዝቡን አዘዘ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-05.jpg)
አንዲት እስራኤላዊት ሴት ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷና ባለቤቷ የቻሉትን ያህል ልጁን ደበቁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-06.jpg)
የልጁ ወላጆች ልጁን ሊደብቁት ባልቻሉ ጊዜ ልጁን በሚንሳፈፍ ቅርጫት ውስጥ አድርገው በአባይ ወንዝ ዳር ባለው ቄጤማ ፊት ለፊት እንዳይገደል ሊያድኑት ወንዙ ላይ ለቀቁት፡፡ ታላቅ እህቱም የሚሆንበትን ለማየት በቅርብ ትከታተለው ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-07.jpg)
የፈርዖን ሴት ልጅ ቅርጫት አየችና በውስጡ ያለውን ተመለከተች፡፡ ሕፃኑን ባየች ጊዜ እንደ ልጇ አድርጋ ወሰደችው፡፡ እርሷም ልጁን የምትንከባከብ እስራኤላዊት ሴት ቀጠረች፡፡ የቀጠረቻትም ሴትዮ የገዛ ልጁ እናት መሆኗን ሳታውቅ ነበር፡፡ ልጁም ሲያድግና የናቱን ጡት መጥባት ባቆመ ጊዜ ሴትዮዋ ወደ ፈርዖን ልጅ መለሰችው ስሙንም ‹‹ሙሴ›› ብለው ጠሩት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-08.jpg)
አንድ ቀን ሙሴ ባደገ ጊዜ አንድ ግብፃዊ እስራኤላዊ የሆነን ባሪያ ሲመታው አየ ሙሴም እስራኤላዊ ወገኑን ሊያድነው ሞከረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-09.jpg)
ሙሴ ማንም የማያይ መስሎት ግብፃዊውን ገድሎ ቀበረው፡፡ ነገር ግን ሙሴ ያደረገውን አንድ ሰው አይቶታል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-10.jpg)
ሙሴ ያደረገውን ፈርዖን በሰማ ጊዜ ሊገድለው ሞከረ፡፡ ሙሴ ግን ከፈርዖን ወታደሮች ነፍሱን ወደሚያድንበት ከግብፅ ወደ ምድረ በዳ ሸሸ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-11.jpg)
ከግብፅ ሩቅ በሆነ ምድረ በዳ ሙሴ የበጐች እረኛ ሆነ፡፡ ከዚያም አገር ሚስት አግብቶ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-12.jpg)
አንድ ቀን ሙሴ በጐቹን እየጠበቀ ሳለ እሳት የሚነድበት ቊጥቋጦ ተመለከተ ይሁን እንጂ ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፤ ሙሴም በደንብ ለማየት ወደ ቊጥቋጦው ጠጋ አለ፡፡ ወደሚቃጠለው ቊጥቋጦ ጠጋ ሲል የእግዚአብሔር ድምፅ ‹‹ሙሴ በቅዱስ ስፍራ ቆመሃልና ከእግርህ ጫማህን አውልቅ›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-13.jpg)
እግዚአብሔርም አለ ‹‹የሕዝቤን መከራ አይቻለሁና ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ እስራኤልንም ከግብፅ ባርነት ነጻ ታወጣቸዋለህ፡፡ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተስፋ የሰጠኋቸውን የከነዓንን ምድር እሰጣቸዋለሁ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-14.jpg)
ሕዝቡ ማንላከህ ብለው ቢጠይቁኝ ምን እላቸዋለሁ ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርምሙሴን ‹‹እኔ ያለሁና የምኖር ነኝ ስለዚህ‹ያለና የሚኖር› ልኮኛልብለህ ንገራቸው›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-09-15.jpg)
ሙሴ ስለ ፈራ ወደ ፈርዖን መሄድ አልፈለገም፡፡ ምክንያቱም የንግግር ችሎታ የለኝም ብሎ በማሰቡ ነበር፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር የሙሴን ወንድም አሮንን አብሮት እንዲሄድና ሙሴን እንዲረዳው ላከው፡፡ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ፈርዖን ሕዝቡን አለቅም በሚል ልቡን ሊያደነድን እንደሚችል አስጠነቀቃቸው፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፅአት 1-4፡፡___

52
content/10.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,52 @@
# 10. ዐሥሩ መቅሠፍቶች #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-01.jpg)
ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄዱ፡፡ ‹‹የእስራኤል አምላክ ‹ሕዝቤንልቀቅ ! ይላሃል አሉት፡፡ ፈርዖን አልሰማቸውም፡፡ እስራኤላውያን ነጻ ሆነው እንዲሄዱ በማድረግፈንታ ከዚህም የከበደ ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-02.jpg)
ፈርዖን ሕዝቡን አልለቅም ማለቱን ቀጠለ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ዐሥር መቅሠፍቶችን ላከ፡፡ እግዚአብሔር በእነዚህ መቅሠፍቶች በኩል ከፈርዖንና ከግብፅ አማልክት ሁሉ ይልቅ ኃያል መሆኑን ለፈርዖን ዐሳየው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-03.jpg)
እግዚአብሔር የዓባይን ውሃ ወደ ደም ለወጠው፣ ነገር ግን ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-04.jpg)
እግዚአብሔር በግብፅ ሁሉ ላይ እንቁራሪቶችን ላከ፡፡ ፈርዖን ሙሴን እንቁራሪቶቹን እንዲያርቅ ለመነው፡፡ ሆነም ቀረ ግን እንቁራሪቶቹ ሁሉ ሞቱ፡፡ ፈርዖን ልቡን አደነደነና እስራኤላውያንን ከግብፅ እንዲወጡ አልለቀቃቸውም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-05.jpg)
ስለዚህ እግዚአብሔር ትንኞችን ላከ፡፡ ከዚያም ዝንቦችን ላከ፡፡ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠራና መቅሠፍቱን ካቆሙ እስራኤላውያን ከግብፅ መሄድ እንደሚችሉ ነገራቸው፡፡ ሙሴ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር ዝንቦችን ሁሉ ከግብፅ አስወገደ፡፡ ነገር ግን ፈርዖን ልቡን አደነደነና ሕዝቡን አልለቀቀም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-06.jpg)
ቀጥሎ እግዚአብሔር የግብፃውያን ከብቶች ሁሉ ታመው እንዲሞቱ አደረገ፡፡ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነና እስራኤላውያንን አልለቀቀም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-07.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር በፈርዖን ፊት ዐመድ ወደ ሰማይ እንዲበትን ለሙሴ ነገረው፡፡ ዐመዱን በበተነ ጊዜ በግብፃውያን ላይ የሚያም ቊስል ሆነ፣ በእስራኤላውያን ላይ ግን ቊስሉ አልሆነባቸውም፡፡ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አደነደነ፣ ፈርዖንም እስራኤላውያንን አልለቀቀም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-08.jpg)
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር በግብፅ ያለውን አብዛኛውን ቡቃያ ያጠፋና ከቤት ውጪ የነበረውን ማንኛውንም ሰው የገደለ በረዶ ላከ፡፡ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፣ ‹‹በድዬአለሁ፡፡ መሄድ ትችላላችሁ›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ስለዚህ ሙሴ ጸለየ፣ በረዶውም ከሰማይ መዝነቡን አቆመ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-09.jpg)
ነገር ግን ፈርዖን እንደ ገና ኃጢአት ሠራ ልቡንም አደነደነ፡፡ እስራኤላውያንን አልለቀቀም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-10.jpg)
ስለዚህ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ የአንበጣዎችን መንጋ አመጣ፡፡ እነዚህ አንበጣዎች በረዶው ያላጠፋውን ሰብል ሁሉ በሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-11.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር ለሦስት ቀን የቆየ ጨለማ ላከ፡፡ ግብፃውያን ከቤቶቻቸው እስከማይወጡ ድረስ በጣም ጨልሞ ነበር፡፡ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ግን ብርሃን ነበረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-10-12.jpg)
ከእነዚህ ዘጠኝ መቅሠፍቶች በኋላ እንኳ ፈርዖን አሁንም እስራኤላውያንን አልለቅም አለ፡፡ ፈርዖን ስለማይሰማ፣ እግዚአብሔር አንድ የመጨረሻ መቅሠፍት ለመላከ ወሰነ፡፡ ይህ የፈርዖንን ዐሳብ ይለውጣል፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 5-10፡፡_

36
content/11.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,36 @@
# 11. ፋሲካ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-01.jpg)
እስራኤላውያንን ካልለቀቀ የሰዎችንና የእንስሳትን ተባዕት በኵር ሁሉ እንደሚገድል እግዚአብሔር ፈርዖንን አስጠነቀቀው፡፡ ፈርዖን ይህን በሰማ ጊዜ፣ አሁንም ማመንና ለእግዚአብሔር መታዘዝ እምቢ አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-02.jpg)
እግዚአብሔር በእርሱ ያመነ የማንኛውም ሰው በኵር ወንድ ልጅ ለማዳን መንገድ አዘጋጀ፡፡ እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ፍጹም የሆነ ጠቦት መርጦ አረደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-03.jpg)
እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የጠቦቱን ደም በቤታቸው በር ላይ እንዲቀቡት፣ ሥጋውንም ጠብሰው ያለ እርሾ ከተጋገረው ቂጣ ጋር በፍጥነት እንዲበሉት ነገራቸው፡፡ ደግሞ በበሉት ጊዜ ከግብፅ ለመውጣት እንዲዘጋጁ ነገራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-04.jpg)
እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር እንዲያደርጉ እንዳዘዛቸው ሁሉንም ነገር አደረጉ፡፡ እኩለ ሌሊት ላይ እግዚአብሔር በመላው ግብፅ አልፎ ወንድ በኵርን ሁሉ ገደለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-05.jpg)
የእስራኤላውያን ቤቶች ሁሉ በሮቻቸው ደም ተቀብተው ነበር፣ ስለዚህ እግዚአብሔር በቤቶቹ አለፈ፡፡ በቤቶቹ ውስጥ የነበረው ሰው ሁሉ ዳነ፡፡ እስራኤላውያን በጠቦቱ ደም ምክንያት ዳኑ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-06.jpg)
ግብፃውያን ግን በእግዚአብሔር አላመኑም፣ ትእዛዛቱንም አልፈጸሙም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር በቤቶቻቸው አላለፈም፡፡ እግዚአብሔር የግብፃውያንን በኵር ወንዶችን ሁሉ ገደለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-07.jpg)
በእስር ቤት ካለው በኵር እስረኛ ጀምሮ እስከ ፈርዖን በኵር ድረስ እያንዳንዱ ግብፃዊ በኵር ወንድ ሞተ፡፡ ከጥልቅ ሐዘናቸው የተነሣ በግብፅ የነበሩ ብዙ ሰዎች ያለቅሱና ይጮኹ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-11-08.jpg)
በዚያው ሌሊት ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፣ ‹‹እስራኤላውያንን ይዛችሁ አሁኑኑ ሂዱ! አላቸው፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 11፡1-12፡32፡፡_

60
content/12.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,60 @@
# 12. የእስራኤላውያን ከግብፅ መውጣት #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-01.jpg)
እስራኤላውያን ከግብፅ በመውጣታቸው በጣም ደስ አላቸው፡፡ ከእንግዲህ ባሪያዎች አይደሉም፣ ወደ ተስፋዪቱ ምድርም በመጓዝ ላይ ነበሩ! ግብፃውያን ለእስራኤላውያን ወርቅና ብር ሌሎችም የከበሩ ነገሮች ሳይቀሩ የጠየቁትን ማንኛውንም ነገር ሰጡአቸውና ከግብፅ ሲወጡ ከሌሎች ብሔሮች የሆኑ አንዳንድ ሰዎች በእግዚአብሔር አምነው ከእስራኤላውያን ጋር ሄዱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-02.jpg)
እግዚአብሔር በፊታቸው በሚሄድ ቀን ረጅም በሆነ የደመና ዓምድ፣ ማታም ረጅም በሆነ የእሳት ዓምድ መራቸው፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእነርሱ ጋር ነበርና ሲጓዙ መራቸው፡፡ ማድረግ ያለባቸው ነገር ቢኖር እርሱን መከተል ብቻ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-03.jpg)
ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ፈርዖንና ሕዝቡ ዐሳባቸውን ለወጡና እስራኤላውያን እንደ ገና የእነርሱ ባሪያዎች እንዲሆኑ ፈለጉ፡፡ እግዚአብሔር ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆኑን ሕዝቡ እንዲያዩ፣ እንዲሁም እርሱ፣ ያሕዌ፣ ከፈርዖንና ከአማልክቱ የበለጠ ኃያል እንደ ሆነ ይረዱ ዘንድ ፈርዖንን ዐሳበ ግትር አደረገው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-04.jpg)
ስለዚህ ፈርዖንና ጦር ሠራዊቱ እንደ ገና ባሪያዎቻቸው ሊያደርጉአቸው እስራኤላውያንን አሳደዱአቸው፡፡ እስራኤላውያን የግብፅ ጦር ሠራዊት ሲመጣ ባዩ ጊዜ፣ በፈርዖን ጦር ሠራዊትና በቀይ ባሕር መካከል እንደ ተጠመዱ ዐወቁ፡፡ በጣም ፈርተው ስለ ነበር፣ ‹‹ከግብፅ ለምን ወጣን? መሞታችን ነው! ብለው ጮኹ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-05.jpg)
ሙሴ እስራኤላውያንን፣ ‹‹አትፍሩ! ዛሬ እግዚአብሔር ይዋጋላችሁና ያድናችኋል›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር፣ ‹‹ወደ ቀይ ባሕር እንዲንቀሳቀሱ ለሕዝቡ ንገራቸው›› ብሎ ለሙሴ ነገረው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ግብፃውያን እስራኤላውያንን ማየት እንዳይችሉ የደመናውን ዓምድ በእስራኤላውያንና በግብፃውያን መካከል አደረገው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-06.jpg)
እግዚአብሔር ለሙሴ በባሕሩ ላይ እጁን እንዲዘረጋና ውሃውን እንዲከፍለው ነገረው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር በባሕሩ መተላለፊያ መንገድ ይኖር ዘንድ ውሃውን ነፋስ ወደ ግራና ወደ ቀኝ እንዲያንቀሳቅሰው አደረገ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-07.jpg)
እግዚአብሔር ለሙሴ በባሕሩ ላይ እጁን እንዲዘረጋና ውሃውን እንዲከፍለው ነገረው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር በባሕሩ መተላለፊያ መንገድ ይኖር ዘንድ ውሃውን ነፋስ ወደ ግራና ወደ ቀኝ እንዲያንቀሳቅሰው አደረገ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-08.jpg)
እስራኤላውያን ውሃው በግራና በቀኛቸው ግድግዳ ሆኖላቸው በባሕሩ በደረቅ መሬት ላይ ተጓዙ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-09.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር ግብፃውያኑ እስራኤላውያን ማምለጣቸውን ያዩ ዘንድ ደመናውን ከመንገዱ ወደ ላይ አንቀሳቀሰው፡፡ ግብፃውያን ከኋላቸው ሆነው ሊያሳድዱአቸው ወሰኑ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-10.jpg)
ስለዚህ በባሕሩ መንገድ እስራኤላውያንን ተከተሉአቸው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ግብፃውያን እንዲጨነቁና ሰረገሎቻቸውም እንዲታሰሩ አደረገ፡፡ ‹‹ሽሹ! እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እየተዋጋላቸው ነው! ብለው ጮኹ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-11.jpg)
እስራኤላውያን ባሕሩን በደኅና ከተሻገሩ በኋላ፣ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን እንዲዘረጋ ለሙሴ ነገረው፡፡ እርሱም በታዘዘ ጊዜ፣ ውሃው በግብፃውያን ሠራዊት ላይ ተመለሰና እንደ መጀመሪያው ሆነ፡፡ መላው የግብፃውያን ጦር ሠራዊት ሰጠመ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-12.jpg)
እስራኤላውያን ግብፃውያን እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ በእግዚአብሔር አመኑ ሙሴም የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን አመኑ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-13.jpg)
ደግሞም እስራኤላውያን እግዚአብሔር ከሞትና ከባርነት ስለ አዳናቸው በብዙ ደስታ ደስ አላቸው! አሁን እግዚአብሔርን ለማገልገል ነጻ ሆኑ፡፡ እስራኤላውያን እርሱ ከግብፃውያን ጦር ሠራዊት ስለ አዳናቸው ዐዲሱን ነጻነታቸውን ለማክበርና እግዚአብሔርን ለማመስገን ብዙ መዝሙሮችን ዘመሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-12-14.jpg)
እንዴት እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ድልን እንደ ሰጣቸውና ባሪያዎች ከመሆን እንዳዳናቸው ያስታውሱ ዘንድ በያመቱ ፋሲካን እንዲያከብሩ እስራኤላውያንን አዘዛቸው፡፡ ፍጹም የሆነ ጠቦት አርደው ካልቦካ ቂጣ ጋር በመብላት ተደሰቱ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 12፡33-15፡21፡፡_

64
content/13.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,64 @@
# 13. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-01.jpg)
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በቀይ ባሕር በኩል ከመራቸው በኋላ፣ በምድረ በዳ በኩል ሲና ተብሎ ወደሚጠራ ተራራ ወሰዳቸው፡፡ ይህም ሙሴ የሚቃጠለውን ቊጥቋጦ ያየበት ተራራ ነው፡፡ ሕዝቡ በተራራው ሥር ድንኳኖቻቸውን ተከሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-02.jpg)
እግዚአብሔር፣ ‹‹ለእኔ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ፣ የከበረ ርስት፣ የንጉሥ ካህናት፣ እንዲሁም ቅዱስ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ›› ብሎ ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ ተናገረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-03.jpg)
ሕዝቡ በመንፈሳዊ በኩል ራሳቸውን ካዘጋጁ ከሦስት ቀን በኋላ፣ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፣ በመብረቅ፣ በጢስ እንዲሁም ከፍ ባለ የመለከት ድምፅ በሲና ተራራ ላይ ወረደ፡፡ ወደ ተራራው እንዲወጣ የተፈቀደው ለሙሴ ብቻ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-04.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሰጣቸውና እንዲህ አለ፣ ‹‹እኔ ከግብፅ ባርነት ያዳንኳችሁ፣ አምላካችሁ፣ ያህዌ ነኝ፡፡ ሌሎችን አማልክት አታምልኩ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-05.jpg)
‹‹ጣዖታትን አትሥራ አታምልካቸውም፣ ምክንያቱም እኔ፣ ያህዌ ቀናተኛ አምላከ ነኝ፡፡ ስሜን በከንቱ አትጥራ፣ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ ዐስብ፡፡ ይኸውም ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ሥራ፣ ምክንያቱም ሰባተኛው ቀን የምታርፍበትና እኔን የምታስታውስበት ዕለት ነው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-06.jpg)
‹‹አባትህንና እናትህን አክብር፡፡ አትግደል፡፡ አታመንዝር፡፡ አትስረቅ፡፡ አትዋሽ፡፡ የባልንጀራህን ሚስት፣ ቤቱን፣ ወይም የእርሱ የሆነውን ማንኛውም ነገር ለመውሰድ አትመኝ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-07.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር እነዚህን ዐሥር ትእዛዛት በሁለት ጠፍጣፋ ድንጋዮች ላይ ጽፎ ለሙሴ ሰጠው፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር የሚከተሉአቸው ሌሎች ብዙ ሕግጋትንና ደንቦችን ሰጣቸው፡፡ ሕዝቡ እነዚህን ሕግጋት ከፈጸሙ እግዚአብሔር እንደሚባርካቸውና እንደሚጠብቃቸው ተስፋ ሰጠ፡፡ ሕግጋቱን ካልፈጸሙ ግን እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-08.jpg)
ደግሞም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲሠሩት ስለሚፈልገው ድንኳን መግለጫ ሰጣቸው፡፡ እርሱ የመገናኛው ድንኳ ተብሎ ይጠራ ነበር፣ በትልቅ መጋረጃ የተከፈሉ ሁለት ክፍሎችም ነበሩት፡፡ እግዚአብሔር በዚያ ይኖር ስለ ነበረ፣ ከመጋረጃ በስተጀርባ ወዳለው ክፍል እንዲገባ የተፈቀደለት ሊቀ ካህን ብቻ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-09.jpg)
የእግዚአብሔርን ሕግ ያልፈጸመ ማንኛውም ሰው በመገናኛው ድንኳ ፊት ለፊት ወዳለው መሠዊያ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚሆን እንስሳ ማምጣት ይችል ነበር፡፡ ካህኑ እንስሳውን ያርድና በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው ነበር፡፡ የተሠዋው እንስሳ ደም የሰውዬውን ኃጢአት ይሸፍንና ያንን ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያነጻው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ካህናቱ ይሆኑ ዘንድ የሙሴን ወንድም አሮንን፣ እንዲሁም የአሮንን ዝርያዎች መረጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-10.jpg)
ሕዝቡ ሁላቸውም እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዛት ለመፈጸም፣ እግዚአብሔርን ብቻ ለማምለክ፣ እንዲሁም የተለዩ ሕዝቡ ለመሆን ተስማሙ፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝ ቃል ከገቡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ክፉኛ ኃጢአት ሠሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-11.jpg)
ሙሴ ለብዙ ቀናት በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር ነበር፡፡ ሕዝቡ እርሱ እስኪመለስ ድረስ መጠባበቅ ሰለቻቸው፡፡ ስለዚህ ወደ አሮን ወርቅ አመጡና ጣዖት እንዲሠራላቸው ጠየቁት!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-12.jpg)
አሮን በጥጃ ቅርፅ የወርቅ ጣዖት ሠራ፡፡ ሕዝቡ ከቊጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ጣዖቱን ማምለክ ጀመሩ፣ መሥዋዕትም ሠዉለት! በኃጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔር በጣም ተቈጣቸው፣ ሊያጠፋቸውም ዐቀደ፡፡ ነገር ግን ሙሴ ጸለየላቸው፣ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰማ እነርሱን አላጠፋቸውም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-13.jpg)
ሙሴ ከተራራው በወረደና ጣዖቱን ባየ ጊዜ፣ በጣም ተቈጥቶ እግዚአብሔር ዐሥሩን ትእዛዛት የጻፈባቸውን ድንጋዮች ሰባበረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-14.jpg)
ከዚያም ሙሴ ጣዖቱን ፈጨው፣ በውሃውም ላይ በተነው፣ ለሕዝቡም አጠጣቸው፡፡ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ መቅሠፍት ላከና ብዙዎቻቸው ሞቱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-13-15.jpg)
ሙሴ እንደ ገና ተራራው ላይ ወጣና እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር እንዲላቸው ጸለየ፡፡ እግዚአብሔር ሙሴን ሰማውና ይቅር አላቸው፡፡ ሙሴ የሰባበራቸውን ለመተካት በዐዲስ ጠፍጣፋ ድንጋዮች ላይ ዐሥሩን ትእዛዛት ጻፈ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር እስራኤላውያን ከሲና ተራራ ወደ ተስፋዪቱ ምድር መራቸው፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 19-34፡፡_

64
content/14.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,64 @@
# 14. በምድረ በዳ ተቅበዘበዙ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-01.jpg)
እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን ክፍል ለሆኑት ሕግጋት እንዲታዘዙ ለእስራኤላውያን ከነገራቸው በኋላ፣ ከሲና ተራራ ሄዱ፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከሲና ተራራ ከነዓን ተብላ ትጠራ ወደ ነበረችው ወደ ተስፋዪቱ ምድር ይመራቸው ጀመር፡፡ የደመናው ዓምድ ከፊት ለፊታቸው ወደ ከነዓን ሄደ፣ እነርሱም ተከተሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-02.jpg)
እግዚአብሔር የተስፋዪቱን ምድር ለዘሮቻቸው እንደሚሰጣቸው ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ተስፋ ሰጥቶአቸው ነበር፣ ነገር ግን አሁን በዚያች ምድር ብዙ የሕዝብ ወገኖች ይኖሩ ነበር፡፡ እነርሱም ከነዓናውያን ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ ከነዓናውያን እግዚአብሔርን አላመለኩትም ወይም አልታዘዙትም፡፡ ሐሰተኞች አማልክትን አመለኩ ብዙ ነገሮችንም አደረጉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-03.jpg)
እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዲህ ብሎ ነገራቸው፣ ‹‹በተስፋዪቱ ምድር ያሉትን ከነዓናውያንን ሁሉ አጥፉአቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር ሰላምን አታድርጉ አታግቡአቸውም፡፡ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉአቸው፡፡ ለእኔ ባትታዘዙ፣ በእኔ ፈንታ የእነርሱን ጣዖታት ታመልካላችሁ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-04.jpg)
እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ድንበር በደረሱ ጊዜ፣ ሙሴ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ አንድ ሰው፣ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን መረጠ፡፡ ሄደው ምድሪቱ ምን እንደምትመስል እንዲሰልሉ መመሪያ ሰጣቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች፣ ብርቱዎች ወይም ደካሞች መሆናቸውን ለማየት ከነዓናውያንን ደግሞ መሰለል ነበረባቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-05.jpg)
ዐሥራ ሁለቱ ሰዎች በከነዓን ለአርባ ቀን ተጓዙና ተመልሰው መጡ፡፡ ‹‹ምድሪቱ በጣም ለም ነች ሰብሉም የተትረፈረፈ ነው! ብለው ለሕዝቡ ነገሩአቸው፡፡ ዐሥሩ ሰላዮች ግን፣ ‹‹ከተሞቹ በጣም ብርቱዎች ሰዎቹም የገዘፉ ናቸው! ብንወጋቸው በእርግጥ ያሸንፉናል ይገድሉናልም! አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-06.jpg)
ወዲያውኑ ሌሎቹ ሁለት ሰላዮች፣ ካሌብና ኢያሱ፣ ‹‹የከነዓን ሰዎች ረጃጅሞችና ብርቱዎች መሆናቸው እውነት ነው፣ ነገር ግን እኛ በእርግጥ እናሸንፋቸዋለን! እግዚአብሔር ስለ እኛ ይዋጋል! አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-07.jpg)
ሕዝቡ ግን ካሌብንና ኢያሱን አልሰሙአቸውም፡፡ ሙሴንና አሮንን ተቈጡአቸውና፣ ‹‹ወደዚህ አስከፊ ቦታ ለምን አመጣችሁን? በጦርነት ከምንሞትና ሚስቶቻችን እንዲሁም ልጆቻችን ባሮች ከሚሆኑ ይልቅ በግብፅ ብንኖር ይሻለን ነበር›› አሉ፡፡ ሕዝቡ ወደ ግብፅ መልሶ የሚወስዳቸው የተለየ መሪ ለመምረጥ ፈለጉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-08.jpg)
እግዚአብሔር በጣም ተቈጣና ወደ መገናኛው ድንኳ መጣ፡፡ እንዲህም አለ፣ ‹‹እናንተ በእኔ ላይ ስላመፃችሁ፣ ሕዝቡ ሁሉ በምድረ በዳ ይቅበዘበዛሉ፡፡ ከኢያሱና ከካሌብ በቀር ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሁሉ በዚያ ይሞታሉ እንጂ ከቶ ወደ ተስፋዪቱ ምድር አይገቡም፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-09.jpg)
ሕዝቡ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ኃጢአት በመሥራታቸው ዐዘኑ፡፡ የጦር መሣሪያዎቻቸውን ይዘው የከነዓንን ሰዎች ለመውጋት ሄዱ፡፡ ሙሴ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ስላልነበረ እንዳይሄዱ አስጠነቀቃቸው፣ ነገር ግን እርሱን አልሰሙትም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-10.jpg)
እግዚአብሔር አብሮአቸው ወደ ጦርነቱ አልሄደም፣ ስለዚህ ተሸነፉ ብዙዎቻቸውም ተገደሉ፡፡ ከዚያም እስራኤላውያን ከከነዓን ተመለሱና በምድረ በዳ ለአርባ ዓመት ተቅበዘበዙ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-11.jpg)
የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ በተቅበዘበዙባቸው አርባ ዓመታት እግዚአብሔር መገባቸው፡፡ ከሰማይ ‹‹መና›› ተብሎ የሚጠራ እንጀራ ሰጣቸው፡፡ ደግሞም ሥጋ ይበሉ ዘንድ ወደ ሰፈራቸው ድርጭቶች ላከላቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ልብሳቸውና ጫማቸው እንዳያልቅ አደረገ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-12.jpg)
እግዚአብሔር ተአምራዊ በሆነ መንገድ ውሃ እንኳ ከአለት ሰጣቸው፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ ግን የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ አማረሩ አጕረመረሙም፡፡ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለሰጠው ተስፋ አሁንም የታመነ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-13.jpg)
ሕዝቡ ምንም ውሃ ባልነበራቸው በሌላ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሙሴ፣ ‹‹አለቱን ተናገረው፣ ከእርሱም ውሃ ይወጣል›› አለው፡፡ ነገር ግን ሙሴ ለአለቱ በመናገር ፈንታ በበትር ሁለት ጊዜ ስለመታው በሕዝቡ ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን አዋረደ፡፡ ሁለም ሰው እንዲጠጣ ከአለቱ ውሃ ወጣ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በሙሴ ላይ ተቈጣና፣ ‹‹ወደ ተስፋዪቱ ምድር አትገባም›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-14.jpg)
እስራኤላውያን ለአርባ ዓመት በምድረ በዳ ከተቅበዘበዙ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁት ሁሉ ሞቱ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ገና ወደ ተስፋዪቱ ምድር ዳርቻ መራቸው፡፡ አሁን ሙሴ አርጅቶ ነበር፣ ስለዚህ ሕዝቡን በመምራት እንዲያግዘው እግዚአብሔር ኢየሱን መረጠ፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር አንድ ቀን እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እንደሚልክ ለሙሴ ተስፋ ሰጠው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-14-15.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር የተስፋዪቱን ምድር ለማየት ይችል ዘንድ ወደ ተራራ ራስ ላይ እንዲወጣ ለሙሴ ነገረው፡፡ ሙሴ የተስፋዪቱን ምድር ዐየ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ እርስዋ እንዲገባ አልፈቀደለትም፡፡ ከዚያም ሙሴ ሞተ፣ እስራኤላውያንም ለሠላሳ ቀናት ዐዘኑ፡፡ ኢያሱ ዐዲሱ መሪአቸው ሆነ፡፡ ኢያሱ በእግዚአብሔር ያመነና የታዘዘውም ስለ ነበር ጥሩ መሪ ነበር፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘጸአት 16-17፤ ዘኍልቁ 10-14፤ 20፤ 27፤ ዘዳግም 34፡፡_

56
content/15.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,56 @@
# 15. የተስፋዪቱ ምድር #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-01.jpg)
በመጨረሻ እስራኤላውያን ወደ ተስፋዪቱ ምድር፣ ወደ ከነዓን የሚገቡበት ጊዜ ደረሰ፡፡ ኢያሱ በብርቱ ግንብ ተጠብቃ ወደ ነበረችው የከነዓናውያን ከተማ ኢያሪኮ ሁለት ሰላዮችን ላከ፡፡ በዚያች ከተማ ሰላዮቹን የሸሸገችና ኋላ ላይ እንዲያመልጡ የረዳቻቸው ረዓብ የተባለች ጋለሞታ ትኖር ነበር፡፡ እርስዋ በእግዚአብሔር ስላመነች ይህን አደረገች፡፡ ሰላዮቹ፣ እስራኤላውያን ኢያሪኮን በሚያጠፉበት ጊዜ ረዓብንና ቤተ ሰብዋን እንደሚያድኑአቸው ቃል ገቡላት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-02.jpg)
እስራኤላውያን ወደ ተስፋዪቱ ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ መሻገር ነበረባቸው፡፡ እግዚአብሔር፣ ‹‹መጀመሪያ ካህናቱ እንዲሻገሩ አድርግ›› ብሎ ለኢያሱ ነገረው፡፡ ካህናቱ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መግባት በጀመሩ ጊዜ፣ እስራኤላውያን በደረቅ መሬት መሻገር ይችሉ ዘንድ ከላይ በኩል የነበረው ውሃ መፍሰሱን አቆመ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-03.jpg)
ሕዝቡ የዮርዳኖስን ወንዝ ከተሻገሩ በኋላ፣ እግዚአብሔር ኃይለኛውን የኢያሪኮ ከተማ እንዴት እንደሚወጋት ለኢያሱ ነገረው፡፡ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታዘዙ፡፡ ወታደሮቹና ካህናቱ ልክ እግዚአብሔር እንደ ነገራቸው በቀን አንዴ ለስድስት ቀናት የኢያሪኮን ከተማ ዞሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-04.jpg)
ከዚያም በሰባተኛው ቀን፣ እስራኤላውያን ሰባት ጊዜ ከተማይቱን ዞሩ፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ከተማዪቱን እየዞሩ እያሉ ወታደሮቹ ጮኹ፣ ካህናቱም መለከቶቻቸውን ነፉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-05.jpg)
ከዚያም በኢያሪኮ ዙሪያ የነበረው ግንብ ወደቀ! እግዚአብሔር እንዳዘዘው እስራኤላውያን በከተማይቱ የነበረውን ነገር ሁሉ አጠፉ፡፡ የእስራኤላውያን ወገን የሆኑትን ረዓብንና ቤተ ሰብዋን ብቻ አዳኑአቸው፡፡ በከነዓን የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦች እስራኤላውያን ኢያሪኮን እንዳጠፉአት በሰሙ ጊዜ፣ እስራኤላውያን እነርሱንም ደግሞ እንደሚወጉአቸው በማሰብ ፈሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-06.jpg)
እግዚአብሔር በከነዓን ካሉ ከማናቸውም የሕዝብ ወገኖች ጋር የሰላም ስምምነት እንዳያደርጉ እስራኤላውያንን አዞአቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ገባዖናውያን የተባሉት ከከነዓናውያን ሕዝብ ወገኖች አንዱ የሆኑት፣ ከከነዓን ራቅ ብሎ ከሚገኝ ቦታ የመጡ መሆናቸውን ለኢያሱ ዋሽተው ነገሩት፡፡ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት እንዲያደርግ ኢያሱን ጠየቁት፡፡ ገባዖናውያን ከየት እንደ ሆኑ ኢያሱና እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አልጠየቁም፡፡ ስለዚህ ኢያሱ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አደረገ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-07.jpg)
ገባዖናውያን እንዳታለሉአቸው ባወቁ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ተናደዱ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት የገቡት ቃል ስለ ነበር፣ ከእነርሱ ጋር ያደረጉትን የሰላም ስምምነት ጠበቁ፡፡ ቆየት ብሎ በሌላ ጊዜ፣ በከነዓን የነበሩ ሌላ ሕዝብ ወገን ነገሥታት፣ አሞራውያን፣ የገባዖን ሰዎች ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት እንዳደረጉ ሰሙ፣ ስለዚህ ጦር ሠራዊታቸውን አንድ ላይ አስተባበሩና ገባዖናውያንን ወጉ፡፡ ገባዖናውያን እርዳታ ጥየቃ ወደ ኢያሱ መልእክት ላኩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-08.jpg)
ስለዚህ ኢያሱ የእስራኤልን ጦር ሠራዊት ሰበሰበና ወደ ገባዖናውያን ለመድረስ ሌሊቱን ሙሉ ተጓዙ፡፡ በማለዳ ሳያስቡት የአሞራውያንን ጦር ሠራዊት ወጉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-09.jpg)
በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተዋጋ፡፡ አሞራውያንን አደናገራቸውና ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ ልኮ ከአሞራውያን ብዙዎችን ገደለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-10.jpg)
ደግሞ እግዚአብሔር እስራኤል አሞራውያንን ፈጽመው ለማሸነፍ በቂ ጊዜ ይኖራቸው ዘንድ ፀሐይ በሰማይ በአንድ ቦታ እንድትዘገይ አደረገ፡፡ በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለእስራኤል ታላቅ ድል አጐናጸፋቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-11.jpg)
እግዚአብሔር እነዚያን ጦር ሠራዊት ካሸነፈ በኋላ፣ ብዙዎቹ የከነዓናውያን ሕዝብ ወገኖች እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ኢያሱና ሌሎቹ እስራኤላውያን ወጉና አሸነፉአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-12.jpg)
ከዚህ ጦርነት በኋላ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ነገድ ከተስፋዪቱ ምድር የሚደርሰውን ክፍል ሰጠው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል በድንበሮችዋ ሁሉ ሰላምን ሰጣት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-15-13.jpg)
ኢያሱ ባረጀ ጊዜ፣ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ አንድ ላይ ጠራ፡፡ ከዚያም ኢያሱ እግዚአብሔር በሲና ከእስራኤላውያን ጋር ላደረገው ቃል ኪዳን እንዲታዘዙ ለሕዝቡ ግዴታቸውን አስታወሳቸው፡፡ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው ለመኖርና ሕግጋቱን ለመከተል ቃል ገቡ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከኢያሱ 1-24፡፡_

76
content/16.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,76 @@
# 16. ነፃ አውጪዎቹ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-01.jpg)
ኢያሱ ከሞተ በኋላ፣ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አልታዘዙም፤ የቀሩትንም ከነዓናውያን ከመካከላቸው አላስወጡም ወይም የእግዚአብሔርን ሕግ አልታዘዙም፡፡ እስራኤላውያን እውነተኛ አምላክ የሆነውን ያህዌን ከማምለክ ይልቅ የከነዓናውያንን አማልክት ማምለክ ጀመሩ፡፡ እስራኤላውያን ንጉሥ አልነበራቸውም፣ ስለዚህ እያንዳንዱ ትክክል መስሎ የሚታየውን ሁሉ ያደርግ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-02.jpg)
እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አለመታዘዛቸውን በመቀጠላቸው፣ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን እንዲያጠቁአቸው አደረገ፡፡ እነዚህ ጠላቶቻቸው የእስራኤላውያንን እቃዎች ሁሉ ሰረቁ፣ ንብረታቸውንም አወደሙ፣ አብዛኞቻቸውንም ገደሉ፡፡ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝና በጠላቶቻቸው በመጨቆን ብዙ ዘመናትን ካሳለፉ በኋላ፣ ንስሐ ገቡ እግዚአብሔርንም ከጠላቶቻቸው እንዲያድናቸው ጠየቁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-03.jpg)
ከዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶቻቸው የሚያድናቸው ነፃ አውጪ ላከላቸው ለምድሪቱም ሰላምን አመጣ፡፡ ነገር ግን ሰዎቹ እግዚአብሔርን እንደ ገና ረሱ፡፡ ጣዖትንም ማምለክ ጀመሩ፤ ስለ ሆነም እግዚአብሔር በአቅራቢያቸው የሚገኙትን ጠላቶቻቸውን ምድያማውያንን አስንሣባቸው፣ አሸነፉአቸውም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-04.jpg)
ምድያማውያን የእስራኤላውያንን ሰብል ሁሉ ለሰባት ዓመታት ወሰዱ፡፡ እስራኤላውያን በጣም ፈርተው ነበር፣ በየሸለቆውና በየዋሻው ተሸሽገው ስለ ነበር ምድያማውያን ሊያገኙአቸው አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም እንዲያድናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-05.jpg)
አንድ ቀን፣ ጌዴዎን የሚባል እስራኤላዊ ምድያማውያን ሰብሉን እንዳይወስዱበት ተደብቆ እህል ይወቃ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ጌዴዎን መጥቶ እንዲህ አለው ‹‹አንተ ብርቱ ተዋጊ ሰው እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፡፡ ሂድና እስራኤልን ከምድያማውያን አድን፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-06.jpg)
የጌዴዎን አባት ለጣዖት አምልኮ የተዘጋጀ መሠዊያ ነበረው፡፡ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን ያንን መሠዊያ እንዲያፈርስ ተናገረው፡፡ ነገር ግን ጌዴዎን ሕዝቡን ስለ ፈራ እስኪመሽ ድረስ ጠበቀ፡፡ ከዚያም መሠዊያውን አፈራረሰው እስኪደቅቅ ድረስም ሰባበረው፡፡ በአጠገቡም ለእግዚአብሔር ዐዲስ መሠዊያን አዘጋጀ፡፡ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን ሠዋበት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-07.jpg)
በማግስቱ ጠዋት ሕዝቡ አንድ ሰው መሠዊያቸውን እንዳፈራረሰው ተመልክተው እጅግ ተበሳጩ፡፡ ጌዴዎንን ለመግደል ወደ ጌዴዎን ቤት ሄዱ፡፡ ነገር ግን የጌዴዎን አባት ‹‹ለምን አምላካችሁን ለማገዝ ትሞክራላችሁ? እርሱ አምላክ ከሆነ ራሱን ይከላከል! አላቸው፡፡ ይህንንም ስላለ ሕዝቡ ጌዴዎንን አልገደሉትም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-08.jpg)
ምድያማውያን አስራኤላውያንን ለመዝረፍ እንደ ገና መጡ፡፡ ቊጥራቸው እጅግ ብዙ ስለ ነበር ማንም ሊቈጥራቸው አይችልም ነበር፡፡ ጌዴዎንም ምድያማውያንን ለመውጋት እስራኤላውያንን ጠራ፡፡ እግዚአብሔር እርሱን ተጠቅሞ እስራኤልን ያድን እንደ ሆነ ለማረጋገጥ ጌዴዎን ሁለት ምልክቶችን ከእግዚአብሔር ጠየቀ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-09.jpg)
ለመጀመሪያው ምልክት ጨርቅ በምድር ላይ አድርጎ የጠዋቱ ጤዛ በጨርቁ ላይ ብቻ እንጂ በምድር ላይ እንዳይሆን ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም እንደዚያው አደረገ፡፡ በሚቀጥለው ምሽት ጌዴዎን እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ ጠየቀ፤ መሬቱ በጠዋቱ ጤዛ እንዲረጥብ ጨርቁ ግን ደረቅ ይሁን አለ፡፡ እግዚአብሔርም እንደዚያው አደረገ፡፡ እነዚህ ሁለቱ ምልክቶች እግዚአብሔር እርሱን ተጠቅሞ እስራኤልን ከምድያም እንደሚያድን ለጌዴዎን ማስረጃ ሆኑለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-10.jpg)
32,000 እስራኤላውያን ወታደሮች ወደ ጌዴዎን መጡ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ቊጥራቸው ብዙ ነው አለው፡፡ ስለዚህ ጌዴዎን መዋጋት የፈሩትን 22,000 ወታደሮችን ወደ ቤታቸው መለሳቸው፡፡ እግዚአብሔር ጌዴዎንን አሁንም የወታደሩ ቊጥር ብዙ ነው አለው፡፡ ስለሆነም ጌዴዎን 300 ወታደሮችን አስቀርቶ ሌሎቹን ወደ ቤታቸው መለሳቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-11.jpg)
በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ጌዴዎንን ‹‹ወደ ምድያማውያን ጦር ሠፈር ውረድ፣ የሚሉትንም ብትሰማ ፈጽመህ አትፍራቸው›› አለው፡፡ ስለ ሆነም ጌዴዎን ወደ ምድያማውያን ጦር ሠፈር በዚያው ሌሊት ወረደ አንድ የምድያም ወታደር ለጓደኛው በሕልሙ ‹‹የጌዴዎን ጦር የምድያምን ጦር ሲያሸንፍ›› እንዳየ ሲነገረው ሰማ፡፡ ጌዴዎን ይህን በሰማ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-12.jpg)
ከዚያም ጌዴዎን ወደ ወታደሮቹ ተመልሶ ለእያንዳንዳቸው ቀንደ መለከት፣ ማሰሮ እና ችቦ ሰጣቸው፡፡ የምድያም ሠራዊት ተኝቶ እያለ ሰፍሮ የነበረበትን የጦር ሠፈር ከበቡ፡፡ የጌድዎን 300 ወታደሮች በማሰሮው ውስጥ ችቦ ይዘው ነበር፣ የምድያም ወታደሮች ግን የችቦውን ብርሃን ማየት አልቻሉም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-13.jpg)
ከዚያም የጌዴዎን ወታሮች በሙሉ በተመሳሳይ ጊዜ ማሰሮዎቻቸውን ሰበሩ ወዲያው የችቦው ብርሃን በድንገት አበራ፡፡ ቀንደ መለከታቸውን እየነፉ ‹‹የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሠራዊት›› እያሉ ጮኹ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-14.jpg)
እግዚአብሔርም ምድያማውያንን ግራ አጋባቸው፣ እርስ በርሳቸውም ተገዳደሉ፡፡ ወዲያው በየቤታቸው ያሉ እስራኤላውያን ተጠርተው ምድያማውያንን ለማባረር ተረዳዱ፡፡ ብዙዎችን ገደሉ የተቀሩቱንም ከእስራኤል ምድር አባረሩ፡፡ በዚያን ጊዜ 120,000 የምድያም ወታደሮች ሞቱ፡፡ እግዚአብሔርም እስራኤልን አዳነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-15.jpg)
ሕዝቡም ጌዴዎንን ንጉሣቸው እንዲሆን ፈለጉ፡፡ ጌዴዎን ግን ይህን እንዲያደርጉ አልፈቀደላቸውም፤ ነገር ግን እያንዳንዳቸው ከምድያማውያን የወሰዱአቸውን የወርቅ ቀለበት እንዲያመጡ ጠየቃቸው፡፡ ሕዝቡም ለጌዴዎን እጅግ ብዙ ወርቅ ሰጡት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-16.jpg)
ጌዴዎንም ወርቁን አቅልጦ ሊቀ ካህኑ እንደሚለብሰው ልዩ ልብስ አድርጎ አሠራው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ያንን ልብስ እንደ ጣዖት ሊያመልኩት ጀመሩ፡፡ ከዚያም የተነሣ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸው እንዲያሸንፉአቸው አድርጎ ቀጣቸው፡፡ በመጨረሻም ሕዝቡ አሁንም እግዚአብሔር እንዲያድናቸው ጠየቁ፣ እግዚአብሔር ሌላ አዳኝ ላከላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-17.jpg)
እንዲህ ያለው ሁኔታ ብዙ ጊዜ ተደጋገመ፡፡ እስራኤላውያን ኃጢአትን ያደርጋሉ፣ እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል፣ እንደ ገና ንስሐ ይገባሉ፣ እግዚአብሔርም ያድናቸው ዘንድ አዳኝን ይልክላቸዋል፡፡ ለብዙ ዓመታት እግዚአብሔር እስራኤልን ለማዳን ብዙ ነፃ አውጪዎችን ልኮላቸዋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-16-18.jpg)
በመጨረሻም፣ ሕዝቡ ሌሎቹ አሕዛብ እንዳሉአቸው ንጉሥን እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ጠየቁ፡፡ በጦርነት የሚመራቸው፣ ረጅምና ጠንካራ የሆነ ንጉሥ እንዲኖራቸው ፈለጉ፡፡ እግዚአብሔር ግን ይህንን ጥያቄአቸውን አልወደደም፣ ሆኖም እንደ ፈለጉት ንጉሥን ሰጣቸው፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- መሳፍንት 1-5፣ 6-8፡፡_

60
content/17.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,60 @@
# 17. እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-01.jpg)
ሳኦል የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ ነበር፡፡ እርሱ ልክ ሕዝቡ እንደ ፈለጉት ረጅምና መልከ መልካም ነበር፡፡ ሳኦል እስራኤልን በገዛባቸው በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት ጥሩ ንጉሥ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ለእግዚአብሔር ያልታዘዘ ክፉ ሰው ሆነ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ቀን በሳኦል ቦታ ንጉሥ የሚሆን የተለየ ሰው መረጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-02.jpg)
እግዚአብሔር ከሳኦል በኋላ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊት የተባለ እስራኤላዊ ወጣት መረጠ፡፡ ዳዊት ከቤተ ልሔም ከተማ የሆነ የበጎች እረኛ ነበር፡፡ ዳዊት በተለያዩ ጊዜያት የአባቱን በጎች ሲጠብቅ፣ በጎቹን ያጠቁ አንበሳና ድብ ገድሎ ነበር፡፡ ዳዊት በእግዚአብሔር የሚያምንና ለእርሱም የሚታዘዝ ትሑትና ጻድቅ ሰው ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-03.jpg)
ዳዊት ታላቅ ወታደርና መሪ ሆነ፡፡ ዳዊት ገና ወጣት በነበረ ጊዜ ጎልያድ ተብሎ ከሚጠራ ግዙፍ ሰው ጋር ተዋጋ፡፡ ጎልያድ የሠለጠነ ወታደር፣ በጣም ብርቱ፣ እንዲሁም ቁመቱ ከሞላ ጎደል ሦስት ሜትር ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ጎልያድን ገድሎ እስራኤልን እንዲያድን ዳዊትን ረዳው፡፡ ከዚያ በኋላ ዳዊት በሕዝቡ የተመሰገነባቸውን፣ በእስራኤል ጠላቶች ላይ ብዙ ድሎችን አገኘ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-04.jpg)
ሳኦል ሕዝቡ ለዳዊት በነበራቸው ፍቅር ቀና፡፡ ሳኦል ብዙ ጊዜ ዳዊትን ሊገድለው ሞከረ፣ ስለዚህ ዳዊት ከሳኦል ተሸሸገ፡፡ አንድ ቀን ሳኦል ይገድለው ዘንድ ዳዊትን እየፈለገው ነበር፡፡ ሳኦል ዳዊት ከእርሱ ይሸሸግበት ወደ ነበረው ዋሻ ሄደ፣ ነገር ግን ሳኦል አላየውም፡፡ ዳዊትም ወደ ሳኦል በጣም ተጠግቶ ነበርና ሊገድለው ይችል ነበር፣ ነገር ግን አልገደለውም፡፡ በዚህ ፈንታ ዳዊት ንጉሥ ለመሆን እንዳልገደለው ለሳኦል ለማረጋገጥ የሳኦልን ልብስ ዘርፍ ቈረጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-05.jpg)
በመጨረሻ፣ ሳኦል በጦርነት ሞተ፣ ዳዊትም የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ ዳዊት ጥሩ ንጉሥ ነበረ፣ ሕዝቡም ወደዱት፡፡ እግዚአብሔር ዳዊትን ባረከው፣ ስኬታማም አደረገው፡፡ ዳዊት ብዙ ጦርነቶችን ተዋጋ፣ የእስራኤልን ጠላቶች እንዲያሸንፍም እግዚአብሔር ረዳው፡፡ ዳዊት ኢየሩሳሌምን አሸንፎ ያዘና ዋና ከተማው አደረጋት፡፡ በዳዊት ንግሥና ጊዜ፣ እስራኤል ኃያልና ባለ ጠጋ ሆነች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-06.jpg)
ዳዊት እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያመልኩበትና ለእርሱ መሥዋዕቶችን የሚያቀርቡበት ቤተ መቅደስ ለመሥራት ፈለገ፡፡ ሕዝቡ ለ400 ዓመት ገደማ ሙሴ በሠራው የመገናኛ ድንኳን እግዚአብሔርን ያመልኩና መሥዋዕቶችን ያቀርቡለት ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-07.jpg)
ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን መልእክት አስይዞ ነቢዩን ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፣ ‹‹አንተ የጦርነት ሰው ስለ ሆንክ ይህን ቤተ መቅደስ ለእኔ አትሠራልኝም፡፡ ልጅህ ይሠራዋል፡፡ ነገር ግን በእጅጉ እባርክሃለሁ፡፡ ከዝርያዎችህ አንዱ በሕዝቤ ላይ ንጉሥ ሆኖ ለዘላለም ይገዛል! ለዘላለም የሚገዛው ብቸኛው የዳዊት ዝርያ፣ መሲሑ ነው፡፡ መሲሑ የዓምን ሕዝቦች ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው የእግዚአብሔር ምርጥ ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-08.jpg)
ዳዊት እነዚህን ቃሎች በሰማ ጊዜ፣ ይህንን ታላቅ ክብርና ብዙ በረከቶችን ሊሰጠው ቃል ስለ ገባለት ወዲያውኑ እግዚአብሔርን አመሰገነ አወደሰም፡፡ ዳዊት እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች መቼ እንደሚያደርግ ዐላወቀም፡፡ ነገር ግን እንደ እውነቱ፣ እስራኤላውያን መሲሑ ከመምጣቱ በፊት ረዘም ላለ ጊዜ፣ ከሞላ ጐደል 1000 ዓመታት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-09.jpg)
ዳዊት በፍትሕና በታማኝነት ለብዙ ዓመታት ገዛ፣ እግዚአብሔርም ባረከው፡፡ ይሁን እንጂ፣ ወደ ሕይወቱ መጨረሻ በእግዚአብሔር ላይ ክፉኛ ኃጢአት ሠራ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-10.jpg)
አንድ ቀን የዳዊት ወታደሮች በሙሉ ከቤታቸው ሄደው ጦርነት በሚዋጉበት ጊዜ፣ እርሱ ከቤተ መንግሥቱ ውጪ ሆኖ አንዲት ቆንጆ ሴት ገላዋን ስትታጠብ ዐየ፡፡ ስምዋ ቤርሳቤህ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-11.jpg)
ዳዊት ፊቱን ወዲያ ከማዞር ፈንታ፣ ወደ እርሱ እንዲያመጣት ሰው ላከ፡፡ ከእርስዋ ጋር ተኛና ወደ ቤት መልሶ ላካት፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቤርሳቤህ አርግዣለሁ ብላ ወደ ዳዊት መልእክት ላከች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-12.jpg)
ኦርዮ ተብሎ የሚጠራው የቤርሳቤህ ባል ከዳዊት ምርጥ ወታደሮች አንዱ ነበር፡፡ ዳዊት ኦርዮን ከጦርነቱ መልሶ ጠራውና ከሚስቱ ጋር እንዲሆን ነገረው፡፡ ነገር ግን ኦርዮ የቀሩት ወታደሮች በጦርነት ላይ እያሉ ወደ ቤት አልሄድም አለ፡፡ ስለዚህ ዳዊት ኦርዮን ወደ ጦርነቱ መልሶ ላከውና ይገደል ዘንድ ጠላት እጅግ በበረታበት ቦታ እንዲያሰልፈው ለጄነራሉ ነገረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-13.jpg)
ኦርዮ ከተገደለ በኋላ ዳዊት ቤርሳቤህን አገባት፡፡ በኋላ እርስዋ የዳዊትን ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ እግዚአብሔር ዳዊት ስላደረገው ነገር በጣም ተቈጣ፣ ኃጢአቱ እንዴት ክፉ እንደ ነበረ ለዳዊት እንዲነግረው እግዚአብሔር ነቢዩን ናታንን ላከው፡፡ ዳዊት ኃጢአቱን ተናዘዘና እግዚአብሔር ይቅር አለው፡፡ ዳዊት በቀረው የሕይወቱ ዘመን በአስቸጋሪ ጊዜያት እንኳ፣ እግዚአብሔርን ተከተለ ታዘዘውም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-17-14.jpg)
ነገር ግን ዳዊት ለሠራው ኃጢአት ቅጣት ሆኖ ልጁ ሞተ፡፡ ደግሞም በቀረው የሕይወቱ ዘመን በዳዊት ቤተ ሰብ ውጊያ ነበረ፣ የዳዊት ኃይልም በእጅጉ ተዳከመ፡፡ ዳዊት ለእግዚአብሔር ያልታመነ ቢሆንም እንኳ፣ እግዚአብሔር አሁንም ለተስፋዎቹ የታመነ ነበረ፡፡ በኋላ ዳዊትና ቤርሳቤህ ሌላ ወንድ ልጅ ወለዱ፣ ስሙንም ሰሎሞን አሉት፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከ1ኛ ሳሙኤል 10፡15-19፤ 24፤ 31፤ 2ኛ ሳሙኤል 5፤ 7፤ 11-12፡፡_

56
content/18.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,56 @@
# 18. የተከፈለው መንግሥት #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-01.jpg)
ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ዳዊት ሞተ፣ ልጁ ሰሎሞንም በእስራኤል ላይይገዛ ጀመር፡፡ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ተናገረውና በይበልጥ ምን እንደሚፈልግ ጠየቀው፡፡ ሰሎሞን ጥበብን በለመነጊዜ፣ በዓለም ላይእጅግ በጣም ጠቢብ ሰው አደረገው፡፡ ሰሎሞን ብዙ ነገሮችን ተማረናበጣም ጠቢብ ፈራጅ ሆነ፡፡ ደግሞም እግዚአብሔርበጣም ባለ ጠጋ አደረገው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-02.jpg)
ሰሎሞን በኢየሩሳሌም አባቱ ዳዊት ያቀደውንና ለግንባታው የሚያስፈልጉ ነገሮች የሰበሰበለትን ቤተ መቅደሱን ሠራ፡፡ አሁን ሕዝቡ በመገናኛው ድንኳ ፈንታ በቤተ መቅደሱ እግዚአብሔርን አመለኩ መሥዋዕትንም አቀረቡለት፡፡ እግዚአብሔር መጥቶ በቤተ መቅደሱ ተገኘ፣ በዚያም ከሕዝቡ ጋር ኖረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-03.jpg)
ነገር ግን ሰሎሞን ከሌሎች አገሮች የሆኑ ሴቶችን ወደደ፡፡ ከሞላ ጐደል 1000 የሚሆኑ ብዙ ሴቶችን በማግባት ለእግዚአብሔር አልታዘዘም! ከእነዚህ ሴቶች ብዙዎቹ ከውጪ አገሮች መጡ፣ ጣዖቶቻቸውን አመጡና እነርሱኑ ማምለካቸውን ቀጠሉ፡፡ ሰሎሞን በሸመገለ ጊዜ፣ እርሱም ደግሞ የእነርሱን አማልክት አመለከ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-04.jpg)
እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ተቈጣ፣ ሰሎሞን ባለመታመኑ እንደ መቀጣጫ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ሁለት መንግሥታት እንደሚከፍል ተናገረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-05.jpg)
ሰሎሞን ከሞተ በኋላ ልጁ ሮብዓም ነገሠ፡፡ ሮብዓም ሞኝ ነበረ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ንጉሥነቱን ሊያጸድቁለት ተሰብስበው መጡ፡፡ ሰሎሞን ብዙ ከባድ ሥራ እንዳሠራቸውና ብዙ ግብር እንዳስከፈላቸው ለሮብዓም ቅሬታቸውን ተናገሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-06.jpg)
ሮብዓም በሞኝነት እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ ‹‹አባቴ ሰሎሞን ከባድ ሥራ አሠርቶናል ብላችሁ ዐስባችኋል፣ ነገር ግን እኔ ከእርሱ የባሰ ከባድ ሥራ አሠራችኋለሁ፣ ከእርሱ የባሰም በኃይል እቀጣችኋለሁ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-07.jpg)
ዐሥሩ የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች በሮብዓም ላይ ዓመፁ፡፡ ሁለት ነገዶች ብቻ ለእርሱ ባላቸው ታማኝነት ቀጠሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ነገዶች የይሁዳ መንግሥት ሆኑ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-08.jpg)
በሮብዓም ላይ ያመፁት ሌሎቹ ዐሥር የእስራኤል ሕዝብ ነገዶች ኢዮርብዓም የተባለውን ሰው ንጉሣቸው አድርገው ሾሙት፡፡ በምድሪቱ ሰሜናዊ ክፍል መንግሥታቸውን አቋቋሙ የእስራኤል መንግሥት ተብለውም ተጠሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-09.jpg)
ኢዮርብዓም በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀና ሕዝቡ ኃጢአት እንዲሠሩ አደረገ፡፡ በይሁዳ መንግሥት ባለው ቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን በማምለክ ፈንታ ሕዝቡ ያመልኩአቸው ዘንድ ሁለት ጣዖታትን ሠራላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-10.jpg)
የይሁዳና የእስራኤል መንግሥታት ጠላቶች ሆኑና ብዙ ጊዜ እርስ በርስ ተዋጉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-11.jpg)
በዐዲሲቱ የእስራኤል መንግሥት፣ ነገሥታቱ ሁሉ ክፉዎች ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ነገሥታት አብዛኞቹ፣ በእነርሱ ቦታ መንገሥ በፈለጉ ሌሎች እስራኤላውያን ተገደሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-12.jpg)
ነገሥታቱ ሁሉና አብዛኞቹ የእስራኤል መንግሥት ሕዝብ ጣዖትን አመለኩ፡፡ የጣዖት አምልኮአቸው ብዙውን ጊዜ ግብረ ገብነት የጐደለው የግብረ ሥጋ ግንኙነትና አንዳንድ ጊዜ ልጆችን መሠዋትን ያካተተ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-18-13.jpg)
የይሁዳ ነገሥታት የዳዊት ዝርያዎች ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ነገሥታት አንዳንዶቹ በትክክል የገዙና እግዚአብሔርን ያመለኩ ጥሩ ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ ነገሥታት ክፉዎችና ብልሹዎች ነበሩ፣ ጣዖታትንም ያመልኩ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ነገሥታት ልጆቻቸውን እንኳ ለሐሰት አማልክት ሠውተዋል፡፡ ደግሞም አብዛኞቹ የይሁዳ ሕዝብ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፁ ሌሎች አማልክትንም አመለኩ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከ1ኛ ነገሥት 1-6፤ 11-12፡፡_

76
content/19.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,76 @@
# 19. ነቢያቱ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-01.jpg)
እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ታሪክ በሙሉ፣ ነቢያትን ላከላቸው፡፡ ከእግዚአብሔር መልእክት ሰሙ ከዚያም የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ ነገሩአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-02.jpg)
አክአብ በእስራኤል መንግሥት ላይ በነገሠ ጊዜ ኤልያስ ነቢይ ነበረ፡፡ አክዓብ በኣል ተብሎ የሚጠራ የሐሰት አምላክ እንዲያመልኩ ሕዝቡን ያደፋፈረ ክፉ ሰው ነበር፡፡ ኤልያስ ለአክዓብ፣ ‹‹እኔ እስከምናገር ድረስ በእስራኤል ዝናብ ወይም ጠል አይኖርም›› አለው፡፡ ይህ አክዓብን በጣም አስቈጣው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-03.jpg)
እግዚአብሔር ሊገድለው ከሚፈልገው ከአክዓብ ለመሸሸግ በምድረ በዳ ወዳለ ወንዝ እንዲሄድ ለኤልያስ ነገረው፡፡ በየጠዋቱና በየምሽቱ ወፎች እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፡፡ አክዓብና ጦር ሠራዊቱ ኤልያስን ፈለጉት፣ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ ድርቁ በጣም ከባድ ነበርና በመጨረሻ ወንዙ ደረቀ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-04.jpg)
ስለዚህ ኤልያስ ወደ አንድ ጐረቤት አገር ሄደ፡፡ በዚያች አገር በረሀቡ ምክንያት አንዲት መበለትና ወንድ ልጅዋ ምግብ ሊያልቅባቸው ተቃርበው ነበር፡፡ ነገር ግን ኤልያስን ተንከባከቡት፣ እግዚአብሔርም ዱቄቱ ከማድጋ ዘይቱም ከማሰሮ እንዳይጐድል አድርጎ መገባቸው፡፡ በረሀቡ ጊዜ ሁሉ ምግብ ነበራቸው፡፡ ኤልያስ በዚያ ለአያሌ ዓመታት ተቀመጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-05.jpg)
ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ ዝናብ የሚያዘንብ መሆኑን ወደ እስራኤል መንግሥት ተመልሶ ለአክዓብ እንዲነግረው እግዚአብሔር ለኤልያስ ነገረው፡፡ አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ፣ ‹‹አንተ ችግር ፈጣሪ፣ መጣህ አይደል! አለው፡፡ ኤልያስ እንዲህ ብሎ መለሰት፣ ‹‹ችግር ፈጣሪ አንተ ነህ! እውነተኛውን አምላክ፣ ያህዌን ትተሃል፣ በኣልንም አምልከሃል የእስራኤልን መንግሥት ሕዝብ ሁሉ በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ሰብስብ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-06.jpg)
450ዎቹ የበኣል ነቢያትን ጨምሮ የእስራኤል መንግሥት ሕዝብ ሁሉ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ መጡ፡፡ ኤልያስ ለሕዝቡ፣ ‹‹ስንት ጊዜ ዐሳባችሁን ትለውጣላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን አገልግሉ! በኣል አምላክ ቢሆን እርሱን አገልግሉ! አላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-07.jpg)
ከዚያም ኤልያስ ለበኣል ነቢያት፣ ‹‹አንድ ወይፈን እረዱና መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡት፣ ነገር ግን እሳት አታንድዱ፡፡ እኔም እንደዚሁ አደርጋለሁ፡፡ በእሳት የሚመልስ አምላክ እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው›› አላቸው፡፡ ስለዚህ የበኣል ካህናት መሥዋዕት አዘጋጁ ነገር ግን እሳት አላነደዱም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-08.jpg)
ከዚያ በኋላ የበኣል ነቢያት ‹‹በኣል ሆይ፣ ስማን! ብለው ወደ በኣል ጸለዩ፡፡ ቀኑን ሙሉ ጸለዩ፣ ጮኹ፣ እንዲሁም ሰውነታቸውን በቢላዋ ቈረጡ፣ ነገር ግን መልስ አልነበረም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-09.jpg)
በመጨረሻ፣ ኤልያስ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጀ፡፡ ከዚያም ሥጋው፣ እንጨቱ፣ እንዲሁም በመሠዊያው ዙሪያ ያለው መሬት እንኳ ፍጹም እስኪረጥብ ድረስ ዐሥራት ሁለት ጋን ሙሉ ውሃ በመሥዋዕቱ ላይ እንዲያፈሱ ለሕዝብ ነገራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-10.jpg)
ከዚያም ኤልያስ እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ ‹‹ያህዌ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ እንደ ሆንክና እኔም አገልጋይህ እንደ ሆንኩ ዛሬ ዐሳየን፡፡ አንተ እውነተኛ አምላክ እንደ ሆንክ ይህ ሕዝብ ያውቅ ዘንድ መልስልኝ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-11.jpg)
ወዲያውኑ፣ እሳት ከሰማይ ወደቀና ሥጋውን፣ እንጨቱን፣ ድንጋዩን፣ ቈሻሻውን፣ እንዲሁም በመሠዊያው ዙሪያ የነበረውን ውሃ እንኳ አቃጠለ፡፡ ሕዝቡ ይህን ባዩ ጊዜ መሬት ላይ ወደቁና ‹‹ያህዌ አምላክ ነው! ያህዌ አምላክ ነው! አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-12.jpg)
ከዚያም ኤልያስ፣ ‹‹ከበኣል ነቢያት አንድም እንዳያመልጥ! አለ፡፡ ስለዚህ ሕዝቡ የበኣልን ነቢያት ያዙና ወስደው ገደሉአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-13.jpg)
ከዚያ በኋላ ኤልያስ ለንጉሥ አክዓብ፣ ‹‹ዝናብ መጥቶአልና ፈጥነህ ወደ ከተማ ተመለስ›› አለው፡፡ ወዲያውኑ ሰማዩ ጠቈረ፣ ከባድ ዝናብም መዝነብ ጀመረ፡፡ ያህዌ ድርቁን አቆመው እውተኛ አምላክ መሆኑንም አረጋገጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-14.jpg)
ከኤልያስ ዘመን በኋላ፣ እግዚአብሔር ነቢይ እንዲሆን ኤልሳዕ የተባለ ሰውን መረጠ፡፡ እግዚአብሔር በኤልሳዕ በኩል ብዙ ተአምራትን አደረገ፡፡ ከተአምራቱ አንዱ አስከፊ የቆዳ በሽታ በያዘው የጠላት ጦር ሠራዊት አዛዥ በነበረው ንዕማን ላይ ተከሠተ፡፡ ስለ ኤልሳዕ ሰምቶ ነበርና ስለዚህ እንዲፈውሰው ኤልሳዕን ሄዶ ጠየቀው፡፡ ኤልሳዕ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እንዲል ለንዕማን ነገረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-15.jpg)
በመጀመሪያ ንዕማን ተቈጣና ሞኝነት ስለ መሰለው ኤልሳዕ የነገረውን ነገር አላደረገውም፡፡ በኋላ ግን ዐሳቡን ለወጠና በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፡፡ በመጨረሻ ከውሃው በወጣ ጊዜ ቆዳው ፍጹም ተፈወሰ! እግዚአብሔር ፈወሰው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-16.jpg)
እግዚአብሔር ሌሎች ብዙ ነቢያትን ላከ፡፡ ሁላቸውም ጣዖታትን ማምለክ እንዲያቆሙና ለሌሎች ፍትሕንና ምሕረትን ማሳየት እንዲጀምሩ ለሕዝቡ ነገሩአቸው፡፡ ነቢያቱ ክፉ መሥራትን ባያቆሙና ለእግዚአብሔር መታዘዝ ባይጀምሩ፣ እግዚአብሔር በበደለኝነት እንደሚፈርድባቸው፣ እንደሚቀጣቸውም ሕዝቡን አስጠነቀቁአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-17.jpg)
አብዛኛውን ጊዜ ሕዝቡ ለእግዚአብሔር አልታዘዙም፡፡ ብዙውን ጊዜ ለነቢያት የነበራቸው አያያዝ መጥፎ ነበረ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገደሉአቸው ነበር፡፡ በአንድ ወቅት፣ ነቢዩ ኤርምያስ ደረቅ በሆነ የውሃ ጕድጓድ ውስጥ ተጥሎ በዚያ እንዲሞት ተትቶ ነበር፡፡ በጕድጓዱ መጨረሻ በነበረው ጭቃ ውስጥ ገባ፣ ነገር ግን ያኔ ንጉሡ ራራለትና ከመሞቱ በፊት ከጕድጓዱ ጐትተው እንዲያወጡት አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-19-18.jpg)
ነቢያቱ ሕዝቡ ቢጡሉአቸውም እንኳ ስለ እግዚአብሔር መናራቸውን ቀጠሉ፡፡ ንስሐ ባይገቡ እግዚአብሔር እንደሚያጠፋቸው ሕዝቡን አስጠነቀቁአቸው፡፡ ደግሞም የእግዚአብሔር መሲሕ እንደሚመጣ ስለ ሰጠው ተስፋ ለሕዝቡ አስታወሱአቸው፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከ1ኛ ነገሥት 16-18፤ 2ኛ ነገሥት 5፤ ኤርምያስ 38፡፡_

56
content/20.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,56 @@
# 20. ምርኮና ከምርኮ መመለስ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-01.jpg)
የእስራኤል መንግሥትና የይሁዳ መንግሥት ሁለቱም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠሩ፡፡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋርበሲና ተራራ ያደረገውን ቃልኪዳን አፈረሱ፡፡ እግዚአብሔርንስሐ እንዲገቡና እንደገና እንዲያመልኩት ሊያስጠነቅቃቸው ነቢያቱንላከ፣ እነርሱ ግን አንታዘዝም አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-02.jpg)
ስለዚህ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸው እንዲያጠፉአቸው በመፍቀድ ሁለቱንም መንግሥታት ቀጣቸው፡፡ የኃያልዋ፣ የጨካኝዋ አገር የአሦር ንጉሠ ነገሥት ግዛት የእስራኤልን መንግሥት አጠፋች፣ ዋጋ ያለውን ነገር ሁሉ ወሰደች፣ ከአገሪቱ አብዛኛውንም አቃጠለች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-03.jpg)
አሦርያውያን መሪዎችን፣ ሀብታሞችን፣ እንዲሁም ሙያ የነበራቸውን ሰዎች ሁሉ ሰበሰቡና ወደ አሦር ወሰዱአቸው፡፡ ያልተገደሉት በጣም ድሆች የነበሩት እስራኤላውያን ብቻ በእስራኤል መንግሥት ቀሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-04.jpg)
ከዚያም አሦራውያን የእስራኤል መንግሥት በነበረባት ምድር እንዲኖሩ ባዕዳንን አመጡ፡፡ ባዕዳኑ የፈረሱትን ከተሞች እንደገና ሠሩና በዚያ ቀርተው የነበሩትን እስራኤላውያን አገቡ፡፡ ባዕዳንን ያገቡት የእስራኤላውያን ዝርያዎች ሳምራውያን ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-05.jpg)
የእስራኤል መንግሥት ሕዝብ እግዚአብሔርን ስላላመኑበትና ስላልታዘዙት እንዴት እንደ ቀጣቸው በይሁዳ መንግሥት የነበሩት ሕዝብ ዐዩ፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን የይሁዳ መንግሥት ሕዝብ የከነዓናውያንን አማልክት ጨምሮ ጣዖታትን አመለኩ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲያስጠነቅቁአቸው ነቢያትን ላከ፣ እነርሱ ግን አንሰማም አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-06.jpg)
አሦራውያን የእስራኤልን መንግሥት ካጠፉ ከ100 ዓመታት ገደማ በኋላ የይሁዳን መንግሥት እንዲወጉ እግዚአብሔር ባቢሎናውያንን ላከ፡፡ ባቢሎን ኃያል የንጉሠ ነገሥት ግዛት ነበረች፡፡ የይሁዳ ንጉሥ የናቡከደነፆር አገልጋይ ለመሆንና በያመቱ ብዙ ገንዘብ ሊከፍለው ተስማማ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-07.jpg)
ነገር ግን ከጥቂት ዓመታት በኋላ የይሁዳ ንጉሥ በባቢሎን ላይ ዓመፀ፡፡ ስለዚህ ባቢሎናውያን ተመልሰው መጥተው የይሁዳን መንግሥት ወጉ፡፡ የኢየሩሳሌምን ከተማ ያዙ፣ ቤተ መቅደሱን አጠፉ፣ እንዲሁም የከተማይቱንና የቤተ መቅደሱን መዛግብት ሁሉ ወሰዱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-08.jpg)
የይሁዳ ንጉሥ ስላመፀበት ሊቀጣው የናቡከደነፆር ወታደሮች የይሁዳን ንጉሥ ወንድ ልጆች በፊቱ ገደሉ፤ እርሱንም ዓይኖቹን አሳወሩ፡፡ ከዚያ በኋላ በባቢሎን በእስር ቤት እንዲሞት ንጉሡን ወሰዱት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-09.jpg)
ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ በእርሻ እንዲሠሩ እጅግ በጣም ድሆች የሆኑትን ሰዎች ብቻ በመተው ከሞላ ጐደል የይሁዳን መንግሥት ሕዝብ ሁሉ ወደ ባቢሎን ማርከው ወሰዱ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ የተስፋዪቱን ምድር እንዲለቁ የተገደዱበት ይህ ወቅት ምርኮ ተብሎ ይጠራል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-10.jpg)
ምንም እንኳ እግዚአብሔር ወደ ምርኮ በመውሰድ ሕዝቡን ስለ ኃጢአታቸው ቢቀጣቸውም እነርሱንና ተስፋዎቹን አልረሳም፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን መጠበቁንና በነቢያቱ በኩል እነርሱን ማነጋገሩን ቀጠለ፡፡ ከሰባ ዓመት በኋላ፣ ወደ ተስፋዪቱ ምድር እንደ ገና እንዲመለሱ ተስፋ ሰጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-11.jpg)
ከሰባ ዓመታት ገደማ በኋላ፣ የፋርስ ንጉሥ ባቢሎንን አሸነፈ፣ ስለዚህ የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ግዛት የባቢሎንን ንጉሠ ነገሥት ግዛት ተካ፡፡ አሁን እስራኤላውያን አይሁዶች ተብለው ተጠሩ አብዛኞቻቸውም ሕይወታቸውን በሙሉ በባቢሎን የኖሩ ነበሩ፡፡ በጣም ያረጁ ጥቂት አይሁዶች ብቻ የይሁዳን ምድር አስታወሱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-12.jpg)
የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ግዛት ጠንካራ ነገር ግን ለያዛቸው ሕዝብ መሐሪ ነበር፡፡ ቂሮስ የፋርሳውያን ንጉሥ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ ወደ ይሁዳ መመለስ የፈለገ ማንኛውም አይሁዳዊ ፋርስን ለቆ ወደ ይሁዳ መመለስ እንደሚችል ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ቤተ መቅደሱን እንደገና እንዲሠሩ የገንዘብ ድጋፍ ሳይቀር አደረገላቸው! ስለዚህ በምርኮ ከቆዩባቸው ሰባ ዓመታት በኋላ፣ ጥቂት የአይሁዶች ቡድን በይሁዳ ወዳለችው ኢየሩሳሌም ከተማ ተመለሱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-20-13.jpg)
ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜ፣ ቤተ መቅደሱንና በከተማዪቱ ዙሪያ ያለውን ቅጥር እንደ ገና ሠሩ፡፡ ምንም እንኳ እስካሁን ድረስ በሌሎች ሕዝቦች የተገዙ ቢሆኑም፣ ዳግመኛ በተስፋዪቱ ምድር ኖሩና በቤተ መቅደሱ አመለኩ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከ2ኛ ነገሥት 17፤ 24-25፤ 2ኛ ዜና 36፤ ዕዝራ 1-10፤ ነህምያ 1-13፡፡_

64
content/21.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,64 @@
# 21. እግዚአብሔር መሲሑን ተስፋ ሰጠ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-01.jpg)
ገና ከመጀመሪያው፣ እግዚአብሔር መሲሑንለመላክ ዐቀደ፡፡ የመጀመሪያው የመሲሑ ተስፋ ወደ አዳምና ሔዋን መጣ፡፡ እግዚአብሔርየእባቡን ራስ የሚቀጠቅጥ የሔዋን ዘር እንደሚወለድ ተስፋ ሰጠ፡፡ ሔዋንን ያታለለው እባብ ሰይጣን ነበር፡፡ ተስፋው መሲሑ ሰይጣንን ፍጹም ያሸንፈዋል ማለት ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-02.jpg)
በእርሱ በኩል የዓለም ሕዝብ ወገኖች በሙሉ በረከት እንደሚቀበሉ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ ሰጠው፡፡ ይህ በረከት ወደ ፊት መሲሑ ሲመጣ ይፈጸማል፡፡ እርሱ በዓለም ካሉ ከሁሉም የሕዝብ ወገኖች የሆኑ ሕዝቦች እንዲድኑ ያደርጋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-03.jpg)
ወደ ፊት እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ እንደሚያስነሣ እግዚአብሔር ለሙሴ ተስፋ ሰጠው፡፡ ይህ ቆይቶ ስለሚመጣው መሲሕ የተሰጠ ሌላ ተስፋ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-04.jpg)
ከዝርያዎቹ አንዱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ንጉሥ ሆኖ ለዘላለም እንደሚገዛ እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት ተስፋ ሰጠው፡፡ ይህም መሲሑ ከዳዊት ዝርያዎች አንዱ ይሆናል ማለት ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-05.jpg)
እግዚአብሔር ዐዲስ ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ተስፋ ሰጠ፣ ይህ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር በሲና ከእስራኤል ጋር እንዳደረገው ቃል ኪዳን ግን አይደለም፡፡ በዐዲሱ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ሕጉን በሕዝቡ ልብ ይጽፋል፣ ሕዝቡ በግል እግዚአብሔርን ያውቁታል፣ ሕዝቡ ይሆናሉ፣ እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር ይላል፡፡ መሲሑ ዐዲሱን ኪዳን ይጀምራል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-06.jpg)
ደግሞም የእግዚአብሔር ነቢያት መሲሑ ነቢይ፣ ካህን እንዲሁም ንጉሥ ይሆናል አሉ፡፡ ነቢይ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቃል ለሕዝቡ የሚያውጅ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔር ለመላክ ተስፋ የሰጠው መሲሕ ፍጹም ነቢይ ይሆናል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-07.jpg)
እስራኤላውያን ካህናት ስለ ኃጢአታቸው በሚደርስባቸው ቅጣት ምትክ በሕዝቡ ፈንታ ለእግዚአብሔር መሥዋዕቶችን አቀረቡ፡፡ ደግሞም ካህናት ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ፡፡ መሲሑ ፍጹም መሥዋዕት አድርጎ ራሱን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ ፍጹም ሊቀ ካህናት ይሆናል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-08.jpg)
ንጉሥ በመንግሥቱ ላይ የሚገዛና በሕዝቡ ላይ የሚፈርድ ሰው ነው፡፡ መሲሑ በቅድማያቱ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ፍጹም ንጉሥ ይሆናል፡፡ በመላው ዓለም ላይ ለዘላለም ይገዛል፣ እንዲሁም ሁልጊዜ በቅንነት ይፈርድና ትክክለኛ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-09.jpg)
የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ተንብየዋል፡፡ ነቢዩ ሚልክያስ መሲሑ ከመምጣቱ በፊት ታላቅ ነቢይ እንደሚመጣ አስቀድሞ ተነበየ፡፡ መሲሑ ከአንዲት ድንግል እንደሚወለድ ነቢዩ ኢሳይያስ ተነበየ፡፡ ነቢዩ ሚክያስ መሲሑ በቤተ ልሔም ከተማ ይወለዳል አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-10.jpg)
ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሑ በገሊላ ይኖራል፣ ልባቸው የተሰበረ ሰዎችን ያጽናናል፣ እንዲሁም ለተማረኩት ነጻነትንና ለታሰሩት መፈታትን ያውጃል፡፡ ደግሞም ነቢዩ መሲሑ የታመሙና መስማት፣ ማየት፣ መናገር፣ ወይም መራመድ የማይችሉትን ሕዝብ እንደሚፈውስ ተነበየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-11.jpg)
ደግሞም ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሑ ያለ ምክንያት እንደሚጠላና ተቃውሞ እንደሚደርስበት ተነበየ፡፡ ሌሎች ነቢያት መሲሑን የገደሉት እነዚያ በልብሶቹ ላይ ዕጣ እንደሚጣጣሉና ወዳጁ እንደሚክደው አስቀድመው ተነበዩ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ መሲሑን ለሚክደው ወዳጅ ሠላሳ ብር እንደሚከፍሉት ተነበየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-12.jpg)
ደግሞም ነቢዩ ስለ መሲሑ አሟሟት ተናገረ፡፡ ኢሳይያስ ሰዎች መሲሑን እንደሚተፉበት፣ እንደሚያፌዙበትና እንደሚመቱት ተነበየ፡፡ ምንም ስሕተት ነገር ያላደረገ ቢሆንም እንኳ ይወጉታል በታላቅ ሕመምና ሥቃይ ይሞታል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-13.jpg)
ደግሞም ነቢያት መሲሑ ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ይሆናል አሉ፡፡ የሌሎች ሰዎችን ኃጢአት ቅጣት ለመቀበል እርሱ ሞተ፡፡ የእርሱ መቀጣት በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ሰላምን ያመጣል፡፡ በዚህ ምክንያት መሲሑን ማድቀቅ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-14.jpg)
መሲሑ እንደሚሞትና እግዚአብሔር ደግሞ ከሙታን እንደሚያስነሣው ነቢያት አስቀድመው ተነበዩ፡፡ እግዚአብሔር በመሲሑ ሞትና ትንሣኤ በኩል ኃጢአተኞችን ለማዳን ዕቅዱን ይፈጽምና ዐዲሱን ኪዳን ይጀምራል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-21-15.jpg)
እግዚአብሔር ለነቢያት ስለ መሲሑ ብዙ ነገሮችን ገለጠላቸው፣ ነገር ግን መሲሑ ከእነዚያ ነቢያት በአንዳቸውም ጊዜ አልመጣም፡፡ ከእነዚህ ትንቢቶች የመጨረሻው ከተተነበየ ከ400 ዓመታት በኋላ፣ ልክ በትክክለኛው ጊዜ፣ እግዚአብሔር መሲሑን ወደ ዓለም ይልካል፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 3፡15፤ 12፡1-3፤ ዘዳግም 18፡15፤ 2ኛ ሳሙኤል 7፤ ኤርምያስ 31፤ ኢሳይያስ 59፡16፤ ዳንኤል 7፤ ሚልክያስ 4፡5፤ ኢሳይያስ 7፡14፤ ሚክያስ 5፡2፤ ኢሳይያስ 9፡1-7፤ 35፡3-5፤ 61፡53፤ መዝሙር 22፡18፤ 35፡19፤ 69፡4፤ 41፡9፤ ዘካርያስ 11፡12-13፤ ኢሳይያስ 50፡6፤ መዝሙር 16፡10-11፡፡_

32
content/22.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,32 @@
# 22. የዮሐንስ መወለድ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-22-01.jpg)
አስቀድሞ እግዚአብሔር በመላእክቱና በነቢያቱ በኩል ለሕዝቡ ተናግሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ለእነርሱ ያልተናገረባቸው 400 ዓመታት አለፉ፡፡ በድንገት አንድ መልአክ ዘካርያስ ተብሎ ወደሚጠራ ሽማግሌ ካህን ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ይዞ መጣ፡፡ ዘካርያስና ሚስቱ ኤልሳቤጥ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ነበሩ፣ ነገር ግን እርስዋ ልጆችን መውለድ አልቻለችም ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-22-02.jpg)
መልአኩ ዘካርያስን አለው፣ ‹‹ሚስትህ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፡፡ ዮሐንስ ብለህ ተጠራዋለህ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል፣ ሕዝቡንም ለመሲሑ ያዘጋጃል! ዘካርያስ፣ ‹‹ሚስቴና እኔ ልጆችን ለመውለድ በጣም አርጅተናል! ይህ እንደሚሆን እንዴት ዐውቃለሁ? ብሎ መለሰ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-22-03.jpg)
መልአኩ ለዘካርያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ ይህን የምሥራች እንዳመጣላችሁ እግዚአብሔር ላከኝ፡፡ ስላላመንከኝ፣ ልጁ እስኪወለድ ድረስ መናገር አትችልም፡፡›› ወዲያኑ ዘካርያስ መናገር አልቻለም፡፡ ከዚያ በኋላ መልአኩ ከዘካርያስ ተለየ፡፡ ዘካርያስም ወደ ቤት ተመለሰ ሚስቱም ፀነሰች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-22-04.jpg)
ኤልሳቤጥ የስድስት ወር ነፍሰ ጡር በነበረች ጊዜ፣ ያው መልአክ በድንገት ስምዋ ማርያም ለተባለ ለኤልሳቤጥ ዘመድ ተገለጠ፡፡ እርስዋ ድንግል ነበረችና ልታገባ ዮሴፍ ለተባለ ሰው ታጭታ ነበር፡፡ መልአኩ፣ ‹‹ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስሙን ኢየሱስ ትዪዋለሽ፡፡ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል ለዘላለምም ገዥ ይሆናል›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-22-05.jpg)
ማርያም ‹‹እኔ ድንግል ስለ ሆንኩ፣ ይህ እንዴት ይሆናል? ብላ መለሰች፡፡ መልአኩ እንዲህ ብሎ አብራራ፣ ‹‹መንፈስ ቅዱስ ወደ አንቺ ይመጣል፣ የልዑል ኃይል ይጸልልሻል፡፡ ስለዚህ ልጁ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል፡፡›› ማርያም አመነች መልአኩ ያለውንም ተቀበለች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-22-06.jpg)
መልአኩ ለማርያም ከተናገረ በኋላ ወዲያወኑ፣ ሄደችና ኤልሳቤጥን ጐበኘቻት፡፡ ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ እንደ ሰማች፣ የኤልሳቤጥ ልጅ በሆዷ ውስጥ ዘለለ፡፡ ሴቶቹ እግዚአብሔር ስላደረገላቸው ነገር አብረው ሐሤት አደረጉ፡፡ ማርያም ኤልሳቤጥን ለሦስት ወራት ከጐበኘቻት በኋላ፣ ማርያም ወደ ቤትዋ ተመለሰች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-22-07.jpg)
ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅዋን ከወለደች በኋላ፣ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ መልአኩ እንዳዘዘው ሕፃኑን ዮሐንስ ብለው ሰየሙት፡፡ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ለዘካርያስ እንደ ገና እንዲናገር ፈቀደለት፡፡ ዘካርያስ እንዲህ አለ፣ ‹‹ሕዝቡን ዐስቦአልና እግዚአብሔር ይመስገን! አንተም ልጄ፣ ለኃጢአታቸው ይቅርታ መቀበል እንዴት እንደሚችሉ ለሕዝቡ የምትናገር የልዑል እግዚአብሔር ነቢይ ትባላለህ!
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሉቃስ 1፡፡_

44
content/23.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,44 @@
# 23. የኢየሱስ ልደት #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-01.jpg)
ማርያም ዮሴፍ ለተባለ ጻድቅ ሰው ታጭታ ነበር፡፡ እጮኛዋ ዮሴፍ ማርያም መፀነስዋን በሰማ ጊዜ፣ ሕፃኑ የእርሱ እንዳልሆነ ዐወቀ፡፡ ማርያምን ለማሳፈር አልፈለገም፣ ስለዚህ ዝም ብሎ ሊፈታት ዐሰበ፡፡ ያንን ከማድረጉ በፊት መልአክ መጣና በሕልም ተናገረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-02.jpg)
መልአኩ እንዲህ አለ፡- ‹‹ዮሴፍ፣ ማርያምን ሚስት አድርገህ ለመውሰድ አትፍራ፡፡ በውስጥዋ ያለው ሕፃን ከመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፡፡ ስሙን ኢየሱስ ብለህ ጥራው (ትርጕሙም፣ ‹ያሕዌ ያድናል› ማለት ነው)፣ ምክንያቱም ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-03.jpg)
ስለዚህ ዮሴፍ ማርያምን አገባትና ሚስቱ አድርጎ ወደ ቤቱ ወሰዳት፣ ነገር ግን እስክትወልድ ድረስ ከእርስዋ ጋር አልተኛም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-04.jpg)
ማርያም የምትወልድበት ጊዜ እንደ ደረሰ፣ የሮማ መንግሥት ሁሉም ሰው ለቈጠራ ቅድማያቶቹ ወደ ኖሩበት ከተማ እንዲሄድ ተናገረ፡፡ ዮሴፍና ማርያም ከሚኖሩበት ከናዝሬት ወደ ቤተ ልሔም ረጅም ጕዞ ተጓዙ ምክንያቱም በቤተ ልሔም ከተማ የተወለደው ቅድማያታቸው ዳዊት ነበረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-05.jpg)
ወደ ቤተ ልሔም በደረሱ ጊዜ ማረፊያ ስፍራ አልነበረም፡፡ ሊያገኙ የቻሉት ብቸኛ ክፍል እንስሶች የሚያድሩበት ስፍራ ነበረ፡፡ ሕፃኑ በተወለደ ጊዜ የሚያስተኙበት አልጋ ስላልነበረ እናቱ በከብቶች መመገቢያ ገንዳ አስተኛችው፡፡ ስሙንም ኢየሱስ አሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-06.jpg)
በዚያ ሌሊት በአቅራቢያው ባለ ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን የሚጠብቁ ጥቂት እረኞች ነበሩ፡፡ በድንገት የሚያበራ መልአክ ታያቸው፣ እነርሱም ፈሩ፡፡ መልአኩ፣ ‹‹አትፍሩ፣ ምክንያቱም ለእናንተ የምሥራች አለኝ፡፡ መሲሑ፣ ጌታ በቤተልሔም ተወልዶአል! አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-07.jpg)
‹‹ሄዳችሁ ሕፃኑን ፈልጉ፣ በጨርቅ ተጠቅልሎና በእንስሶች መመገቢያ ገንዳ ተኝቶ ታገኙታላችሁ፡፡›› ድንገትም ሰማያት በመላእክት ተሞሉ፣ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ ‹‹ክብር ለእግዚአብሔር በሰማይ ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ! አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-08.jpg)
እረኞች ኢየሱስ ወደ ነበረበት ስፍራ ፈጥነው ደረሱና ልክ መልአኩ እንደ ነገራቸው በእንስሶች መመገቢያ ገንዳ ተኝቶ አገኙት፡፡ በጣም ደስ አላቸው፡፡ ማርያምም ደግሞ በጣም ደስ አላት፡፡ እረኞቹ ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣ በጎቻቸው ወደ ነበሩባቸው ሜዳዎች ተመለሱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-09.jpg)
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከሩቅ ምሥራቅ አገሮች የሆኑ ጠቢባን በሰማይ አንድ ያልተለመደ ኮከብ ዐዩ፡፡ ዐዲስ የአይሁድ ንጉሥ የተወለደ መሆኑን እንደሚያመለክት ተገነዘቡ፡፡ ስለዚህ ይህንን ንጉሥ ለማየት በጣም ረጅም ርቀት ተጓዙ፡፡ ወደ ቤተ ልሔም መጡና ኢየሱስና ወላጆቹ የነበሩበትን ቤት አገኙት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-23-10.jpg)
ጠቢባኑ ኢየሱስን ከእናቱ ጋር ባዩት ጊዜ ወድቀው ሰገዱለት፡፡ ለኢየሱስ ውድ ስጦታዎች ሰጡት፡፡ ከዚያም ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 1፤ ሉቃስ 2፡፡_

40
content/24.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,40 @@
# 24. ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-01.jpg)
የዘካርያስና የኤልሳቤጥ ልጅ ዮሐንስ አደገና ነቢይ ሆነ፡፡ በምድረ በዳ ኖረ፣ የበረሐ ማርና አንበጣ ተመገበ፣ ከግመል ፀጉር የተሠራ ልብስም ለበሰ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-02.jpg)
ብዙ ሕዝብ ዮሐንስን ለመስማት ወደ ምድረ በዳ መጡ፡፡ እርሱም፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ›› በማለት ሰበከላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-03.jpg)
ሕዝቡ የዮሐንስን መልእክት በሰሙ ጊዜ፣ አብዛኞቻቸው ኃጢአታቸውን ተናዘዙ፣ ዮሐንስም አጠመቃቸው፡፡ ብዙ የሃይማኖት መሪዎች ደግሞ በዮሐንስ ሊጠመቁ መጡ፣ ነገር ግን ንስሐ አልገቡም ወይም ኃጢአታቸውን አልተናዘዙም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-04.jpg)
ዮሐንስ ለሃይማኖት መሪዎቹ እንዲህ አላቸው፣ ‹‹እናንተ መርዛማ እባቦች! ንስሐ ግቡና ድርጊታችሁን ለውጡ፡፡ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጥና ወደ እሳት ይጣላል፡፡›› ዮሐንስ ነቢያት ‹‹እነሆ፣ መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡›› በማለት የተናገሩትን ፈጽመ።
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-05.jpg)
አንዳንድ አይሁዶች መሲሕ ስለ መሆኑ ዮሐንስን ጠየቁት፡፡ ዮሐንስ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ ‹‹እኔ መሲሑ አይደለሁም፣ ነገር ግን ከእኔ በኋላ የሚመጣ አንድ ሰው አለ፡፡ የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ እንኳ የማይገባኝ በጣም ታላቅ ነው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-06.jpg)
በቀጣዩ ቀን፣ ኢየሱስ በዮሐንስ ለመጠመቅ መጣ፡፡ ዮሐንስ ባየው ጊዜ፣ ‹‹ተመልከቱ! እነሆ፣ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-07.jpg)
ዮሐንስ ኢየሱስን፣ ‹‹እኔ አንተን ለማጥመቅ ተገቢ ሰው አይደለሁም፡፡ በዚህ ፈንታ አንተ እኔን ማጥመቅ አለብህ እንጂ›› አለው፡፡ ኢየሱስ ግን፣ ‹‹መደረግ ያለበት ትክክለኛ ነገር ነውና አንተ እኔን ማጥመቅ ይገባሃል›› አለ፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ከቶ ኃጢአት ባይሠራም እንኳ ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-08.jpg)
ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ከውኃው እንደ ወጣ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ አምሳል ታየና ወርዶ በእርሱ ላይ ዐረፈ፡፡ በዚሁ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ ከሰማይ፣ ‹‹አንተ እኔ የምወድህ ልጄ ነህ፣ በአንተም በጣም ደስ ብሎኛል›› ብሎ ተናገረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-24-09.jpg)
እግዚአብሔር ለዮሐንስ፣ ‹‹መንፈስ ቅዱስ ይወርድና አንተ በምታጠምቀው ሰው ላይ ያርፋል፡፡ ሰውዬው የእግዚአብሔር ልጅ ነው›› ብሎ ተናግሮት ነበር፡፡ አንድ አምላክ ብቻ አለ፡፡ ነገር ግን ዮሐንስ ኢየሱስን ባጠመቀው ጊዜ፣ እግዚአብሔር አብ ሲናገር ሰማ፣ እግዚአብሔር ወልድን ዐየ፣ እርሱም ኢየሱስ ነው፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን ዐየ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 3፤ ማርቆስ 1፡9-11፤ ሉቃስ 3፡1-23፡፡_

36
content/25.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,36 @@
# 25. ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-01.jpg)
ኢየሱስ ከተጠመቀበኋላ ወዲያውኑ፣ መንፈስቅዱስ ወደምድረ በዳ ወሰደው፣ እዚያምአርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡ ከዚያም ሰይጣን ወደ ኢየሱስመጣና ኃጢአት እንዲሠራ ኢየሱስን ፈተነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-02.jpg)
‹‹የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንክ፣ መብላት ትችል ዘንድ እነዚህን ድንጋዮች ወደእንጀራ ለውጥ›› በማለት ሰይጣን ኢየሱስን ፈተነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-03.jpg)
ኢየሱስ፣ ‹‹‹ሰዎች ለመኖር እንጀራ ብቻ አያስፈልጋቸውም፣ነገር ግን እግዚአብሔር የሚናገረው እያንዳንዱ ቃል ያስፈልጋቸዋል›ተብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተጽፎአል! ብሎ መለሰለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-04.jpg)
ከዚያም ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደስ ጫፍ ወሰደውና፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ወደ ታች ወርውር፣ ምክንያቱም፣ ‹ድንጋይ እግርህን እንዳይመታህ ይሸከሙህዘንድ እግዚአብሔር መላእክቱንያዛል ተብሎ ተጽፎል››› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-05.jpg)
ነገር ግን ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ቃል በመጥቀስ ለሰይጣን መለሰለት፡፡ ‹‹በእግዚአብሔር ቃል፣ ‹ጌታ አምላክህን አትፈታተነው› በማለት ሕዝቡን ያዛል አለ፡፡›››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-06.jpg)
ከዚያም ሰይጣን የዓለምን መንግሥታትና ክብራቸውን ሁሉ ዐሳየውና፣ ‹‹ወድቀህ ብትሰግድልኝይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-07.jpg)
ኢየሱስ፣ ‹‹ሂድ፣ አንተ ሰይጣን! በእግዚአብሔር ቃልሕዝቡን፣ ‹ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻአምልክ› ብሎአዞአል›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-25-08.jpg)
ኢየሱስ ለሰይጣንፈተና አልተሸነፈም፣ ስለዚህ ሰይጣን ተወው፡፡ ከዚያ በኋላ መላእክት መጥተው ኢየሱስን አገለገሉት፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 4፡1-11፤ ማርቆስ 1፡12-13፤ ሉቃስ 4፡1-13፡፡_

44
content/26.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,44 @@
# 26. ኢየሱስ አገልግሎቱን ጀመረ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-01.jpg)
ኢየሱስ የሰይጣንን ፈተና ካሸፈነ በኋላ፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይኖርበት ወደ ነበረው ወደገሊላ አውራጃ ተመለሰ፡፡ ኢየሱስ ከቦታ ወደ ቦታ እየሄደ አስተማረ፡፡ሁሉም ሰው ስለ እርሱ መልካም ይናገሩ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-02.jpg)
ኢየሱስ በልጅነቱ ወደ ኖረበት ወደ ናዝሬትከተማ ተመለሰ፡፡ በሰንበት ወደ አምልኮ ቦታ ሄደ፡፡ያነብ ዘንድ የነቢዩን የኢሳይያስን ጥቅልልጽሑፍ ሰጡት፡፡ ኢየሱስ ጥቅልል ጽሑፉን ከፍቶ በከፊል ለሕዝቡ አነበበላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-03.jpg)
ኢየሱስ፣ ‹‹ለድሆች የምሥራችን፣ ለተማረኩት ነጻትን፣ ለዕውሮች ማየትን፣ ለታሰሩትም መፈታትን እሰብክዘንድ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰጥቶኛል፡፡ይህች የተወደደችውየጌታ ዓመት ነች›› ብሎ አነበበ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-04.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ ተቀመጠ፡፡ ሁላቸውም በቅርበት ተመለከቱት፡፡ ልክ አሁን ያነበበው የእግዚአብሔር ቃል ምንባብ መሲሑን ያመለክት ነበር፡፡ ኢየሱስ፣‹‹ይህ ያነበብኩላችሁ ቃል ልክአሁን እየተፈጸመ ነው›› አለ፡፡ሕዝቡ ሁሉ ተደነቁ፡፡ ‹‹ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-05.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ፣‹‹ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር እውነትነው፣ በነቢዩ ኤልያስ ዘመን፣ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፡፡ነገር ግን ለሦስትዓመት ተኩል ዝናብ ባልዘነበ ጊዜ እግዚአብሔር ኤልያስን በተለየአገር እንጂ በእስራኤልያለች መበለትን እንዲረዳ አልላከውም፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-06.jpg)
ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መናገሩን ቀጠለ፣ ‹‹በነቢዩ ኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል የቆዳ ሕመም የያዛቸው ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ኤልሳዕ አንዳቸውንም አልፈወሰም፡፡ የእስራኤል ጠላቶች አዛዥ የነበረውን የንዕማንን ቆዳ በሽታ ብቻ ፈወሰ፡፡›› ኢየሱስን ይሰሙ የነበሩት ሕዝብ አይሁዳውያን ነበሩ፡፡ ስለዚህ ይህን ሲናገር በሰሙት ጊዜ ተናደዱበት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-07.jpg)
የናዝሬት ሕዝብ ኢየሱስን ከአምልኮው ቦታ ጐተቱትና ወርውረው ሊገድሉት ወደ ተራራውአፋፍ ወሰዱት፡፡ነገር ግን ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል ተራመደና ወደ ናዝሬትከተማ ሄደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-08.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ በገሊላ አውራጃ ሁሉ ተዘዋወረ፣ ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ፡፡ ማየት፣ መራመድ፣ መስማት፣ ወይም መናገር የማይችሉትን ጨምሮ ብዙ የታመሙ ወይም የአካል ጕዳተኞች የሆኑ ሰዎችን አመጡ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-09.jpg)
አጋንንት የነበሩባቸው ብዙ ሰዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፡፡ በኢየሱስ ትእዛዝ አጋንንቱ ከሰዎቹ ወጡ፣ ብዙ ጊዜም፣ ‹‹አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ! ብለው ጮኹ፡፡ ሕዝቡ ተደነቁና እግዚአብሔርን አመለኩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-26-10.jpg)
ከዚያም ኢየሱስደቀ መዛሙርቱ ተብለው የተጠሩትን ዐሥራ ሁለት ሰዎች መረጠ፡፡ ሐዋርያቱ ከኢየሱስ ጋር ተጓዙና ከእርሱ ተማሩ፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 4፡12-25፤ ማርቆስ 1፡14-15፣ 35-39፤ 3፡13-21፤ ሉቃስ 4፡14-30፣ 38-44፡፡_

48
content/27.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,48 @@
# 27.የደጉ ሳምራዊ ታሪክ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-01.jpg)
አንድ ቀን አንድ የአይሁድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈትነው ወደ ኢየሱስ መጣ፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? አለው፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹በእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈው ምንድን ነው? ብሎ መለሰለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-02.jpg)
ሕግ ዐዋቂው የእግዚአብሔርሕግ፣ ‹‹ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም ዐሳብህም ውደድ፡፡ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ›› ይላል ብሎ መለሰ፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ትክክል ነህ! ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-03.jpg)
ነገር ግን ሕግ ዐዋቂው ጻድቅ መሆኑን ለማረጋገጥ ፈለገ፣ ስለዚህ፣ ‹‹ባልንጀራዬ ማን ነው? ብሎ ጠየቀ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-04.jpg)
ኢየሱስ ታሪክ በመናገር ለሕግ ዐዋቂው መለሰለት፡፡ ‹‹ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይጓዝ የነበረ አንድ አይሁዳዊ ነበረ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-05.jpg)
‹‹ሰውዬው በመጓዝ ላይ እያለ ወንበዴዎች ያዙት፡፡ የነበረውን ነገር ሁሉ ወሰዱበትና እስኪሞት ድረስ ደበደቡት፡፡ ከዚያም ሄዱ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-06.jpg)
ከዚያ በኋላ ወዲያውኑ አንድ አይሁዳዊ ካህን በዚያ መንገድ ይጓዝ ነበር፡፡ ይህ የሃይማኖት መሪ የተዘረፈውንና የተደበደበውን ሰው ባየ ጊዜ ወደ መንገዱ ሌላኛ ጎን ሄደ፣ ርዳታ የፈለገውን ሰው ቸል አለውና ጕዞውን ቀጠለ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-07.jpg)
ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ፣አንድ ሌዋዊ መጣ፡፡( ሌዋውያን በቤተ መቅደስ ካህናቱን የሚረዱ የአይሁድ ነገድ ነበሩ፡፡) ሌዋዊውም ደግሞ ወደ መንገዱ ሌላኛ ጎን ተሻገረና የተዘረፈውንና የተደበደበውን ሰው በቸልታ አለፈው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-08.jpg)
በዚያ መንገድ የወረደው የሚቀጥለው ሰው ሳምራዊ ነበር፡፡(ሳምራውያን የሌሎች አገሮች ሰዎችን ያገቡ የአይሁድ ዝርያዎች ነበሩ፡፡ሳምራውያንና አይሁዳውያን እርስ በርስ ይጠላሉ ነበር፡፡) ነገር ግን ሳምራዊው አይሁዳዊውን ባየ ጊዜ በጣም አድርጎ ራራለት፡፡ ስለዚህ ተንከባከበውና ቊስሉን አሰረለት፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-09.jpg)
‹‹ከዚያ በኋላ ሳምራዊው ሰውዬውን አንሥቶ በራሱ አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደሪያ ወሰደው ተንከባከበውም፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-10.jpg)
‹‹በማግሥቱም ሳምራዊው ጕዞውን መቀጠል አስፈለገው፡፡ ለእንግዶች ማረፊያው ባለቤት ጥቂት ገንዘብ ሰጠውና፣ ‹‹ተንከባከበው፣ ከዚህ ሌላ ገንዘብ የምታወጣ ከሆነ በምመለስበት ጊዜ እከፍልሃለሁ አለው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-27-11.jpg)
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሕግ ዐዋቂውን፣ ‹‹ምን ታስባለህ? ለተዘረፈውና ለተደበደበው ሰው ባልንጀራው ከሦስቱ ሰዎች የትኛው ነበር? ብሎ ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ ‹‹ምሕረት ያደረገለት ነበር›› ብሎ መለሰለት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹አንተም ሄደህ እንደዚሁ አድርግ›› ብሎ ነገረው፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሉቃስ 10፡25-37፡፡_

44
content/28.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,44 @@
# 28. ባለ ጠጋው ወጣት #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-01.jpg)
አንድ ቀንአንድ ባለጠጋወጣት ወደ ኢየሱስ መጣና፣ ‹‹ቸር መምህር፣ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ስለ ምን ‹ቸር› ትለኛለህ? ቸርአንድ ብቻአለ፣ እርሱም እግዚአብሔር ነው፡፡ነገር ግንአንተ የዘላለም ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግህ ለእግዚአብሔር ሕግታዘዝ›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-02.jpg)
‹‹የትኞቹን ልታዘዝ? ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ ‹‹አትግደል፡፡ አታመንዝር፡፡ አትስረቅ፡፡ አትዋሽ፡፡ አባትህንና እናትህን አክብር፣ ባልጀራህንምእንደ ራስህ ውደድ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-03.jpg)
ነገር ግን ወጣቱ፣ ‹‹ከልጅነቴጀምሮ እነዚህንሕጎች ሁሉ ፈጽሜአለሁ፡፡ ለዘላለም ለመኖርሌላስ ምን ማድረግ ያስፈልገኛል? አለ፡፡ ኢየሱስ ዐየውና ወደደው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-04.jpg)
ኢየሱስ፣ ‹‹ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ያለህን ንብረት ሁሉሽጥና ገንዘቡን ለድሆች ስጥ፣ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፡፡ ከዚያም በኋላ ናና ተከተለኝ›› ብሎመለሰለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-05.jpg)
ወጣቱ፣ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ በጣም ባለ ጠጋ ነበርና ያለውን ነገር ሁሉ መስጠት ስላልፈለገ በጣም ዐዘነ፡፡ ከኢየሱስ ፊቱን አዞረና ሄደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-06.jpg)
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፣ ‹‹ለባለ ጠጎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እጅግ አስቸጋሪ ነው! አዎ፣ ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-07.jpg)
ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ ደነገጡና፣ ‹‹ታዲያ ማን ሊድን ይችላል? አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-08.jpg)
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ተመለከተና፣ ‹‹ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-09.jpg)
ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ ‹‹እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፡፡ ዋጋችን ምን ይሆን? አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-28-10.jpg)
ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ ‹‹ስለ እኔ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን ወይም ንብረትን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል፡፡ ነገር ግን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች፣ ኋለኞችም የሆኑ ብዙዎች ፊተኞች ይሆናሉ፡፡››
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 19፡16-30፤ ማርቆስ 10፡17-31፤ ሉቃስ 18፡18-30፡፡_

40
content/29.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,40 @@
# 29. የምሕረት የለሹ ባሪያ ታሪክ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-01.jpg)
አንድ ቀን ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን? ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ሰባት ጊዜ አይደለም፣ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ›› አለው፡፡ ኢየሱስ ይህን ሲል ሁልጊዜ ይቅር ማለት አለብን ማለቱ ነው፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ይህን ታሪክ ተናገረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-02.jpg)
ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንግሥት ባሮቹን ሊቈጣጠር የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች፡፡ ከባሮቹ አንዱ የ10,000 መክሊት የሚያክል ከፍተኛ ዕዳ ነበረበት፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-03.jpg)
ባሪያው ዕዳን መክፈል ስላልቻለ፣ ንጉሡ፣ ‹‹ዕዳውን ይከፍል ዘንድ ይህን ሰውና ቤተ ሰቡን ሽጡአቸው›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-04.jpg)
‹‹ባሪያው በንጉሡ ፊት በጉልበቱ ወደቀና፣ ‹እባክህን ታገሠኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ› አለው፡፡ ንጉሡ ለባሪያው አዘነለት፣ ዕዳውንም ሁሉ ሰረዘለትና እንዲሄድ ለቀቀው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-05.jpg)
‹‹ነገር ግን ባሪያው ከንጉሡ ዘንድ በወጣ ጊዜ፣ የአራት ወር ደመወዝ የሚሆን ዕዳ ያለበትን ባልንጀሮቹ ከሆኑት ባሪያዎች አንዱን አገኘ፡፡ ባሪያው ባልንጀራው የሆነውን ባሪያ ያዘውና፣ ‹ዕዳህን ክፈለኝ! አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-06.jpg)
‹‹ባልንጀራው ባሪያ በጉልበቱ ወድቆ፣ ‹እባክህን ታገሠኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ› አለው፡፡ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ያ ባሪያ ባልንጀራ ባሪያውን ዕዳውን እስኪከፍለው ድረስ በወኅኒ ጣለው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-07.jpg)
‹‹ሌሎች ባሮችም የሆነውን ነገር ዐይተው እጅግ ተረበሹ፡፡ ወደ ንጉሡ ሄደውም የሆነውን ነገር ሁሉ ነገሩት፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-08.jpg)
‹‹ንጉሡ ባሪያውን ጠራና፣ ‹አንተ ክፉ ባሪያ! ስለ ለመንኸኝ ዕዳህን ተውሁልህ፡፡ አንተም ይህንኑ ማድረግ ይገባህ ነበር› አለው፡፡ ንጉሡ በጣም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ክፉውን ባሪያ በወኅኒ ጣለው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-29-09.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ ‹‹ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ይቅር ካላለ፣ እንዲሁ ደግሞ የሰማይ አባቴ ያደርግባችኋል፡፡››
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 18፡21-35፡፡_

40
content/30.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,40 @@
# 30. ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን መገበ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-01.jpg)
ኢየሱስ በተለያዩ ብዙ መንደሮች እንዲሰብኩና ሰዎችን እንዲያስተምሩ ሐዋርያቱን ላከ፡፡ እነርሱ ኢየሱስ ወደ ነበረበት በተመለሱጊዜ፣ ያደረጉትንነገር ነገሩት፡፡ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ሐይቁን ተሻግረውጸጥታ ወዳለበት ቦታ አብረውት እንዲሄዱናጥቂት እንዲያርፉ ጋበዛቸው፡፡ ስለዚህጀልባ ውስጥ ገቡና ሐይቁን ተሻገሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-02.jpg)
ነገር ግን በጀልባውሲሄዱ ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን ያዩአቸው ብዙሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህሰዎች ሊቀድሙአቸው በባሕሩዳርቻ ሮጡ፡፡ ስለዚህ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ በደረሱጊዜ፣ በጣም ብዙሰዎች አስቀድመውበዚያ ተገኝተው ይጠባበቁአቸው ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-03.jpg)
ሕዝቡ ሴቶችና ልጆች ሳይቈጠሩ ከ5000 በላይ ወንዶች ነበሩ፡፡ ኢየሱስ ለሕዝቡ እጅግ አዘነላቸው፡፡ ለኢየሱስ እነዚህ ሕዝብ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ነበሩ፡፡ ስለዚህ አስተማራቸውና በመካከላቸው የነበሩትን በሽተኞች ፈወሳቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-04.jpg)
በዚያ ምሽት ደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብለው ነገሩት፣ ‹‹ጊዜው መሽቶአልና በአቅራቢያው ከተሞች የሉም፡፡ የሚበሉትን ነገር ይገዙ ዘንድ ሕዝቡን አሰናብታቸው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-05.jpg)
ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹የሚበሉትን እናንተ ስጡአቸው! አላቸው፡፡ እነርሱም፣‹‹ይህን ማድረግ እንዴት እንችላለን? ያለን አምስት እንጀራናሁለት ዓሣ ብቻ ነው››ብለው መለሱለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-06.jpg)
ሃምሳ ሃምሳ ሆነው ሣሩ ላይ እንዲቀመጡ ለሕዝቡ ይነግሩ ዘንድ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-07.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ ተመለከተ፣ ስለ ምግቡም እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-08.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ እንጀራውንና ዓሣውን ቈረሰ፡፡ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ምግቡን ማደላቸውን ቀጠሉ፣ ከቶም አላለቀም! ሕዝቡ ሁሉ በልተው ጠገቡ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-30-09.jpg)
ከዚያ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ቊርስራሹን ምግብ ሰበሰቡ፣ እርሱም ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ነበር! ምግቡ ሁሉ የመጣው ከአምስቱ እንጀራና ከሁለቱ ዓሣ ነበር፡፡
_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 14፡13-21፤ ማርቆስ 6፡31-44፤ ሉቃስ 9፡10-17፤ ዮሐንስ 6፡5-15፡፡_

36
content/31.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,36 @@
# 31. ኢየሱስ በውሃ ላይ ተራመደ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-01.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ ጀልባ ውስጥ ገብተው እየቀዘፉ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው፡፡ ኢየሱስ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፡፡ በዚያ ኢየሱስ ብቻውን ነበር፣ እስከ እኩለ ሌሊትም ጸለየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-02.jpg)
በዚሁ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ጀልባቸውን እየቀዘፉ ነበር፣ በእኩለ ሌሊት የደረሱት ወደ ሐይቁ አጋማሽ ብቻ ነበር፡፡ ነፋሱ በእነርሱ ላይ በኃይል ይነፍስ ስለ ነበር የሚቀዝፉት በጣም በችግር ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-03.jpg)
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መጸለዩን ጨረሰና ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄደ፡፡ በውሃው ላይ እየተራመደ ሐይቁን አቋርጦ ወደ ጀልባቸው ሄደ!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-04.jpg)
ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን ባዩ ጊዜ በጣም ፈሩ፣ ምክንያቱም ምትሐት ያዩ መሰላቸው፣ ኢየሱስ የፈሩ መሆናቸውን ዐወቀ፣ ስለዚህ ወደ እነርሱ ተጣራና፣ ‹‹አትፍሩ፡፡ እኔ ነኝ! አላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-05.jpg)
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ አንተስ ከሆንክ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዝ›› አለው፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ‹‹ና! አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-06.jpg)
ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጣና በውሃው ላይ ወደ ኢየሱስ መራመድ ጀመረ፡፡ ነገር ግን አጭር ርቀት ከተራመደ በኋላ ዓይኖቹን ከኢየሱስ አዞረና ማዕበሉን ያይ ብርቱው ነፋስም ይሰማው ጀመር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-07.jpg)
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ፈራና በውሃው መስጠም ጀመረ፡፡ ‹‹መምህር ሆይ፣ አድነኝ! ብሎ ጮኸ፡፡ ኢየሱስ ወዲያው እጆቹን ዘረጋና ያዘው፡፡ ከዚያም ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ተጠራጠርህ? አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-31-08.jpg)
ጴጥሮስና ኢየሱስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን ወዲያውኑ አቆመና ጸጥ አለ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ተደነቁ፡፡ ‹‹በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ›› በማለት ለኢየሱስ ሰገዱለት፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 14፡22-23፤ ማርቆስ 6፡45-52፤ ዮሐንስ 6፡16-21፡፡___

68
content/32.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,68 @@
# 32. ኢየሱስ ርኵስ መንፈስ የያዘውን ሰውና የታመመችውን ሴት ፈወሰ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-01.jpg)
አንድ ቀን ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሐይቁን አቋርጠው የጌርጌሴኖን ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ ሄዱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-02.jpg)
ወደ ሐይቁ ማዶ በደረሱ ጊዜ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ሮጦ ወደ ኢየሱስ መጣ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-03.jpg)
ይህ ሰው ማንም ሊቈጣጠረው የማይችል እጅግ ብርቱ ነበረ፡፡ ሰዎች እጆቹንና እግሮቹን እንኳ በሰንሰለት አስረውት ነበር፣ ነገር ግን ሰንሰለቱን ይበጣጥስ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-04.jpg)
ሰውዬው በአካባቢው ባሉ መቃብሮች መካከል ይኖር ነበር፡፡ ይህ ሰው ቀኑንና ሌሊቱን ሁሉ ይጮኽ ነበር፡፡ ልብስ አይለብስም ነበር፣ ሰውነቱንም በተደጋጋሚ በድንጋይ ይቧጭር ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-05.jpg)
ሰውዬው ወደ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ፣ በፊቱ በጉልበቱ ወድቆ ሰገደለት፡፡ ኢየሱስ ርኵስ መንፈሱን፣ ‹‹ከዚህ ሰው ውጣ! አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-06.jpg)
ርኵስ መንፈሱ ያለበት ሰው ከፍ ባለ ድምፅ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ? እባክህን አታሠቃየኝ! ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ርኵስ መንፈሱን፣ ‹‹ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ ‹‹ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው›› አለና መለሰ፡፡ (‹‹ሌጌዎን›› በሮማ ጦር ሠራዊት ብዙ ሺህ ወታደሮችን የያዘ ክፍል ነበር፡፡)
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-07.jpg)
ርኵሳን መናፍስቱ፣ ‹‹እባክህን ከዚህ አካባቢ አታርቀን! ብለው ለመኑት፡፡ በአቅራቢያው ባለ ኮረብታ ላይ የእሪያ መንጋ ተሰማርቶ ነበር፡፡ ስለዚህ ርኵሳን መናፍስቱ ኢየሱስን፣ ‹‹እባክህን በዚህ ፈንታ ወደ እሪያዎቹ ስደደን! ብለው ለመኑት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ሂዱ! አላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-08.jpg)
ርኵሳን መናፍስቱ ከሰውዬው ወጡና ወደ እሪያዎቹ ገቡ፡፡ እሪያዎቹ ከአፋፉ ቊልቊል ሮጡና በሐይቁ ሰጠሙ፡፡ በመንጋው 2,000 ያህል እሪያዎች ነበሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-09.jpg)
እሪያዎቹን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ ወደ ከተማ ሮጡና ኢየሱስ ያደረገውን ነገር ላገኙት ሰው ሁሉ ተናገሩ፡፡ የከተማው ሰዎች መጡና ርኵሳን መናፍስት የነበሩበትን ሰው ዐዩ፡፡ ልብሱን ለብሶ እንደ ጤናማ ሰው ሆኖ በጸጥታ ተቀምጦ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-10.jpg)
ሰዎቹ በጣም ፈርተው ነበርና ኢየሱስን እንዲሄድ ጠየቁት፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ጀልባ ውስጥ ገባና ለመሄድ ተዘጋጀ፡፡ ርኵን መናፍስት የነበሩበት ሰው ከኢየሱስ ጋር ለመሄድ ልመና አቀረበ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-11.jpg)
ነገር ግን ኢየሱስ፣ ‹‹አይደለም፣ ወደ ቤትህ ሄደህ እግዚአብሔር ስላደረገልህ ነገር ሁሉና እንዴት እንደ ማረህ ለወዳጆችህና ለቤተ ሰብህ እንድትነግር እፈልጋለሁ›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-12.jpg)
ስለዚህ ሰውዬው ሄደና ኢየሱስ ስላደረገለት ነገር ለሁሉም ሰው ተናገረ፡፡ ታሪኩን የሰማ ሰው ሁሉ በአድናቆትና በአግራሞት ተሞላ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-13.jpg)
ኢየሱስ ወደ ሐይቁ ማዶ ተመለሰ፡፡ እዚያ በደረሰ ጊዜ ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰበሰቡና አጨናነቁት፡፡ በሕዝቡ መካከል ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት ነበረች፡፡ እንዲፈውሱአት ገንዘብዋን ሁሉ ለሐኪሞች ከፍላ ነበር፣ ነገር ግን ባሰባት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-14.jpg)
ኢየሱስ ብዙ በሽተኞችን እንደ ፈወሰ ሰምታ ነበርና፣ ‹‹የኢየሱስን ልብስ ብቻ ብዳስስ ያኔ እኔም እንደምፈወስ እርግጠኛ ነኝ! ብላ ዐሰበች፡፡ ስለዚህ ከኢየሱስ ኋላ መጣችና ልብሱን ዳሰሰች፡፡ ልብሱን እንደ ዳሰሰች ወዲያውኑ ደምዋ ቆመ!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-15.jpg)
ወዲያውኑ፣ ኢየሱስ ኃይል ከእርሱ እንደ ወጣ ዐወቀ፡፡ ስለዚህ ወደ ኋላ ዞረና፣ ‹‹ማን ነው የዳሰሰኝ? ብሎ ጠየቀ፡፡ ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹በዙሪያህ የተሰበሰቡና የሚያጋፉህ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ‹ስለ ምን ማን ዳሰሰኝ› ብለህ ትጠይቃለህ? ብለው መለሱለት።
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-32-16.jpg)
ሴቲቱ እየተንቀጠቀጠችና በጣም እየፈራች በኢየሱስ ፊት ተደፋች፡፡ ከዚያም ያደረገችውን፣ እንዲሁም የተፈወሰች መሆንዋን ነገረችው፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹እምነትሽ አድኖሻል፡፡ በሰላም ሂጂ›› አላት፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 8፡28-34፤ 9፡20-22፤ ማርቆስ 5፡1-20፤ 5፡24-34፤ ሉቃስ 8፡26-39፤ 8፡42-48፡፡___

40
content/33.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,40 @@
# 33. የአርሶ አደሩ ታሪክ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-01.jpg)
አንድ ቀን ኢየሱስ በሐይቁ ዳርቻ አጠገብ በጣም ብዙ ሕዝብ እያስተማረ ነበር፡፡ ኢየሱስ ሊናገራቸው በቂ ቦታ ለማግኘት በውሃው ዳርቻ በጀልባ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ በጣም ብዙ ሰዎች ሊሰሙት መጡ፡፡ በጀልባው ተቀመጠና ሕዝቡን አስተማረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-02.jpg)
ኢየሱስ ይህንን ታሪክ ተናገረ፡፡ ‹‹አንድ አርሶ አደር ዘር ሊዘራ ወጣ፡፡ በእጁ ዘሩን ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፣ ወፎችም መጥተው ያን ዘር በሙሉ በሉት፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-03.jpg)
‹‹ሌላው ዘር ብዙ መሬት በሌለበት በአለታማ መሬት ላይ ወደቀ፣ ነገር ግን ሥሩ ወደ መሬት መጥለቅ አልቻለም፡፡ ፀሐይዋ በወጣችና በሞቀች ጊዜ፣ ቡቃያው ጠወለገና ደረቀ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-04.jpg)
‹‹አሁንም ሌላው ዘር በእሾኽ መካከል ወደቀ፡፡ ይህ ዘር መብቀል ጀመረ፣ ነገር ግን እሾኹ አነቀው፡፡ ስለዚህ በእሾኻማው መሬት ላይ የበቀለው ቡቃያ ምንም ፍሬ አላፈራም፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-05.jpg)
‹‹ሌላው ዘር በመልካም መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ይህ ዘር በቀለና አንዱ 30፣ አንዱ 60፣ አንዱም መቶ ፍሬ ሰጠ፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-06.jpg)
ይህ ታሪክ ደቀ መዛሙርቱን ግራ አጋባቸው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ አብራራላቸው፣ ‹‹ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ የመንገዱ ዳር የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ሰው ነው፣ ነገር ግን አያስተውለውም፣ ዲያብሎስም ቃሉን ይወስድበታል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-07.jpg)
‹‹በአለታማ መሬት የተዘራው ዘር የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ በደስታ የሚቀበለው ሰው ነው፡፡ ነገር ግን መከራ ወይም ስደት በሚያጋጥመው ጊዜ እምነቱን ይተዋል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-08.jpg)
‹‹እሾኻማው መሬት የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ ሰው ነው፣ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ የዚህ ዓለም ዐሳብ፣ ባለጠግነትና ደስታ ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር ያንቃል፡፡ ከዚህ የተነሣ፣ የሰማው ትምህርት ፍሬ አያፈራም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-33-09.jpg)
‹‹መልካሙ መሬት ግን የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፣ የሚያምነውና ፍሬ የሚያፈራ ሰው ነው፡፡››
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 13፡1-8፣ 18-23፤ ማርቆስ 4፡1-8፣ 13-20፤ ሉቃስ 8፡4-15፡፡___

44
content/34.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,44 @@
# 34.ኢየሱስ ሌሎች ታሪኮችን አስተማረ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-01.jpg)
ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ሌሎች ብዙ ታሪኮችን አስተማረ፡፡ ለምሳሌ፣ እንዲህ አለ፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንግሥት ሰው በማሳው የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች፡፡ እርስዋም ከሁሉ ዘር የምታንስ ነች፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-02.jpg)
‹‹ነገር ግን የሰናፍጭ ዘር ባደገች ጊዜ አዕዋፍ መጥተው እስኪሰፍሩ ድረስ በአትክልት ቦታ ካሉ ተክሎች ሁሉ ትበልጣለች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-03.jpg)
ኢየሱስ ሌላ ታሪክ ተናገረ፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንግሥት ሴት ወስዳ ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ከዱቄት ጋር የለወሰችው እርሾ ትመስላለች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-04.jpg)
‹‹ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ሰው በእርሻ ውስጥ የሸሸገው መዝገብ ትመስላለች፡፡ ሌላ ሰው መዝገቡን አገኘውና እንደ ገና ቀበረው፡፡ በጣም በደስታ ተሞልቶ ነበርና ሄዶ ያለውን ነገር ሁሉ ሸጠና በገንዘቡ እርሻውን ገዛው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-05.jpg)
‹‹ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ዋጋዋ እጅግ ውድ የሆነ ዕንቊ ትመስላለች፡፡ የዕንቊ ነጋዴ ባገኛት ጊዜ ያለውን ነገር ሁሉ ሸጠና ገዛት፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-06.jpg)
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በራሳቸው መልካም ሥራ ለሚታመኑና ሌሎችን ለሚንቁ አንዳንድ ሰዎች ታሪክ ተናገረ፡፡ ‹‹ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፡፡ አንዱ ቀረጥ ሰብሳቢ ሲሆን፣ ሌላው የሃይማኖት መሪ ነበር›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-07.jpg)
‹‹የሃይማኖት መሪው እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ ‹እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፣ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፣ እንደዚህ ቀረጥ ሰብሳቢ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-08.jpg)
‹‹ለምሳሌ፣ እኔ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፣ ከማገኘውም ገንዘብና ንብረት ሁሉ ከዐሥር አንድ አወጣለሁ፡፡›››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-09.jpg)
‹‹ቀረጥ ሰብሳቢው ግን ከሃይማኖት መሪው ራቅ ብሎ ቆመ፣ ወደ ሰማይ እንኳ አልተመለከተም፡፡ በዚህ ፈንታ፣ ደረቱን በእጁ እየመታ፣ ‹እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ እባክህን ማረኝ፡፡›››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-34-10.jpg)
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ ‹‹እውነት እላችኋለሁ፣ እግዚአብሔር የቀረጥ ሰብሳቢውን ጸሎት ሰማና ጻድቅ ነህ አለው፡፡ የሃይማኖት መሪውን ጸሎት ግን አልወደደም፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ከፍ የሚያደርገውን ሁሉ ያዋርዳል፣ ራሱን የሚያዋርደውን ግን ከፍ ያደርጋል፡፡›
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 13፡31-33፣ 44-46፤ ማርቆስ 4፡30-32፤ ሉቃስ 13፡18-21፤ 18፡9-14፡፡___

56
content/35.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,56 @@
# 35. የርኅሩኁ አባት ታሪክ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-01.jpg)
አንድ ቀን ኢየሱስ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችንና ሊሰሙት የተሰበሰቡ ሌሎች ኃጢአተኞችን ያስተምር ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-02.jpg)
ደግሞም በዚያ የነበሩ አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስ ኃጢአተኞችን ወዳጆች አድርጎ ሲቀበላቸው ዐዩ፣ እርስ በርሳቸውም ይነቅፉት ጀመር፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ይህንን ታሪክ ነገራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-03.jpg)
ሁለት ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበር፡፡ ታናሹ ልጅ አባቱን፣ አባቴ ሆይ፣ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል አሁን ስጠኝ! አለው፡፡ ስለዚህ አባትዬው ገንዘቡን ለሁለቱ ልጆቹ አካፈላቸው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-04.jpg)
‹‹ታናሹ ልጅ ወዲያውኑ ያለውን ሁሉ ሰበሰበና ሩቅ አገር ሄዶ በኃጢአት እየኖረ ገንዘቡን አጠፋ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-05.jpg)
‹‹ከዚያ በኋላ ታናሹ ልጅ በነበረበት አገር ጽኑ ረሀብ ሆነ፣ ምግብ የሚገዛበት ገንዘብም አልነበረውም፡፡ ስለዚህ ብቸኛ የነበረውን፣ እሪያዎችን የመመገብ ሥራ ያዘ፡፡ በጣም ተጐሳቊሎና ተርቦ ስለ ነበር የእሪያዎችን ምግብ ለመብላት ይመኝ ነበር፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-06.jpg)
‹‹በመጨረሻ፣ ታናሹ ልጅ ለራሱ እንዲህ አለ፣ ‹ምን እያደረግሁ ነው? የአባቴ አገልጋዮች ሁሉ የሚበሉት ብዙ ምግብ አላቸው፣ እኔ ግን ተርቤአለሁ፡፡ ወደ አባቴ ተመልሾ እሄድና ከአገልጋዮቹ አንዱ እንዲያደርገኝ እለምነዋለሁ፡፡›››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-07.jpg)
ስለዚህ ታናሹ ልጅ ወደ አባቱ ቤት መመለስ ጀመረ፡፡ ገና በሩቅ እያለ አባቱ ዐየውና አዘነለት፡፡ ወደ ልጁ ሮጠና አቀፈው ሳመውም፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-08.jpg)
‹‹ልጁም አለ፣ ‹አባቴ ሆይ፣ እግዚአብሔርንና አንተን በድዬአለሁ፡፡ ልጅህ ልባል አይገባም፡፡›››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-09.jpg)
‹‹ነገር ግን አባቱ ከአገልጋዮቹ ለአንዱ እንዲህ ብሎ ነገረው፣ ‹ፈጥነህ ሂድና ማለፊያ ልብስ አምጥተህ ለልጄ አልብሰው! ለጣቱ ቀለበት ለእግሩም ጫማ አድርግለት፡፡ ከዚያም እንበላና ደስ ይለን ዘንድ የሰባ ፍሪዳ አምጥታችሁ እረዱ፣ ምክንያቱም ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፣ ሕያውም ሆኖአል! ጠፍቶ ነበር፣ አሁን ግን ተገኝቶአል!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-10.jpg)
‹‹ስለዚህ ሰዎቹ ደስ ይላቸው ጀመር፡፡ ብዙ ሳይቆይ፣ ይሠራበት ከነበረው እርሻ ታላቅ ወንድሙ ወደ ቤት መጣ፡፡ የሙዚቃና የዘፈን ድምፅ ሰማ፣ ምን እየሆነ ነው ብሎም ተገረመ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-11.jpg)
‹‹ታላቁ ልጅ ወንድሙ ስለ መጣ እየተደሰቱ መሆናቸውን ባወቀ ጊዜ፣ በጣም ስለ ተቈጣ ወደ ቤት ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ አባቱ ወጣና ገብቶ ከእነርሱ ጋር እንዲደሰት ለመነው፣ እርሱ ግን እምቢ አለ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-12.jpg)
ታላቁ ልጅ አባቱን እንዲህ አለው፣ ‹በእነዚህ ዓመታት ሁሉ በታማኝነት ለአንተ ሠርቼአለሁ! ከቶ ትእዛዝህን አልተላለፍኩም፣ እስካሁንም ከጓደኞቼ ጋር እንድደሰት አንድ ጥቦት ፍየል እንኳ አልሰጠኸኝም፡፡ ኃጢአት በመሥራት ገንዘብህን ያጠፋው ይህ ልጅህ ግን ወደ ቤት በመጣ ጊዜ፣ የሰባ ፍሪዳ አረድህለት!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-35-13.jpg)
‹‹አባቱ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ ‹ልጄ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፣ ያለኝም ነገር ሁሉ የአንተ ነው፡፡ መደሰታችን ግን ትክክል ነው፣ ምክንያቱም ወንድምህ ሞቶ ነበር፣ አሁን ግን ሕያው ሆኖአል፡፡ ጠፍቶ ነበር፣ አሁን ግን ተገኝቶአል!
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሉቃስ 15፡11-32፡፡___

32
content/36.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,32 @@
# 36. የኢየሱስ መልክ ተለወጠ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-36-01.jpg)
አንድ ቀን ኢየሱስ ሦስቱን ደቀ መዛሙርቱን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ያዞ ሊጸልዩ ወደ ረጅም ተራራ ወጡ። ( ዮሐንስ የተባለው ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ያጠመቀው ሰው አልነበረም፡፡)
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-36-02.jpg)
ኢየሱስ በመጸለይ ላይ እያለ፣ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፣ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፣ በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊያነጻው እስከማይችል ድረስ በጣም ነጭ ሆነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-36-03.jpg)
በዚያን ጊዜ ሙሴና ነቢዩ ኤልያስ ታዩ፡፡ እነዚህ ሰዎች በመቶዎች ከሚቈጠሩ ዓመታት በፊት በምድር ላይ ይኖሩ ነበር፡፡ በቅርቡ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ሞቱ ከኢየሱስ ጋር ተነጋገሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-36-04.jpg)
ሙሴና ኤልያስ ከኢየሱስ ጋር በመነጋገር ላይ እያሉ ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ ‹‹በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ እንዲሁም አንድ ለኤልያስ፣ ሦስት መጠለያዎችን እንሥራ›› አለው፡፡ ጴጥሮስ የሚናገረውን አያውቅም ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-36-05.jpg)
ጴጥሮስ እየተናገረ እያለ፣ ብሩህ ደመና መጥቶ ከበባቸውና ከደመናው ድምፅ፣ ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት›› አለ፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ፈሩና መሬት ላይ ወደቁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-36-06.jpg)
ያኔ ኢየሱስ ዳሰሳቸውና፣ ‹‹አትፍሩ፣ ተነሡ›› አላቸው፡፡ ዙሪያቸውን ሲያዩ ከኢየሱስ በቀር ማንም አልነበረም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-36-07.jpg)
ኢየሱስና ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ከተራራው ወረዱ፡፡ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ ‹‹በዚህ ስለ ሆነው ነገር ገና ለማንም አትናገሩ፡፡ እኔ በቶሎ እሞታለሁ፣ ሕያውም እሆናለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ለሰዎች መናገር ትችላላችሁ፡፡››
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 17፡1-9፤ ማርቆስ 9፡2-8፤ ሉቃስ 9፡28-36፡፡___

48
content/37.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,48 @@
# 37. ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሣ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-01.jpg)
አንድ ቀን ኢየሱስ አልዓዛር በጣም ታሞአል የሚል መልእክት ደረሰው፡፡ አልዓዛርና ሁለቱ እኅቶቹ ማርያምና ማርታ የኢየሱስ የቅርብ ወዳጆች ነበሩ፡፡ ኢየሱስ ይህንን ወሬ በሰማ ጊዜ፣ ‹‹ይህ ሕመም ለእግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም›› አለ፡፡ ኢየሱስ ወዳጆቹን ይወዳቸው ነበር፣ ነገር ግን ለሁለት ቀናት በነበረበት ስፍራ ቆየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-02.jpg)
ሁለቱ ቀናት ካለፉ በኋላ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹ወደ ይሁዳ እንሂድ›› አላቸው፡፡ ‹‹ነገር ግን መምህር ሆይ፣ ‹‹ልክ ከጥቂት ጊዜ በፊት በዚያ ያሉት ሕዝብ ሊገድሉህ ይፈልጉ ነበር! ብለው ደቀ መዛሙርቱ መለሱለት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቶአል፣ ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ›› አላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-03.jpg)
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ አልዓዛር ተኝቶስ ከሆነ፣ ይድናል›› ብለው መለሱለት፡፡ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በግልጽ ነገራቸው፣ ‹‹አልዓዛር ሞቶአል፡፡ እናንተ በእኔ ታምኑ ዘንድ እዚያ ባለመኖሬ ደስ ብሎኛል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-04.jpg)
ኢየሱስ አልዓዛር ወደ ተወለደበት ከተማ በደረሰ ጊዜ፣ አልዓዛር ከሞተ አራት ቀን ሆኖት ነበር፡፡ ማርታ ኢየሱስን ልትገናኘው ወጣችና እንዲህ አለች፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትኖር ኖሮ ወንድሜ አይሞትም ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እንደሚሰጥህ አምናለሁ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-05.jpg)
ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፣ ‹‹እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፡፡ በእኔ የሚያምን ሁሉ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡ በእኔ የሚያምን ሁሉ ከቶ አይሞትም፡፡ ይህን ታምኛለሽን? ማርታ፣ ‹‹አዎን፣ ጌታ ሆይ! አንተ መሲሑ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አምናለሁ›› ብላ መለሰችለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-06.jpg)
ከዚያም ማርያም መጣች፡፡ በኢየሱስ እግር ወደቀችና፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር›› አለች፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹አልዓዛርን ወዴት ነው ያኖራችሁት? ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ‹‹በመቃብር ነው፡፡ ናና እይ›› ብለው ነገሩት፡፡ ከዚያም ኢየሱስ አለቀሰ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-07.jpg)
መቃብሩ ዋሻ ነበር፣ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር፡፡ ኢየሱስ ወደ መቃብሩ በደረሰ ጊዜ ድንጋዩን አንከባሉት›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ነገር ግን ማርታ፣ ‹‹ከሞተ አራት ቀን ሆኖታል፡፡ አሁን ይሸታል›› አለችው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-08.jpg)
ኢየሱስ፣ ‹‹በእኔ ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርኩሽምን? አላት፡፡ ስለዚህ ድንጋዩን አንከባለሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-09.jpg)
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ወደ ላይ ተመለከተና፣ ‹‹አባት ሆይ፣ ስለምትሰማኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ ሁልጊዜ እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ፣ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ እዚህ ስለ ቆሙት ስለ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ይህን እላለሁ›› አለ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ፣ ‹‹አልዓዛር ሆይ፣ ወደ ውጭ ና! ብሎ ጮኸ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-10.jpg)
ስለዚህ አልዓዛር ወጣ! በከፈን እንደ ተገነዘ ነበር፡፡ ኢየሱስም፣ ‹‹ፍቱትና ይሂድ ተዉት! አላቸው፡፡ ከአይሁድ ብዙዎች በዚህ ተአምር ምክንያት በኢየሱስ አመኑ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-37-11.jpg)
ነገር ግን የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ቀኑ፣ ስለዚህ ኢየሱስንና አልዓዛርን እንዴት መግደል እንዳለባቸው ለማቀድ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዮሐንስ 11፡1-46፡፡___

64
content/38.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,64 @@
# 38. ኢየሱስ ተላልፎ ተሰጠ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-01.jpg)
አይሁድ በያመቱ የፋሲካን በዓል ያከብሩ ነበር፡፡ ይህም በዓል ከብዙ ምእት ዓመታት በፊት እግዚአብሔር ቅድማያቶቻቸውን በግብፅ ከነበረው ባርነት እንዴት እንዳዳናቸው የሚከበር ነበር፡፡ ኢየሱስ መጀመሪያ በይፋ መስበኩንና ማስተማሩን ከጀመረ ከሦስት ዓመት ገደማ በኋላ፣ ይህን ፋሲካ በኢየሩሳሌም ከእነርሱ ጋር ሊያከብር እንደ ፈለገ፣ በዚያም እንደሚገደል ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-02.jpg)
ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ ይሁዳ ተብሎ የሚጠራ ሰው ነበር፡፡ ይሁዳ የሐዋርያቱ የገንዘብ ከረጢት ኃላፊ ነበር፣ ነገር ግን ገንዘብ ይወድ ነበርና ብዙ ጊዜ ከከረጢቱ ውስጥ ገንዘብ ይሰርቅ ነበር፡፡ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ከደረሱ በኋላ፣ ይሁዳ ወደ አይሁድ መሪዎች ሄደና ኢየሱስን በገንዘብ አሳልፎ ሊሰጣቸው ተስማማ፡፡ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን የአይሁድ መሪዎች እንደ ካዱና ሊገድሉት ያሤሩ እንደ ነበር ዐወቀ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-03.jpg)
የአይሁድ መሪዎች በሊቀ ካህናቱ እየተመሩ፣ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጣቸው ለይሁዳ ሠላሳ ብር ከፈሉት፡፡ ልክ ነቢያት እንደ ተነበዩት ይህ ሆነ፡፡ ይሁዳ ተስማማ፣ ገንዘቡንም ይዞ ሄደ፡፡ ኢየሱስን እንዲይዙት ሊረዳቸው አጋጣሚ መፈለግ ጀመረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-04.jpg)
በኢየሩሳሌም፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ፋሲካን አከበረ፡፡ በፋሲካው ምግብ ጊዜ ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ቈረሰ፡፡ እንዲህም አለ፣ ‹‹እንካችሁ ይህንን ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ የተሰጠ ሥጋዬ ነው፡፡ ይህንን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፡፡›› በዚህ ዓይነት ኢየሱስ ሥጋው ስለ እርሱ እንደሚሠዋ ነገራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-05.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ ጽዋን አንሣና፣ ‹‹ይህንን ጠጡ፡፡ ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የዐዲስ ኪዳን ደሜ ነው፡፡ ይህንን በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ለመታሰቢያዬ አድርጉት፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-06.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጠኛል›› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ደነገጡ፣ እንዲህ ያለ ነገር ማን ያደርጋል ብለውም ጠየቁ፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ይህንን ቊራሽ እንጀራ የምሰጠው ሰው እኔን አሳልፎ ይሰጠኛል›› አለ፡፡ ከዚያ በኋላ እንጀራውን ለይሁዳ ሰጠው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-07.jpg)
ይሁዳ እንጀራውን ከተቀበለ በኋላ፣ ሰይጣን ገባበት፡፡ ይሁዳ ኢየሱስን እንዲይዙ የአይሁድ መሪዎችን ሊረዳቸው ሄደ፡፡ ጊዜው ማታ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-08.jpg)
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ እራት ከበሉ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ሄዱ፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ዛሬ ማታ ሁላችሁም ትተዉኛላችሁ፡፡ ‹እረኛውን እመታለሁ በጎቹም ሁሉ ይበተናሉ› ተብሎ ተጽፎአል›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-09.jpg)
ጴጥሮስ፣ ‹‹ሌሎቹ ሁሉ ቢተዉህ እንኳ፣ እኔ ግን አላደርገውም! ብሎ መለሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፣ ‹‹ሰይጣን ሁላችሁንም ሊወስዳችሁ ይፈልጋል፣ ነገር ግን ጴጥሮስ እምነትህ እንዳይደክም ጸልዬልሃለሁ፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን ዛሬ ማታ ዶሮ ከመጮኹ በፊት እንደማታውቀኝ እንኳ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-10.jpg)
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስ፣ ‹‹መሞት ቢኖርብኝ እንኳ፣ ከቶ አልክድህም›› አለው፡፡ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ሁሉ ይህንኑ አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-11.jpg)
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደሚባል ቦታ ሄደ፡፡ ኢየሱስ ወደ ፈተና እንዳይገቡ እንዲጸልዩ ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ብቻውን ሊጸልይ ሄደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-12.jpg)
ኢየሱስ ሦስት ጊዜ ጸለየ፣ ‹‹አባቴ ሆይ፣ ቢቻልስ ይህን የመከራ ጽዋ እንዳልጠጣው አድርግ፡፡ ነገር ግን የሰዎች ኃጢአት ይቅር የሚባልበት ሌላ መንገድ ከሌለ፣ ፈቃድህ ይሁን፡፡›› ኢየሱስ በጣም ታወከ ላቡም እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ፡፡ እግዚአብሔር ሊያበረታታው መልአክ ላከ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-13.jpg)
ከእያንዳንዱ የጸሎት ጊዜ በኋላ ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመላለሰ፣ እነርሱ ግን ተኝተው ነበር፡፡ ሦስተኛ በተመለሰ ጊዜ ግን፣ ‹‹ተነሡ! አሳልፎ የሚሰጠኝ እዚህ ነው›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-14.jpg)
ይሁዳ ከአይሁድ መሪዎች፣ ከወታደሮችና ከብዙ ሕዝብ ጋር መጣ፡፡ ሰይፍና ዱላ ይዘው ነበር፡፡ ይሁዳ ወደ ኢየሱስ መጣና፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን›› አለው፣ ሳመውም፡፡ ይህም የአይሁድ መሪዎች ማንን እንደሚይዙ ምልክት ነበር፡፡ ከዚያም ኢየሱስ፣ ‹‹ይሁዳ፣ በመሳም አሳልፈህ ትሰጠኛለህን? አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-38-15.jpg)
ወታደሮቹ ኢየሱስን እንደ ያዙት፣ ጴጥሮስ ሰይፉን መዘዘና የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮ ቈረጠ፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ! ይከላከሉልኝ ዘንድ የመላእክት ሠራዊት እንዲልክልኝ አባቴን መጠየቅ እችላለሁ›› አለው፡፡ ከዚያም ኢየሱስ የሰውዬውን ጆሮ ፈወሰው፡፡ ኢየሱስ ከተያዘ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ሸሹ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 26፡14-56፤ ማርቆስ 14፡10-50፤ ሉቃስ 22፡1-53፤ ዮሐንስ 12፡6፤ 18፡1-11፡፡___

52
content/39.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,52 @@
# 39. ኢየሱስ ለፍርድ ቀረበ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-01.jpg)
አሁን ጊዜው እኩለ ሌሊት ነው፡፡ ሊቀ ካህናቱ ይጠይቀው ዘንድ ወታደሮቹ ኢየሱስን ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት ወሰዱት፡፡ ጴጥሮስ ራቅ ብሎ ከኋላ ተከተላቸው፡፡ ኢየሱስን ወደ ቤቱ ባስገቡት ጊዜ፣ ጴጥሮስ በውጪ ሆኖ እሳት ይሞቅ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-02.jpg)
በቤቱ ውስጥ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ለፍርድ አቀረቡት፡፡ ስለ እርሱ የዋሹ ብዙ የሐሰት ምስክሮችን አመጡ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ቃላቸው እርስ በርሱ አልተስማማም፣ ስለዚህ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስ በማንኛውም ነገር በደለኛ መሆኑን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-03.jpg)
በመጨረሻ፣ ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን በቀጥታ ተመለከተውና፣ ንገረን፣ አንተ መሲሑ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህን? አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-04.jpg)
ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ተቀምጬና ከሰማይ ስመጣ ታያለህ›› አለው፡፡ ሊቀ ካህናቱ በቊጣ ልብሱን ቀደደና ወደ ሌሎቹ የሃይማኖት መሪዎች፣ ‹‹ተጨማሪ ምስክሮች አያስፈልጉም! የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ሲል ሰምታችሁታል፡፡ ፍርዳችሁ ምንድን ነው? ብሎ ጮኸ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-05.jpg)
ሁሉም የአይሁድ መሪዎች፣ ‹‹መሞት ይገባዋል! ብለው ለሊቀ ካህናቱ መለሱለት፡፡ ከዚያም ኢየሱስን ፊቱን ሸፈኑት፣ ተፉበት፣ መቱት፣ ዘበቱበትም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-06.jpg)
ጴጥሮስ ከቤቱ ውጪ በመጠባበቅ ላይ እያለ የቤት ሠራተኛ የሆነች ልጅ ዐየችውና፣ ‹‹አንተም ደግሞ ከኢየሱስ ጋር ነበርክ! አለችው፡፡ ጴጥሮስ እርስዋ የተናገረችውን ካደ፡፡ ከዚያ በኋላ ሌላዋ የቤት ሠራተኛ ያንኑ ተናገረች፣ ጴጥሮስም እንደገና ካደ፡፡ በመጨረሻ ሕዝቡ ‹‹ሁለታችሁም ከገሊላ ስለሆናችሁ አንተ ከኢየሱስ ጋር መሆንህን እናውቃለን›› አሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-07.jpg)
ከዚያም ጴጥሮስ፣ ‹‹ይህንን ሰው የማውቀው ከሆነ የእግዚአብሔር መርገም በእኔ ላይ ይሁን! ብሎ ማለ፡፡ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ፣ ኢየሱስም ዘወር አለና ጴጥሮስን ተመለከተው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-08.jpg)
ጴጥሮስ ሄደና በምሬት አለቀሰ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ፣ የአይሁድ መሪዎች እንዲሞት በኢየሱስ ላይ እንደ ፈረዱበት ዐየ፡፡ ይሁዳ በሐዘን ተሞልቶ ሄደና ራሱን ገደለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-09.jpg)
በነጋታው ማለዳ ላይ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ወደ ሮማው ገዥ ወደ ጲላጦስ አመጡት፡፡ ጲላጦስ ኢየሱስን ጥፋተኛ ነህ ብሎ ይፈርድበትና በሞት እንዲቀጣ ያደርጋል ብለው ተስፋ አደረጉ፡፡ ጲላጦስ ኢየሱስን፣ ‹‹የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-10.jpg)
ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ ‹‹አንተ አልህ፣ ነገር ግን መንግሥቴ ምድራዊ መንግሥት አይደለችም፡፡ እንደዚያ ብትሆን ኖሮ፣ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር፡፡ ስለ እግዚአብሔር እውነቱን ለመናገር ወደ ምድር መጥቼአለሁ፡፡ እውነትን የሚወድ ሁሉ እኔን ይሰማኛል፡፡›› ጲላጦስ፣ ‹‹እውነት ምንድን ነው? አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-11.jpg)
ጲላጦስ ከኢየሱስ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሕዝቡ ወጣና፣ ‹‹በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም›› አለ፡፡ የአይሁድ መሪዎችና ሕዝቡ ግን፣ ‹‹ስቀለው! ብለው ጮኹ፡፡ ጲላጦስ፣ ‹‹በደለኛ አይደለም›› ብሎ መለሰላቸው፡፡ እነርሱ ግን የበለጠ ጮኹ፡፡ ከዚያም ጲላጦስ ለሦስተኛ ጊዜ፣ ‹‹በደል የለበትም! አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-39-12.jpg)
ጲላጦስ ሕዝቡ መረበሽ ይጀምራሉ ብሎ ፈራ፣ ስለዚህ ኢየሱስን እንዲሰቅሉት ወታደሮቹን አዘዘ፡፡ የሮማ ወታደሮች ኢየሱስን ገረፉትና ቀይ ልብስ አለበሱት፣ እንዲሁም የሾኽ አክሊል በራሱ ላይ አደረጉ፡፡ ከዚያም፣ ‹‹እነሆ፣ የአይሁድ ንጉሥ! በማለት ዘበቱበት፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 26፡57-27፡26፤ ማርቆስ 14፡53-15፡15፤ ሉቃስ 22፡54-23፡25፤ ዮሐንስ 18፡12-19፡16፡፡___

40
content/40.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,40 @@
# 40. ኢየሱስ ተሰቀለ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-01.jpg)
ወታደሮቹ በኢየሱስ ላይ ከዘበቱ በኋላ፣ ሊሰቅሉት ወሰዱት፡፡ የሚሞትበትን እንዲሸከም አደረጉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-02.jpg)
ወታደሮቹ ኢየሱስን ‹‹የራስ ቅል›› ተብሎ ወደሚጠራ ስፍራ አመጡትና እጆቹንና እግሮቹን በመስቀል ላይ ጠረቁአቸው፡፡ ኢየሱስ ግን፣ ‹‹አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን ዐያውቁምና ይቅር በላቸው›› አለ፡፡ ጲላጦስ፣ በምልክት ላይ፣ ‹‹የአይሁድ ንጉሥ›› ብለው እንዲጽፉና ከኢየሱስ ራስ በላይ በመስቀሉ ላይ እንዲያኖሩት አዘዘ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-03.jpg)
ወታደሮቹ በኢየሱስ ልብስ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፡፡ ይህንን ባደረጉበት ጊዜ፣ ‹‹ልብሶቼን ተከፋፈሉ፣ በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ›› የሚለውን ትንቢት ፈጸሙ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-04.jpg)
ኢየሱስ በሁለት ወንበዴዎች መካከል ተሰቀለ፡፡ አንደኛው በኢየሱስ ላይ ዘበተበት፣ ሌላኛው ግን፣ ‹‹አንተ እግዚአብሔርን አትፈራም? እኛ በደለኞች ነን፣ ይህ ሰው ግን በደል የለበትም›› አለ፡፡ ከዚያም ኢየሰስን፣ ‹‹እባክህን በመንግሥትህ ዐስበኝ›› አለው፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ›› ብሎ መለሰለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-05.jpg)
የአይሁድ መሪዎችና በሕዝቡ መካከል የነበሩ ሌሎች ሰዎች በኢየሱስ ላይ ተዘባበቱበት፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ከመስቀል ላይ ውረድና ራስህን አድን! ከዚያ በኋላ እናምንብሃለን›› አሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-06.jpg)
በዚያን ጊዜ እኩለ ቀን ቢሆንም፣ በአካባቢው ሁሉ ላይ ሰማዩ ፍጹም ጨለማ ሆነ፡፡ ከእኩለ ቀን እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ እንደ ጨለመ ቆየ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-07.jpg)
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ፣ ‹‹ተፈጸመ! አባት ሆይ፣ ነፍሴን በእጅህ እሰጣለሁ›› ብሎ ጮኸ፡፡ ከዚያም ራሱን አዘነበለና መንፈሱን ሰጠ፡፡ በሞተ ጊዜ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፣ በቤተ መቅደስ የነበረው ሕዝቡን ከእግዚአብሔር መገኘት የለየው ትልቁ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-08.jpg)
ኢየሱስ በሞቱ በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡ ለሰዎች መንገድ ከፈተላቸው፡፡ ኢየሱስን ይጠብቅ የነበረው ወታደር የሆነውን ሁሉ ባየ ጊዜ፣ ‹‹በእርግጥ ይህ ሰው በደል የለበትም፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-40-09.jpg)
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን ያመኑ ሁለት የአይሁድ መሪዎች፣ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ የኢየሱስን ሥጋ እንዲሰጣቸው ጲላጦስን ለመኑት፡፡ ሥጋውን በጨርቅ ገነዙትና ከአለት በተወቀረ መቃብር አኖሩት፡፡ ከዚያም ክፍቱን ስፍራ ለመዝጋት ከመቃብሩ ፊት ለፊት ትልቅ ድንጋይ አንከባለሉ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 27፡27-61፤ ማርቆስ 15፡16-47፤ ሉቃስ 23፡26-56፤ ዮሐንስ 19፡17-42፡፡___

36
content/41.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,36 @@
# 41. እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሙታን አስነሣው #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-01.jpg)
ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ፣ የማያምኑት የአይሁድ መሪዎች ጲላጦስን፣ ‹‹ያ ውሸታም፣ ኢየሱስ፣ ከሦስት ቀን በኋላ ከሙታን እነሣለሁ ብሎአል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን እንዳይሰርቁትና ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ ለማረጋገጥ አንድ ሰው መቃብሩን መጠበቅ አለበት›› አሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-02.jpg)
ጲላጦስ፣ ‹‹አንዳንድ ወታደሮችን ውሰዱና መቃብሩን በተቻለ መጠን እንዲጠበቅ አድርጉ›› አለ፡፡ ስለዚህ በመቃብሩ መግቢያ ባለው ድንጋይ ላይ ማኅተም አደረጉና ሥጋውን ማንም እንዳይሰርቀው ለማረጋገጥ በዚያ ወታደሮችን አቆሙ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-03.jpg)
ኢየሱስ ከተሰቀለ በኋላ የነበረ ቀን ሰንበት ነበረ፡፡ አይሁድ በዚያ ቀን ወደ መቃብር እንዲሄዱ አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ ስለዚህ ከሰንበት ቀን በኋላ በማለዳ ብዙ ሴቶች ሥጋው ላይ ተጨማሪ ሽቱ ለማርከፍከፍ ወደ ኢየሱስ መቃብር ሊሄዱ ተዘጋጁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-04.jpg)
በድንገትም ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፡፡ እንደ መብረቅ የሚያበራ መልአክ ከሰማይ ታየ፡፡ የመቃብሩን መግቢያ ከድኖ የነበረውን ድንጋይ አንከባለለና ተቀመጠበት፡፡ መቃብሩን ይጠብቁ የነበሩት ወታደሮች ፈሩና እንደ ሞቱ ሰዎች ሆነው መሬት ላይ ወደቁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-05.jpg)
ሴቶቹ ወደ መቃብሩ በደረሱ ጊዜ መልአኩ፣ ‹‹አትፍሩ ኢየሱስ እዚህ የለም፡፡ ልክ እነሣለሁ ብሎ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነሥቶአል! መቃብሩን ተመልከቱና እዩ›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ውስጥ ተመለከቱና የኢየሱስን ሥጋ ያኖሩበትን ስፍራ ዐዩ፡፡ ሥጋው በዚያ አልነበረም!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-06.jpg)
ከዚያም መልአኩ ለሴቶቹ፣ ‹‹ሂዱና ‹ኢየሱስ ከሙታን ተነሥቶአል ቀድሞአችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው››› ብሎ ነገራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-07.jpg)
ሴቶቹ በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ተሞልተው ነበር፡፡ የምሥራቹን ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር እየሮጡ ሄዱ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-41-08.jpg)
ሴቶቹ የምሥራቹን ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር በመሄድ ላይ እያሉ፣ ኢየሱስ ታያቸው፣ እነርሱም ሰገዱለት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹አትፍሩ፡፡ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለደቀ መዛሙርቴ ንገሩአቸው፡፡ በዚያ ያዩኛል›› አላቸው፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 27፡62-28፡15፤ ማርቆስ 16፡1-11፤ ሉቃስ 24፡1-12፤ ዮሐንስ 20፡1-18፡፡___

48
content/42.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,48 @@
# 42. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-01.jpg)
ኢየሱስ ከሙታን በተነሣበት ቀን ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱ በአቅራቢያው ወዳለች ከተማ እየሄዱ ነበር፡፡ ሲጓዙም፣ በኢየሱስ ላይ ስለ ደረሰው ነገር ተነጋገሩ፡፡ እርሱ መሲሕ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገው ነበር፣ ነገር ግን ያኔ እርሱ ተገደለ፡፡ አሁን ሴቶቹ እንደ ገና ሕያው ሆኖአል አሉ፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት የሚያምኑትን ነገር ዐላወቁም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-02.jpg)
ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበና አብሮአቸው ይጓዝ ጀመር፣ እነርሱ ግን ዐላወቁትም፡፡ ስለ ምን ይነጋገሩ እንደ ነበረ ጠየቃቸው፣ እነርሱም ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢየሱስን በሚመለከት ስለ ሆኑት አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ነገሩት፡፡ በኢየሩሳሌም የሆነውን ነገር ከማያውቅ እንግዳ ጋር ይነጋገሩ እንደ ነበር ዐሰቡ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-03.jpg)
ከዚያም ኢየሱስ፣ ስለ መሲሑ የእግዚአብሔር ቃል የተናገረውን አብራራላቸው፡፡ መሲሑ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚገደል፣ ነገር ግን በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነቢያት የተናገሩትን አስታወሳቸው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ሊያድሩባት ወዳሰቡአት ከተማ ሲደርሱ፣ ጊዜው ሊመሽ ምንም ያህል አልቀረውም ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-04.jpg)
ሁለቱ ሰዎች ከእነርሱ ጋር እንዲያድር ጋበዙት፣ እርሱም ግብዣቸውን ተቀበለ፡፡ እራት ለመብላት በተዘጋጁ ጊዜ ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ እግዚአብሔርን አመሰገነ፣ ከዚያም ቈረሰው፡፡ በድንገትም ኢየሱስ መሆኑን ዐወቁ፡፡ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እርሱ ከዓይናቸው ተሰወረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-05.jpg)
ሁለቱ ሰዎች፣ ‹‹ኢየሱስ ነው! የእግዚአብሔርን ቃል ሲያብራራልን ልባችን ሲቃጠልብን የነበረው ስለዚህ ነው! ተባባሉ። ወዲያውኑ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ በደረሱ ጊዜም ለደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹ኢየሱስ ሕያው ነው! ዐይተነዋል! ብለው ነገሩአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-06.jpg)
ደቀ መዛሙርቱ እየተነጋገሩ እያሉ፣ ኢየሱስ በድንገት በነበሩበት ክፍል በመካከላቸው ታየና፣ ‹‹ሰላም ለእናንተ ይሁን! አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ መንፈስ መሰላቸው፣ ኢየሱስ ግን፣ ‹‹ለምን ትፈራላችሁ ትጠራጠራላችሁም? እጆቼንና እግሮቼን እዩ፡፡ መናፍስት እንደ እኔ አካል የላቸውም›› አላቸው፡፡ መንፈስ አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚበላ ነገር እንዲሰጡት ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቊራጭ ሰጡት፣ በላም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-07.jpg)
ኢየሱስም፣ ‹‹በእግዚአብሔር ቃል ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም አለበት ብዬ ነግሬአችኋለሁ›› አለ፡፡ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲረዱ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፡፡ ‹‹መሲሑ መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚሞት፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሣ ከረጅም ዘመን በፊት ተጽፎአል›› አላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-08.jpg)
‹‹ደግሞም በመጻሕፍት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ለማግኘት ሰዎች ሁሉ ንስሐ ይገቡ ዘንድ ደቀ መዛሙርቴ እንደሚያውጁ ተጽፎአል፡፡ እነርሱ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ይህን ያደርጋሉ፣ ከዚያም በሁሉም ስፍራ ወዳሉ የሕዝብ ወገኖች ሁሉ ይሄዳሉ፡፡ እናንተ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ናችሁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-09.jpg)
በቀጣዮቹ አርባ ቀናት ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ታያቸው፡፡ አንዴ ከ500 ለሚበልጡ ሰዎች በአንድ ጊዜ ታይቶአል! ሕያው መሆኑን በብዙ መንገድ ለደቀ መዛሙርቱ አረጋገጠላቸው፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም አስተማራቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-10.jpg)
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፣ ‹‹ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፡፡ ስለዚህ ሂዱ፣ የሕዝብ ወገኖችን ሁሉ በአብ፣ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው፡፡ እኔ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር እንደምሆን አስታውሱ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-42-11.jpg)
ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ ከአርባ ቀናት በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በመጣ ጊዜ አባቴ ኃይልን እስኪሰጣችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ›› አላቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ወጣ፣ ደመናም ከዓይናቸው ሰወረችው፡፡ ኢየሱስ በፍጥረት ሁሉ ላይ ሊገዛ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 28፡16-20፤ ማርቆስ 16፡12-20፤ ሉቃስ 24፡13-53፤ ዮሐንስ 20፡19-23፤ የሐዋርያት ሥራ 1፡1-11፡፡___

56
content/43.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,56 @@
# 43. ቤተ ክርስቲያን ተጀመረች #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-01.jpg)
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው በኢየሩሳሌም ቆዩ፡፡ በዚያ የነበሩት አማኞች ለመጸለይ ያለ ማቋረጥ ተሰበሰቡ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-02.jpg)
አይሁድ በያመቱ ከፋሲካ በኋላ ባሉት 50 ቀናት ጴንጤቆስጤ ተብሎ የሚጠራ አስፈላጊ ቀን ያከብሩ ነበር፡፡ ጴንጤቆስጤ አይሁድ የመከር በዓልን የሚያከብሩበት ቀን ነበር፡፡ አይሁድ ጴንጤቆስጤን በአንድነት ለማክበር ከመላው ዓለም ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፡፡ በዚህ ዓመት፣ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ የጴንጤቆስጤ ጊዜ መጣ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-03.jpg)
አማኞቹ ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው እያሉ፣ በድንገት የነበሩበት ቤት ድምፅ በመሰለ ብርቱ ነፋስ ተሞላ፡፡ ከዚያም በአማኞቹ ሁሉ ራስ ላይ የእሳት ነበልባል የሚመስል ነገር ታየ፡፡ ሁላቸውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉና በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-04.jpg)
በኢየሩሳሌም የነበሩት ሰዎች ድምፅን በሰሙ ጊዜ፣ በመሆን ላይ የነበረውን ነገር ለማየት በብዛት መጡ፡፡ አማኞቹ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች ሲያውጁ ሰዎቹ በሰሙ ጊዜ እነዚህን ነገሮች በገዛ ራሳቸው ቋንቋ በመስማታቸው ተደነቁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-05.jpg)
አንዳንዶቹ ሰዎች ደቀ መዛሙርቱ ሰክረዋል ብለው ወቀሱአቸው፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ ቆመና እንዲህ አላቸው፣ ‹‹ስሙኝ! እነዚህ ሰዎች አልሰከሩም! እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዮኤል ‹በመጨረሻው ቀን መንፈሴን አፈስሳለሁ! ያለው ትንቢት በዚህ ይፈጸማል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-06.jpg)
‹‹የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እናንተ እንዳያችሁትና አስቀድማችሁ እንደምታውቁት ኢየሱስ በእግዚአብሔር ኃይል ብዙ ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደረገ ሰው ነው፡፡ ነገር ግን እናንተ ሰቀላችሁት!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-07.jpg)
‹‹ኢየሱስ ቢሞትም እንኳ እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፡፡ ይህም ‹ቅዱስህንም በመቃብር መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም› የሚለው ትንቢት ፍጻሜ ነው፡፡ እግዚአብሔር ኢየሱስን ሕያው አድርጎ እንዳስነሣው እኛ ምስክሮች ነን፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-08.jpg)
‹‹ኢየሱስ አሁን በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ከፍ ብሎአል፡፡ ደግሞም ኢየሱስ ልክ ተስፋ እንደ ሰጠው መንፈስ ቅዱስን ልኮአል፡፡ አሁን የምታዩአቸውንና የምትሰሙአቸውን ነገሮች መንፈስ ቅዱስ ነው ያደረጋቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-09.jpg)
‹‹ይህንን ኢየሱስን ሰቀላችሁት፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ኢየሱስን ጌታና መሲሕ እንዳደረገው በእርግጥ እወቁ!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-10.jpg)
ጴጥሮስን ይሰሙ የነበሩት ሰዎች በተናገራቸው ነገሮች በእጅጉ ተነኩ፡፡ ስለዚህ ጴጥሮስንና ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹ወንድሞች ሆይ፣ ምን እናድርግ? ብለው ጠየቁአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-11.jpg)
ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ ‹‹እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ እያንዳንዳችሁ ንስሐ ግቡና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፡፡ ከዚያ በኋላ እርሱ የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ደግሞ ይሰጣችኋል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-12.jpg)
3000 የሚያህሉ ሰዎች ጴጥሮስ የተናገረውን አምነው የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ፡፡ እነርሱ ተጠምቀው በኢየሩሳሌም ያለችው ቤተ ክርስቲያን አባል ሆኑ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-43-13.jpg)
ደቀ መዛሙርቱ ያለ ማቋረጥ የሐዋርያትን ትምህርት ሰሙ፣ አብረው ጊዜ አሳለፉ፣ አብረው በሉ፣ አንዳቸው ለሌላኛው ጸለዩ፡፡ አብረው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፣ የነበራቸውንም ነገር ሁሉ እርስ በርስ ተካፈሉ፡፡ ሁሉም ሰው ስለ እነርሱ መልካም ያስብ ነበር፡፡ በየዕለቱ ብዙ ሰዎች አማኞች ሆኑ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሐዋርያት ሥራ 2፡፡___

40
content/44.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,40 @@
# 44. ጴጥሮስና ዮሐንስ ይለምን የነበረውን ሰው ፈወሱ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-01.jpg)
አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደስ ይሄዱ ነበር፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ ደጃፍ እንደ ቀረቡ፣ ገንዘብ ይለምን የነበረ ሽባ ሰው ዐዩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-02.jpg)
ጴጥሮስ ሽባውን ተመለከተውና፣ ‹‹የምሰጥህ ምንም ገንዘብ የለኝም፡፡ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም ተነሣና ተመላለስ! አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-03.jpg)
ወዲያውኑ እግዚአብሔር ሽባውን ሰው ፈወሰው፣ እርሱም መራመድና መዝለል፣ እግዚአብሔርንም ማመስገን ጀመረ፡፡ በቤተ መቅደሱ አጥር ግቢ የነበሩት ሰዎች ተደነቁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-04.jpg)
ሕዝብም የተፈወሰውን ሰው ለማየት ፈጥነው ተሰበሰቡ፡፡ ጴጥሮስ እንዲህ አላቸው፣ ‹‹ይህ ሰው ስለ ተፈወሰ ለምን ተደነቃችሁ? በገዛ ኃይላችን ወይም በጎነታችን አልፈወስነውም፡፡ ይልቁንም ይህንን ሰው የፈወሰው የኢየሱስ ኃይልና ኢየሱስ የሚሰጠው እምነት ነው፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-05.jpg)
‹‹ኢየሱስን እንዲገድለው ለሮማው ገዥ የነገራችሁት እናንተ ናችሁ፡፡ የሕይወትን ጀማሪ ገደላችሁት፣ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፡፡ ታደርጉት የነበረው ነገር ባይገባችሁም እንኳ፣ መሲሑ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚሞት የተነገሩትን ትንቢቶች ለመፈጸም እግዚአብሔር በድርጊቶቻችሁ ተጠቀመ፡፡ ስለዚህ ኃጢአታችሁ ይታጠብላችሁ ዘንድ አሁን ንስሐ ግቡና ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-06.jpg)
የቤተ መቅደሱ መሪዎች ጴጥሮስና ዮሐንስ ይናገሩት በነበረው ነገር በጣም ተበሳጩ፡፡ ስለዚህ ያዙአቸውና እስር ቤት አስገቡአቸው፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች የጴጥሮስን መልእክት አመኑ፣ በኢየሱስ ያመኑት ሰዎች ቊጥርም ወደ 5,000 ገደማ ዐደገ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-07.jpg)
በማግስቱ፣ የአይሁድ መሪዎች ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ሊቀ ካህናቱና ወደ ሌሎቹ የሃይማኖት መሪዎች አመጡአቸው፡፡ ጴጥሮስንና ዮሐንስን፣ ‹‹ይህንን ሽባ ሰው በምን ኃይል ፈወሳችሁት? ብለው ጠየቁአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-08.jpg)
ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ ‹‹ይህ ሰው በመሲሑ በኢየሱስ ኃይል ተፈውሶ በፊታችሁ ቆሞአል፡፡ እናንተ ኢየሱስን ሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ግን እንደ ገና አስነሣው! እናንተ አልተቀበላችሁትም፣ ነገር ግን በኢየሱስ ኃይል ካልሆነ በቀር ሌላ የመዳን መንገድ የለም!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-44-09.jpg)
ጴጥሮስና ዮሐንስ በጣም በድፍረት በመናገራቸው እነዚህ መሪዎች ደነገጡ፣ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ማየት ችለው ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ አስታወሱ፡፡ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ካስፈራሩአቸው በኋላ፣ እንዲሄዱ ለቀቁአቸው፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሐዋርያት ሥራ 3፡1-4፡22፡፡ ___

56
content/45.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,56 @@
# 45. ፊልጶስና ኢትዮጵያዊው ባለ ሥልጣን #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-01.jpg)
በጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን ከነበሩት መሪዎች አንዱ እስጢፋኖስ ተብሎ የሚጠራ ሰው ነበር፡፡ እርሱ መልካም ስም ያለውና መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላበት ሰው ነበር፡፡ እስጢፋኖስ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ሰዎች በኢየሱስ እንዲያምኑ አሳማኝ ምክንያት የሚያቀርብ ሰው ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-02.jpg)
አንድ ቀን እስጢፋኖስ ስለ ኢየሱስ በሚያስተምርበት ጊዜ፣ በኢየሱስ ያላመኑ አንዳንድ አይሁድ ከእስጢፋኖስ ጋር መከራከር ጀመሩ፡፡ በጣም ተቈጡና ስለ እስጢፋኖስ ለሃይማኖት መሪዎች ዋሽተው ተናገሩ፡፡ ‹‹ስለ ሙሴና ስለ እግዚአብሔር ክፉ ነገሮችን ሲናገር ሰምተነዋል! አሉ፡፡ ስለዚህ የሃይማኖት መሪዎቹ እስጢፋኖስን ያዙትና ተጨማሪ የሐሰት ምስክሮች ስለ እስጢፋኖስ ዋሽተው ወደተናገሩበት ወደ ሊቀ ካህናቱና ወደ ሌሎቹ የአይሁድ መሪዎች አመጡት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-03.jpg)
ሊቀ ካህናቱ እስጢፋኖስን፣ ‹‹እነዚህ ነገሮች እውነት ናቸውን? ብሎ ጠየቀው፡፡ እስጢፋኖስ ከአብርሃም ዘመን ጀምሮ እስከ ኢየሱስ ዘመን ድረስ እግዚአብሔር ስላደረጋቸው ብዙ ታላላቅ ነገሮች፣ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሕዝብ በተከታታይ በእርሱ ላይ ስለ ማመፃቸው በማስታወስ መልስ ሰጠ፡፡ ከዚያም እንዲህ አለ፣ ‹‹እናንተ አንገተ ደንዳኖችና ዓመፀኞች ሕዝብ ልክ ቅድማያቶቻችሁ እግዚአብሔርን እንደ ተቃወሙትና ነቢያቱን እንደ ገደሉ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፡፡ እናንተ ግን ከእነርሱ ይልቅ የባሰ ነገር አድርጋችኋል፡፡ መሲሑን ገድላችኋል!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-04.jpg)
የሃይማኖት መሪዎቹ ይህንን በሰሙ ጊዜ፣ ጆሮአቸውን እስኪደፍኑና ከፍ ባለ ድምፅ እስኪጮኹ ድረስ በጣም ተቈጡ፡፡ እስጢፋኖስን ከከተማይቱ ውጪ ጐተቱትና ሊገድሉት በድንጋይ ወገሩት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-05.jpg)
እስጢፋኖስ በመሞት ላይ እያለ፣ ‹‹ኢየሱስ ሆይ፣ ነፍሴን ተቀበላት›› ብሎ ጮኸ፡፡ ከዚያም በጉልበቱ ተንበረከከና፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ይህንን ኃጢአት አትቊጠርባቸው›› ብሎ እንደ ገና ጮኸ፡፡ ከዚያ በኋላ ሞተ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-06.jpg)
ሳውል የተባለ ወጣት እስጢፋኖስን ከገደሉት ሰዎች ጋር ተስማማና በእርሱ ላይ ድንጋይ በሚወረውሩበት ጊዜ ልብሳቸውን ይጠብቅ ነበር፡፡ በዚያን ዕለት በኢየሩሳሌም የነበሩ ብዙ ሰዎች የኢየሱስን ተከታዮች ማሳደድ ጀመሩ፣ ስለዚህ አማኞቹ ወደ ሌሎች ስፍራዎች ሸሹ፡፡ ነገር ግን ስደቱ ቢኖርም እንኳ፣ በሄዱበት ስፍራ ሁሉ ስለ ኢየሱስ ሰበኩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-07.jpg)
ፊልጶስ የተባለ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር በስደቱ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ከሸሹት አማኞች አንዱ ነበር፡፡ ወደ ሰማርያ ሄዶ ስለ ኢየሱስ ሰበከና ብዙ ሰዎች ዳኑ፡፡ ከዚያ በኋላ አንድ ቀን ከእግዚአብሔር የተላከ መልአክ በምድረ በዳ ወዳለ አንድ መንገድ እንዲሄድ ለፊልጶስ ነገረው፡፡ ፊልጶስ በመንገዱ በመሄድ ላይ እያለ አንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ባለ ሥልጣን በሰረገላው ሲሄድ ዐየ፡፡ ወደዚህ ሰው ሄዶ እንዲያነጋግረው መንፈስ ቅዱስ ለፊልጶስ ነገረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-08.jpg)
ፊልጶስ ወደ ሰረገለው በቀረበ ጊዜ፣ ኢትዮጵያዊው ነቢዩ ኢሳይያስ ከጻፈው ውስጥ አንዱን ክፍል ሲያነብ ሰማ፡፡ ሰውዬው እንዲህ አነበበ፣ ‹‹እንደሚታረድ በግ ነዱት፣ በግ ዝም እንደሚል አንድም ቃል አልተናገረም፡፡ በፍርድ ተወሰደ፣ አላከበሩትምም፡፡ ከሕያዋን ምድር አስወገዱት፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-09.jpg)
ፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን፣ ‹‹የምታነበውን ታስተውለዋለህን? ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢትዮጵያዊው፣ ‹‹አይደለም፡፡ የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር ላስተውለው አልችልም፡፡ እባክህን ናና ከጐኔ ተቀመጥ፡፡ ኢሳይያስ የጻፈው ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለ ሌላ ሰው?
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-10.jpg)
ኢሳይያስ የጻፈው ስለ ኢየሱስ መሆኑን ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው አብራራለት፡፡ ደግሞም ፊልጶስ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች ሊነግረው ሌሎች የእግዚአብሔር ቃል ክፍሎችን ተጠቀመ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-11.jpg)
ፊልጶስና ኢትዮጵያዊው እንደ ተጓዙ፣ ውሃ ወዳለበት ስፍራ ደረሱ፡፡ ኢትዮጵያዊው፣ ‹‹እነሆ፣ በዚያ ቦታ ውሃ አለ! ልጠመቅን? አለ፡፡ ለነጂውም ሰረገላውን እንዲያቆመው ነገረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-12.jpg)
ስለዚህ ወደ ውሃው ወረዱ፣ ፊልጶስም ኢትዮጵያዊውን አጠመቀው፡፡ ከውሃው ከወጡ በኋላ መንፈስ ቅደስ በድንገት ፊልጶስን ወደ ሌላ ስፍራ ነጠቀው፤ ስለ ኢየሱስ ለሰዎች መናገሩንም ቀጠለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-45-13.jpg)
ኢትዮጵያዊው ኢየሱስን በማወቁ እየተደሰተ ወደ አገሩ ለመመለስ ጕዞውን ቀጠለ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሐዋርያት ሥራ 6፡8-8፡5፤ 8፡26-40፡፡___

44
content/46.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,44 @@
# 46. ጳውሎስ ክርስቲያን ሆነ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-01.jpg)
ሳውል እስጢፋኖስን የገደሉት ሰዎች ልብስ ይጠብቅ የነበረ ወጣት ነበረ፡፡ በኢየሱስ አላመነም፣ ስለዚህም አማኞችን አሳደደ፡፡ ወንዶችንና ሴቶችን እየያዘ ወደ እስር ቤት ለመጨመር በኢየሩሳሌም ከቤት ወደ ቤት ሄደ፡፡ ሊቀ ካህናቱ በዚያ ያሉትን ክርስቲያኖች ይይዝና ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ ያመጣቸው ዘንድ ወደ ደማስቆ ከተማ እንዲሄድ ለሳውል ፈቃድ ሰጠው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-02.jpg)
ሳውል ወደ ደማስቆ በመጓዝ ላይ እያለ፣ ከሰማይ ብሩህ ብርሃን በዙሪያው ሁሉ አበራ፣ እርሱም ወደ መሬት ወደቀ፡፡ አንድ ሰው፣ ‹‹ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? ሲለው ሰማ፡፡ ሳውል፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፣ ‹‹እኔ ኢየሱስ ነኝ፡፡ አንተ እያሳደድከኝ ነው! ብሎ መለሰለት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-03.jpg)
ሳውል በተነሣ ጊዜ፣ ማየት ተሳነው፡፡ ወዳጆቹ ወደ ደማስቆ እየመሩ ወሰዱት፡፡ ሳውል ለሦስት ቀናት ምንም አልበላም ወይም አልጠጣም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-04.jpg)
በደማስቆ ሐናንያ የተባለ ደቀ መዝሙር ነበረ፡፡ እግዚአብሔር ለሐናንያ፣ ‹‹ሳውል ወዳለበት ቤት ሂድ፡፡ እንደ ገና ያይ ዘንድ እጅህን ጫንበት›› አለው፡፡ ሐናንያ ግን፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰው አማኞችን እንዴት እንዳሳደደ ሰምቼአለሁ›› አለ፡፡ እግዚአብሔር፣ ‹‹ሂድ! ለአይሁዶችና ከሌሎች ሕዝቦች ለሆኑ ወገኖች ስሜን እንዲያውጅ መርጬዋለሁ፡፡ ስለ ስሜ ብዙ መከራ ይቀበላል›› አለው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-05.jpg)
ስለዚህ ሐናንያ ወደ ሳውል ሄደ፡፡ እጆቹን ጫነበት፣ እንዲህም አለ፣ ‹‹ወደዚህ ስትመጣ የታየህ ኢየሱስ፣ እንደ ገና ታይና በመንፈስ ቅዱስ ትሞላ ዘንድ ወዳንተ ላከኝ፡፡›› ሳውል ወዲያውኑ ማየት ቻለ፣ ሐናንያም አጠመቀው፡፡ ከዚያ በኋላ ሳውል ምግብ በላ፣ በረታም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-06.jpg)
ሳውል ወዲያውኑ፣ ‹‹ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው! በማለት በደማስቆ ለነበሩ አይሁድ መስበክ ጀመረ፡፡ አይሁዶች አማኞችን ለማጥፋት የሞከረው ሰው አሁን ደግሞ በኢየሱስ በማመኑ ተደነቁ! ሳውል ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን በማረጋገጥ አይሁዶችን አሳመነ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-07.jpg)
ከብዙ ቀናት በኋላ አይሁዶች ሳውልን ለመግደል ዐቀዱ፡፡ ይገድሉት ዘንድ በከተማይቱ በሮች የሚጠባበቁትን ሰዎች ላኩ፡፡ ነገር ግን ሳውል ስለ ዕቅዱ ሰማ፣ ወዳጆቹም እንዲያመልጥ ረዱት፡፡ አንድ ሌሊት በቅርጫት አድርገው በከተማዪቱ ቅጥር አወረዱት፡፡ ሳውል ከደማስቆ ካመለጠ በኋላ ስለ ኢየሱሰ መስበኩን ቀጠለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-08.jpg)
ሳውል ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመገናኘት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፣ እነርሱ ግን ፈሩት፡፡ በዚያን ጊዜ በርናባስ የተባለ አማኝ ሳውልን ወደ ሐዋርያቱ ወሰደውና ሳውል በደማስቆ እንዴት በድፍረት እንደ ሰበከ ነገራቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ሳውልን ተቀበሉት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-09.jpg)
በኢየሩሳሌም ከነበረው ስደት የሸሹ አንዳንድ አማኞች ወደ አንጾኪያ ርቀው ሄዱና ስለ ኢየሱስ ሰበኩ፡፡ በአንጾኪያ የነበሩት ብዙዎቹ ሰዎች አይሁዶች አልነበሩም፣ ነገር ግን ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በጣም ብዙዎቻቸው ደግሞ አማኞች ሆኑ፡፡ በርናባስና ሳውል እነዚህን ዐዳዲስ አማኞች በተጨማሪ ስለ ኢየሱስ ሊያስተምሯቸውና ቤተ ክርስቲያንን ሊያጠናክሩ ወደዚያ ሄዱ፡፡ በኢየሱስ የሚያምኑ መጀመሪያ ጊዜ በአንጾኪያ ‹‹ክርስቲያኖች›› ተባሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-46-10.jpg)
አንድ ቀን በአንጾኪያ የነበሩ ክርስቲያኖች እየጾሙና እየጸለዩ እያሉ መንፈስ ቅዱስ፣ ‹‹የጠራኋቸውን ሥራ እንዲሠሩ በርናባስንና ሳውልን ለዩልኝ›› አላቸው፡፡ ስለዚህ በአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለበርናባስና ለሳውል ጸለዩላቸው፣ እጆቻቸውንም ጫኑባቸው፡፡ ከዚያም በሌሎች ብዙ ቦታዎች ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች እንዲሰብኩ ላኩአቸው፡፡ በርባናስና ሳውል ከተለያዩ የሕዝብ ወገኖች የሆኑ ሰዎችን አስተማሩ፣ ብዙ ሰዎችም በኢየሱስ አመኑ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሐዋርያት ሥራ 8፡3፤ 9፡1-31፤ 11፡19-26፤ 13፡1-3፡፡___

60
content/47.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,60 @@
# 47. ጳውሎስና ሲላስ በፊልጵስዩስ #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-01.jpg)
ሳውል በሮማ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሁሉ በሚጓዝበት ጊዜ፣ ሮማዊ ስሙን ‹‹ጳውሎስ››ን መጠቀም ጀመረ፡፡ አንድ ቀን ጳውሎስና ጓደኛው ሲላስ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች ሊያውጁ ወደ ፊልጵስዩስ ከተማ ሄዱ፡፡ ሰዎች ሊጸልዩ ወደ ተሰበሰቡበት ከከተማይቱ ውጭ በወንዙ አጠገብ ወዳለ ስፍራ ሄዱ፡፡ በዚያ ነጋዴ የነበረች ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት አገኙ፡፡ እርስዋ እግዚአብሔርን ትወድና ታመልክ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-02.jpg)
ስለ ኢየሱስ የሚነገረውን መልእክት እንድታምን እግዚአብሔር የልድያን ልብ ከፈተላት፤ እርስዋና ቤተ ሰብዋ ተጠመቁ፣ በቤትዋ እንዲኖሩ ጳውሎስንና ሲላስን ጋበዘቻቸው፣ ስለዚህ እነርሱ ከእርስዋና ከቤተ ሰብዋ ጋር ኖሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-03.jpg)
ጳውሎስና ሲላስ ብዙ ጊዜ በጸሎት ስፍራ ከሰዎች ጋር ይገናኙ ነበር፡፡ በየዕለቱ ወደዚያ ሲሄዱ ጋኔን የያዛት አንዲት ባሪያ ልጃገረድ ትከተላቸው ነበር፡፡ እርሷም በዚህ ጋኔን አማካይነት ስለ መጪው ጊዜ ለሰዎች ትተነብይላቸው ነበር፣ ስለዚህ በጥንቈላ ለጌቶችዋ ብዙ ገንዘብ ታስገኝ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-04.jpg)
ባሪያዪቱ ልጃገረድ እነርሱ ሲዘዋወሩ እየተከተለቻቸው፣ ‹‹እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፡፡ የመዳንን መንገድ ይነግሩአችኋል! በማለት መጮህዋን ቀጠለች፡፡ ጳውሎስ እስኪቈጣ ድረስ ይህንን ደጋግማ አደረገች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-05.jpg)
በመጨረሻም አንድ ቀን ባሪያዪቱ ልጃገረድ መጮኽ በጀመረች ጊዜ ጳውሎስ ወደ እርስዋ ዘወር አለና በእርስዋ የነበረውን ጋኔን፣ ‹‹በኢየሱስ ስም፣ ከእርስዋ ውጣ›› አለው፡፡ ወዲያውኑ ጋኔኑ ለቀቃት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-06.jpg)
የባሪያዪቱ ልጃገረድ ጌቶች የነበሩት ሰዎች በጣም ተቈጡ! ያለ ጋኔኑ ባሪያዪቱ ልጅ ስለ ሰዎች መጪ ጊዜ መናገር እንደማትችል ዐወቁ፡፡ ይህም ሰዎች የሚደርስባቸውን ነገር ትነግራቸው ዘንድ ስለማትችል ለጌቶችዋ ገንዘብ አይከፍሉም ማለት ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-07.jpg)
ስለዚህ የባሪያዪቱ ልጃገረድ ጌቶች ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ሮማ ባለ ሥልጣናት ወሰዱአቸው፣ እነርሱም ደብድበው ወደ እስር ቤት ጣሉአቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-08.jpg)
እነርሱም ጳውሎስንና ሲላስን በእስር ቤት ውስጠኛ ክፍል አሰሩአቸው እግሮቻቸውን እንኳ ከግንድ ጋር አሰሩአቸው፡፡ ሆኖም ግን እከለ ሌሊት ላይ ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘመሩ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-09.jpg)
በድንገት ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ! የእስር ቤቱ በሮች ሁሉ ወለል ብለው ተከፈቱ፣ የእስረኞቹ ሁሉ ሰንሰለቶችም ረገፉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-10.jpg)
የእስር ቤቱ ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቃ፣ የእስር ቤቱ በሮች ሁሉ መከፈታቸውን ባየ ጊዜ ፈራ! እስረኞቹ ሁሉ ያመለጡ መሰለው፣ ስለዚህ ራሱን ለመግደል ዐሰበ፡፡ (እስረኞቹ እንዲያመልጡ ካደረገ የሮማ ባለ ሥልጣናት እንደሚገድሉት ዐወቀ፡፡) ነገር ግን ጳውሎስ ዐየውና፣ ‹‹ተው! ራስህን አትጕዳ፡፡ ሁላችንም እዚህ አለን›› ብሎ ጮኸበት፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-11.jpg)
የእስር ቤቱ ጠባቂ ወደ ጳውሎስና ሲላስ እየመጣ እያለ ተንቀጠቀጠና፣ ‹‹እድን ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀ፡፡ ጳውሎስ፣ ‹‹በጌታ በኢየሱስ እመን፣ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ›› ብሎ መለሰለት፡፡ ከዚያም የእስር ቤት ጠባቂው ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ቤቱ ወሰዳቸውና ቊስላቸውን አጠበላቸው፡፡ ጳውሎስ በቤቱ ለነበሩት ሁሉ ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች ሰበከላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-12.jpg)
የእስር ቤት ጠባቂውና መላው ቤተ ሰቡ በኢየሱስ አምነው ተጠመቁ፡፡ ከዚያም የእስር ቤት ጠባቂው ለጳውሎስና ለሲላስ ምግብ አቀረበላቸውና በአንድነት ደስ አላቸው፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-13.jpg)
በማግስቱ የፊልጵስዩስ መሪዎች ጳውሎስና ሲላስን ከእስር ቤት ፈቱአቸውና ከፊልጵስዩስ እንዲሄዱ ጠየቁአቸው፡፡ ጳውሎስና ሲላስ ልድያንና አንዳንድ ሌሎች ወዳጆችን ጐበኙና ከተማይቱን ለቀው ሄዱ፡፡ ስለ ኢየሱስ የሚናገረው የምሥራች መስፋፋቱን ቀጠለ ቤተ ክርስቲያንም ማደግዋን ቀጠለች፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-47-14.jpg)
ጳውሎስና ሌሎች ክርስቲያን መሪዎች ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች እየሰበኩና እያስተማሩ ወደ ብዙ ከተሞች ተጓዙ፡፡ ደግሞም በአብያተ ክርስቲያናቱ ላሉ አማኞች ሊያበረታቱአቸውና ሊያስተምሩአቸው ብዙ መልእክቶችን ጻፉላቸው፡፡ ከእነዚህ መልእክቶች አንዳንዶቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ያሉት መጻሕፍት ሆኑ፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሐዋርያት ሥራ 16፡11-40፡፡___

60
content/48.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,60 @@
# 48. ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠው መሲሕ ነው #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-01.jpg)
እግዚአብሔር ዓለምን በፈጠረ ጊዜ ሁሉም ነገር ፍጹም ነበረ፡፡ ኃጢአት አልነበረም፡፡ አዳምና ሔዋን እርስ በርሳቸው ይዋደዱ ነበር፣ እግዚአብሔርንም ይወዱት ነበር፡፡ በሽታ ወይም ሞት አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር ዓለም እንድትሆን የፈለገው እንደዚህ ነበር፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-02.jpg)
ሰይጣን በገነት ሔዋንን ያስት ዘንድ በእባቡ በኩል ተናገረ፡፡ ከዚያ በኋላ እርስዋና አዳም በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠሩ፡፡ እነርሱ ኃጢአት በመሥራታቸው ምክንያት በምድር ያለ ሰው ሁሉ ይታመማል ይሞታልም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-03.jpg)
አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራታቸው ምክንያት ከዚያም የበለጠ መጥፎ ነገር እንኳ ሆነ፡፡ እነርሱ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆኑ፡፡ ከዚህ የተነሣ ከዚያን ጊዜ አነሥቶ ሁሉም ሰው በኃጢአት ባሕርይ ተወልዶአል ደግሞም የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል፡፡ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የነበረው ግንኙነት በኃጢአት ተቋረጠ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ያንን ግንኙነት የመመለስ ዕቅድ ነበረው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-04.jpg)
ከሔዋን ዝርያዎች አንዱ የሰይጣንን ራስ እንደሚቀጠቅጥ፣ ሰይጣንም ሰኰናውን እንዲያቈስል እግዚአብሔር ተስፋ ሰጠ፡፡ ይህም ሰይጣን መሲሑን ይገድላል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ገና ያስነሣዋል ማለት ነው፣ ከዚያም መሲሑ የሰይጣንን ኃይል ለዘላለም ይቀጠቅጠዋል፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር መሲሑ ኢየሱስ መሆኑን ገለጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-05.jpg)
እግዚአብሔር ምድርን ሁሉ በጥፋት ውሃ ባጠፋ ጊዜ፣ በእርሱ ያመኑትን ሰዎች ለማዳን መርከብ አቀረበ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ሰው ሁሉ በኃጢአቱ ምክንያት መጥፋት ይገባው ነበር፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ለማዳን ኢየሱስን ሰጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-06.jpg)
ለብዙ መቶ ዓመታት ካህናት ለኃጢአታቸው የሚገባቸውን ቅጣት ለማሳየት ስለ ሕዝቡ ያለ ማቋረጥ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡ ነገር ግን እነዚያ መሥዋዕቶች ኃጢአታቸውን ሊያስወግዱ አልቻሉም፡፡ ኢየሱስ ታላቁ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ከሌሎች ካህናት በተለየ ሁኔታ ራሱን በዓለም ላይ ያሉ ሰዎችን ሁሉ ኃጢአት ማስወገድ የሚችል ብቸኛ መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፡፡ ኢየሱስ ማንኛውም ሰው የሠራውን የእያንዳንዱን ኃጢአት ቅጣት ስለ ወሰደ ፍጹም ሊቀ ካህናት ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-07.jpg)
እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ‹‹የምድር ሕዝብ ወገኖች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ›› ብሎ ነገረው፡፡ ኢየሱስ ከአብርሃም ትውልድ ነው፡፡ በእርሱ በኩል የሕዝብ ወገኖች ሁሉ ተባርከዋል፣ ምክንያቱም በኢየሱስ የሚያምን እያንዳንዱ ሰው ከኃጢአት ድኖአል፣ እንዲሁም የአብርሃም መንፈሳዊ ትውልድ ይሆናል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-08.jpg)
ልጁን ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብ እግዚአብሔር ለአብርሃም በነገረው ጊዜ፣ እግዚአብሔር በልጁ በይስሐቅ ፈንታ የመሥዋዕት በግ አቀረበ፡፡ ሁላችንም በኃጢአታችን መሞት ይገባናል! ነገር ግን እግዚአብሔር መሥዋዕት ሆኖ በእኛ ቦታ እንዲሞት የእግዚአብሔር በግ የሆነውን ኢየሱስን ሰጠ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-09.jpg)
እግዚአብሔር በግብፅ ላይ የመጨረሻውን መቅሠፍት በላከ ጊዜ እንከን የሌለበት ጥቦት እንዲያርዱና ደሙን በበሩ መቃንና ጉበን ላይ እንዲረጩት ለእስራኤላውያን ቤተ ሰቦች ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር ደሙን ባየ ጊዜ ቤቶቹን አልፎ ሄደ በኵር ልጆቻቸውንም አልገደለም፡፡ ይህ ታሪካዊ ድርጊት ፋሲካ ተብሎአል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-10.jpg)
ኢየሱስ የፋሲካ በጋችን ነው፡፡ እርሱ ፍጹምና ያለ ኃጢአት ነው በፋሲካ በዓል ጊዜም ተገደለ፡፡ ማንኛውም ሰው በኢየሱስ በሚያምንበት ጊዜ፣ የኢየሱስ ደም ለዚያ ሰው ኃጢአት ክፍያ ነው፣ የእግዚአብሔር ቅጣትም በዚያ ሰው ላይ ያልፋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-11.jpg)
እግዚአብሔር የተመረጡ ሕዝቡ ከነበሩት ከእስራኤላውያን ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ነገር ግን አሁን እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው የሚሆን ዐዲስ ቃል ኪዳን አድርጎአል፡፡ በዚህ ዐዲስ ቃል ኪዳን ምክንያት ከማንም ሕዝብ ወገን የሆነ ማንኛውም ሰው በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ሕዝብ ወገን መሆን ይችላል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-12.jpg)
ሙሴ የእግዚአብሔርን ቃል ያወጀ ታላቅ ነቢይ ነበረ፡፡ ኢየሱስ ግን ከሁሉም የላቀ ነቢይ ነው፡፡ እርሱ አምላክ ነው፣ ስለዚህ እርሱ ያደረገውና የተናገረው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ሥራና ቃል ነው፡፡ ስለዚህ ነው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ የሚጠራው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-13.jpg)
ከዝርያዎቹ አንዱ ንጉሥ ሆኖ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ለዘላለም እንደሚገዛ እግዚአብሔር ለንጉሥ ዳዊት ተስፋ ሰጠው፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅና መሲሑ ስለሆነ፣ ለዘላለም መግዛት የሚችል ያ ልዩ የዳዊት ዘር ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-48-14.jpg)
ዳዊት የእስራኤል ንጉሥ ነበር፣ ኢየሱስ ግን የፍጥረት ዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው! ተመልሶ ይመጣና በፍትሕና በሰላም መንግሥቱን ለዘላለም ይገዛል፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከዘፍጥረት 1-3፤ 6፤ 14፤ 22፤ ዘጸአት 12፣ 20፤ 2ኛ ሳሙኤል 7፤ ዕብራውያን 3፡1-6፤ 4፡14-5፡10፤ 7፡1-8፡13፤ 9፡11-10፡18፤ ራእይ 21፡፡___

76
content/49.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,76 @@
# 49. ዐዲሱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-01.jpg)
አንድ መልአክ ማርያም ለተባለች ድንግል የእግዚአብሔርን ልጅ እንደምትወልድ ነገራት፡፡ ስለዚህ እርስዋ ገና ድንግል እያለች ወንድ ልጅ ወለደችና ኢየሱስ ብላ ሰየመችው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ አምላክም ሰውም ነው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-02.jpg)
ኢየሱስ አምላክ መሆኑን የሚያረጋግጡ ብዙ ተአምራትን አደረገ፡፡ በውሃ ላይ ተራመደ፣ ማዕበልን ጸጥ አደረገ፣ ብዙ በሽተኞችን ፈወሰ፣ አጋንንትን አወጣ፣ ሙታንን አስነሣ፣ እንዲሁም አምስት እንጀራና ሁለት ትንንሽ ዓሣ ከ5,000 ለበለጡ ሰዎች እንዲበቃ አደረገ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-03.jpg)
ደግሞም ኢየሱስ ታላቅ መምህር ነው፣ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነም በሥልጣን ተናገረ፡፡ ራሳችሁን እንደምትወዱ ሌሎችን ሰዎችንም ውደዱ ብሎ አስተማረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-04.jpg)
ደግሞም እርሱ ሀብታችሁን ጨምሮ ማንኛውንም ነገር እንደምትወዱ እግዚአብሔርን መውደድ አለባችሁ ብሎ አስተማረ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-05.jpg)
ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥት በዓለም ካለ ከማንኛውም ነገር ይልቅ የከበረች ነች አለ፡፡ ለማንኛውም ሰው እጅግ በጣም አስፈላጊው ነገር የእግዚአብሔር መንግሥት ወገን መሆን ነው፡፡ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት ከኃጢአታችሁ መዳን አለባችሁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-06.jpg)
ኢየሱስ አንዳንድ ሰዎች ተቀብለውት እንደሚድኑ፣ ሌሎች ግን እንደማይቀበሉት አስተማረ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንደ መልካም መሬት ናቸው አለ፡፡ የኢየሱስን የምሥራች ተቀብለው ይድናሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች የእግዚአብሔር ቃል ዘር እንደማይገባበትና ምንም ፍሬ እንደማያፈራ በመንገድ ዳር እንዳለ አለትማ መሬት ናቸው፡፡ እነዚያ ሰዎች ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን መልእክት የማይቀበሉና ወደ መንግሥቱ የማይገቡ ናቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-07.jpg)
ኢየሱስ፣ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን በጣም እንደሚወድ አስተማረ፡፡ ይቅር ሊላቸውና ልጆቹ ሊያደርጋቸው ይፈልጋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-08.jpg)
ደግሞም ኢየሱስ እግዚአብሔር ኃጢአትን እንደሚጠላ ነግሮናል፡፡ አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ፣ ኃጢአቱ ዝርያዎቻቸውን ሁሉ ጐዳ፡፡ ከዚህ የተነሣ በዓለም ያለ ሁሉም ሰው ኃጢአት ይሠራል ከእግዚአብሔርም ይለያያል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-09.jpg)
ነገር ግን በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-10.jpg)
በኃጢአታችሁ ምክንያት በደለኞች ናችሁና መሞት ይገባችኋል፡፡ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ መቈጣት ነበረበት፣ ነገር ግን ቊጣውን በእናንተ ላይ በማፍስስ ፈንታ በኢየሱስ ላይ አፈሰሰው፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ፣ የእናንተን ቅጣት ተቀበለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-11.jpg)
ኢየሱስ ከቶ ኃጢአት አላደረገም፣ ነገር ግን የእናንተን ኃጢአትና በዓለም ያለውን የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአት ለማስወገድ መቀጣትንና ፍጹም መሥዋዕት ሆኖ መሞትን መረጠ፡፡ ኢየሱስ ራሱን ስለ ሠዋ፣ እግዚአብሔር ማንኛውንም ኃጢአት፣ አስከፊ የሆነውን ኃጢአት እንኳ ይቅር ማለት ይችላል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-12.jpg)
መልካም ሥራዎች ሊያድኑአችሁ አይችሉም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖራችሁ ልታደርጉ የምትችሉት ምንም ነገር የለም፡፡ ኢየሱስ ብቻ ኃጢአታችሁን ሊያጥብ ይችላል፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን፣ በእናንተ ፈንታ በመስቀል ላይ መሞቱን እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው ብቻ ማመን አለባችሁ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-13.jpg)
እግዚአብሔር በኢየሱስ የሚያምነውንና ጌታው አድርጎ የሚቀበለውን ማንኛውንም ሰው ያድናል፡፡ ባለ ጠጎች ሆኑ ወይም ድሆች፣ ወንድ ወይም ሴት፣ ሽማግሌ ወይም ወጣት፣ ወይም የትም ብትኖሩ ምንም አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የቅርብ ግንኙነት ሊኖረው ይችል ዘንድ ይወዳችኋል በኢየሱስ እንድታምኑም ይፈልጋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-14.jpg)
ኢየሱስ እንድታምኑና እንድትጠመቁ ይጋብዛችኋል፡፡ ኢየሱስ መሲሕ፣ ብቸኛው የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ታምናላችሁ? ኃጢአተኞች መሆናችሁንና እግዚአብሔር ቢቀጣችሁ የተገባ መሆኑን ታምናላችሁ? ኢየሱስ ኃጢአታችሁን ለማስወገድ በመስቀል ላይ መሞቱን ታምናላችሁ?
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-15.jpg)
በኢየሱስና እርሱ ለእናንተ በሠራው ሥራ ብታምኑ፣ እናንተ ክርስቲያኖች ናችሁ! እግዚአብሔር ከሰይጣንና ከጨለማ መንግሥት አውጥቶአችሁ በእግዚአብሔር የብርሃን መንግሥት ውስጥ አድርጎአችኋል፡፡ እግዚአብሔር ነገሮችን የምታደርጉበትን አሮጌውንና ኃጢአተኛውን መንገዳችሁን አስወግዶ ዐዲስና ጻድቅ የሆነ የአደራረግ መንገድ ሰጥቶአችኋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-16.jpg)
እናንተ ክርስቲያኖች ናችሁ፣ ኢየሱስ በሠራው ሥራ ምክንያት እግዚአብሔር ኃጢአታችሁን ይቅር ብሎአችኋል፡፡ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶች ፈንታ የቅርብ ወዳጆች አድርጎ ይቈጥራችኋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-17.jpg)
የእግዚአብሔር ወዳጆችና የጌታ ኢየሱስ አገልጋዮች ከሆናችሁ፣ ኢየሱስ ለሚያስተምራችሁ ነገር ትታዘዛላችሁ፡፡ ክርስቲያኖች ብትሆኑም እንኳ፣ አሁንም ኃጢአት ለመሥራት ትፈተናላችሁ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የታመነ ነውና ኃጢአታችሁን ብትናዘዙ ይቅር እላችኋለሁ ይላል፡፡ ኃጢአትን የምትቃወሙበትን ብርታት ይሰጣችኋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-49-18.jpg)
እግዚአብሔር እንድትጸልዩ፣ ቃሉን እንድታጠኑ፣ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር እንድታመልኩ፣ ያደረገላችሁንም ለሌሎች እንድትነግሩ ይጠይቃችኋል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ከእርሱ ጋር የጠለቀ ግንኙነት እንዲኖራችሁ ይረዱአችኋል፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከሮሜ 3፡21-26፤ 5፡1-11፤ ዮሐንስ 3፡16፤ ማርቆስ 16፡16፤ ቈላስይስ 1፡13-14፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17-21፤ 1ኛ ዮሐንስ 1፡5-10፡፡___

72
content/50.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,72 @@
# 50. ኢየሱስ ይመለሳል #
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-01.jpg)
ለ2,000 ዓመታት ያህል በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሰዎች ስለ መሲሑ ኢየሱስ የሚናገረውን የምሥራች እየሰሙ ቈይተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን እያደገች ኖራለች፡፡ ኢየሱስ በዓም ፍጻሜ እንደሚመለስ ተስፋ ሰጥቶአል፡፡ እርሱ ገና ባይመለስም እንኳ፣ ተስፋውን ይጠብቃል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-02.jpg)
የኢየሱስን መመለስ እየተጠባበቅን እያለን፣ እግዚአብሔር ቅዱስ በሆነና እርሱን በሚያስከብረው መንገድ እንድንኖር ይፈልጋል፡፡ ደግሞም ስለ መንግሥቱ ለሌሎች እንድንናገር ይፈልጋል፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ ይኖር በነበረበት ጊዜ፣ ‹‹ደቀ መዛሙርቴ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የሚናገረውን የምሥራች በዓለም በሁሉም ስፍራ ላሉ ሰዎች ይሰብካሉ፣ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል›› አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-03.jpg)
ብዙ የሕዝብ ወገኖች አሁንም ስለ ኢየሱስ አልሰሙም፡፡ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት፣ የምሥራቹን ከቶ ላልሰሙት ሰዎች እንዲያውጁ ለክርስቲያኖች ነገራቸው፡፡ ‹‹ሂዱና የሕዝብ ወገኖችን ሁሉ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው! ‹‹መከሩም ደርሶአል! አለ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-04.jpg)
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ ‹‹አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም፡፡ ልክ የዚህ ዓለም ባለ ሥልጣናት እኔን እንደ ጠሉኝ፣ በእኔ ምክንያት ያሠቃዩአችሁና ይገድሉአችኋል፡፡ ምንም እንኳ በዚህ ዓለም መከራ ብትቀበሉም፣ አይዞአችሁ ምክንያቱም እኔ ይህን ዓለም የሚገዛውን ሰይጣንን አሸንፌዋለሁ፡፡ እናንተ በእኔ አምናችሁ እስከ መጨረሻ ብትጸኑ፣ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ያድናችኋል!
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-05.jpg)
ኢየሱስ የዓለም ፍጻሜ በሚሆንበት ጊዜ፣ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ነገር ለማብራራት ለደቀ መዛሙርቱ አንድ ታሪክ ነገራቸው፡፡ አንድ ሰው በእርሻው መልካም ዘርን ዘራ፡፡ ተኝቶ እያለ ጠላቱ መጣና በስንዴው ላይ የአረም ዘር ዘራበትና ሄደ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-06.jpg)
‹‹የተዘራው ስንዴ በበቀለ ጊዜ፣ የሰውዬው አገልጋዮች፣ ‹ጌታው፣ በዚያ እርሻ መልካም ዘር ዘርተህ ነበር፡፡ ታዲያ በውስጡ ለምንድን ነው አረም ያለበት? ብለው ጠየቁት፣ጌታውም፣ ‹የዘራው ጠላት መሆን አለበት››› ብሎ መለሰላቸው፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-07.jpg)
‹‹አገልጋዮቹ ለጌታቸው፣ ‹አረሙን እንንቀለውን? ብለው መለሱለት፡፡ ጌታቸው እንዲህ አለ፣ ‹አይደለም፡፡ ይህንን ብታደርጉ ስንዴውንም ትነቅሉታላችሁ፡፡ እስከ መከር ድረስ ቆዩና አረሙን ሰብስባችሁ አቃጥሉት፣ ስንዴውን ግን በጎተራዬ አከማቹት፡፡›››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-08.jpg)
ደቀ መዛሙርቱ የታሪኩ ትርጕም አልገባቸውም፣ ስለዚህ እንዲያብራራላቸው ኢየሱስን ጠየቁት፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ ‹‹መልካሙን ዘር የዘራው ሰው መሲሑን ይወክላል፡፡ እርሻው ዓለምን ይወክላል፡፡ መልካሙ ዘር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሰዎች ይወክላል፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-09.jpg)
‹‹አረሙ ከክፉው ወገን የሆኑ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አረሙን የዘራው ጠላት ዲያብሎስን ይወክላል፡፡ መከሩ የዓለምን ፍጻሜ ይወክላል፣ አጫጆቹም የእግዚአብሔርን መላእክት ይወክላሉ፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-10.jpg)
‹‹በዓለም ፍጻሜ፣ መላእክት የዲያብሎስ ወገኖች የሆኑ ሰዎችን ሁሉ በአንድ ላይ ይሰበስቡና ወደሚንቀለቀል እሳት ይጥሉአቸዋል፣ በዚያም ይጮኻሉ አስከፊ በሆነ ሥቃይም ጥርሶቻቸውን ያፋጫሉ፡፡ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ፡፡››
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-11.jpg)
ደግሞም ኢየሱስ ልክ ከዓለም ፍጻሜ በፊት ወደ ምድር እንደሚመለስ ተናገረ፡፡ በሄደበት አኳኋን ተመልሶ ይመጣል፣ ይኸውም፣ አካላዊ ሰውነት ይኖረዋል፣ በሰማይ ደመናም ይመጣል፡፡ ኢየሱስ በሚመለስበት ጊዜ እያንዳንዱ የሞተ ክርስቲያን ከሙታን ይነሣና በሰማይ ይገናኘዋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-12.jpg)
በዚያን ጊዜ ገና በሕይወት ያሉ ክርስቲያኖች ወደ ሰማይ ይነጠቁና ከሙታን ከተነሡ ሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ይቀላቀላሉ፡፡ በዚያ ሁላቸውም ከኢየሱስ ጋር ይሆናሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከሕዝቡ ጋር ፍጹም በሆነ ሰላምና አንድነት ለዘላለም ይኖራል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-13.jpg)
ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ዘውድ ለመስጠት ተስፋ ሰጥቶአል፡፡ እነርሱ ፍጹም በሆነ ሰላም ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ይኖራሉ ይነግሣሉም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-14.jpg)
ነገር ግን እግዚአብሔር በኢየሱስ በማያምኑ ሁሉ ላይ ይፈርዳል፡፡ ለዘላለም ወደሚያለቅሱበትና በሥቃይ ጥርሶቻቸውን ወደሚያፏጩበት ወደ ሲኦል ይጥላቸዋል፡፡ ከቶ የማይጠፋ እሳት ባለማቋረጥ ያቃጥላቸዋል፣ ትሎችም እነርሱን መብላታቸውን በጭራሽ አያቋርጡም፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-15.jpg)
ኢየሱስ በሚመለሰበት ጊዜ፣ ሰይጣንና መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ ያጠፋቸዋል፡፡ ሰይጣንን ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ እርሱን ለመከተል ከመረጡት ሁሉ ጋር ለዘላለም ወደሚቃጠሉበት ወደ ሲኦል ይጥለዋል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-16.jpg)
አዳምና ሔዋን ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙና ኃጢአትን ወደዚህ ዓለም ስላመጡ፣ እግዚአብሔር ዓለምን ረገማት ሊያጠፋትም ወሰነ፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን እግዚአብሔር ፍጹም የሚሆን ዐዲስ ሰማይና ዐዲስ ምድር ይፈጥራል፡፡
![Image](https://cdn.door43.org/obs/jpg/360px/obs-en-50-17.jpg)
ኢየሱስና ሕዝቡ በዐዲሲቱ ምድር ይኖራሉ፣ ባለው ሁሉ ነገር ላይ ለዘላለም ይነግሣሉ፡፡ እርሱ እንባን ሁሉ ያብሳል፣ ከእንግዲህ ሥቃይ፣ ሐዘን፣ ልቅሶ፣ ክፋት፣ ሕመም፣ ወይም ሞት አይኖርም፡፡ ኢየሱስ መንግሥቱን በሰላምና በፍትሕ ይገዛል፣ ለዘላለምም ከሕዝቡ ጋር ይሆናል፡፡
___የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ፡- ከማቴዎስ 24፡14፤ 28፡18፤ ዮሐንስ 15፡20፤ 16፡33፤ ራእይ 2፡10፤ ማቴዎስ 13፡24-30፤ 36-42፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡13-5፡11፤ ያዕቆብ 1፡12፤ ማቴዎስ 22፡13፤ ራእይ 20፡10፤ 21፡1-22፡21፡፡___

11
content/back/intro.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,11 @@
### ተሳተፍ! ###
ይህ ሥዕላዊ አነስተኛ መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም የዓለም ቋንቋዎች እንዲገኝ ለማድረግ እንፈልጋለን፣ አንተም መርዳት ትችላለህ! ይህ የማይቻል አይደለም፤ መላው የክርስቶስ አካል ይህን ጽሑፍ ለመተርጐምና ለማሠራጨት አብሮ ሊሠራ ይችላል ብለን እናስባለን፡፡
### በነጻ ለሌሎች አካፍል ###
በተቻለ መጠን ያለ ገደብ የዚህን መጽሐፍ ብዙ ቅጂዎች እንደፈለግኸው ስጥ፡፡ በቊጥር የሚሠሩ /ዲጂታል/ እትሞች ሁሉ በዓምደ መረብ /ኢንተርኔት/ በነጻ ይገኛሉ፣ እየተጠቀምንበት ባለው ግልጽ ፈቃድ ምክንያትም ያለ አበል ክፍያ በማንኛውም የዓለም ክፍል በንግድ መስክ ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ዳግም ማሳተም እንኳ ትችላለህ! በተጨማሪ በ [http://openbiblestories.com](http://openbiblestories.com) ፈልግ፡፡
### አስፋፋ! ###
ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን በቪዲዮና በሞባይል ስልክ አጠቃቀም በ[http://openbiblestories.com](http://openbiblestories.com) በሌሎች ቋንቋዎች አግኝ፡፡ በድረ ገጽ፣ ግለጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ወደ ቋንቋህ ለመተርጐም እርዳታ ማግኘት ደግሞ ትችላለህ፡፡

32
content/front/intro.md Normal file
View File

@ -0,0 +1,32 @@
የተገለጠ ቃል/ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች
ያልተገደበ፣ ሥዕላዊ አነስተኛ መጽሐፍ ቅዱስ በማንኛውም ቋንቋ
[http://openbiblestories.com](http://openbiblestories.com)
ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፣ አማርኛ፣ እትም
በዲስታንት ሾርስ ሚዲያ የተዘጋጀ ([http://distantshores.org](http://distantshores.org)) እና ዘ ዶር43 ወርልድ ሚሽንስ ኮምዩኒቲ ([http://door43.org](http://door43.org)).
__ፈቃድ፡- __
ይህ ሥራ ከ a Creative Commons Atribution ShareAlike 4.0 International License ሥር እንዲገኝ ተደርጎአል ([http://creativecommons.org/licenses/by-sa/4.0/](http://creativecommons.org/licenses/by-sa/4.0/)).
የሚከተሉትን ለማድረግ ነጻነት አለህ፡-
* <font inherit/inherit;;inherit;;inherit>__ ለሌሎች ለማካፍል __ - መጽሐፉን አባዝተህ</font> በማንኛውም<font inherit/inherit;;inherit;;inherit>መገናኛ ዘዴ ወይም ይዞታና አቀራረብ እንደገና ማሠራጨት፡፡</font>
* <font inherit/inherit;;inherit;;inherit>__ ለሁኔታ እንዲስማማ አድርገህ ማቅረብ __ - መጽሐፉን ለማንኛውም ዓላማ፣ ለንግድ እንኳ እንደ ገና መቀየር፣ መቀየር፣ ማዳበር፡፡</font>
በሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሠረት፡-
* <font inherit/inherit;;inherit;;inherit>የሥራው ባለቤትነት - የሥራውን ባለቤት እንደሚከተለው ግለጽ፡- ‹‹የመጀመሪያው</font> ሥራ<font inherit/inherit;;inherit;;inherit>በ http://openbiblestories.com ይገኛል፡፡ ሥራው የተገኘባቸው የሥራው ባለቤትነት መግለጫዎች</font> በማንኛውም<font inherit/inherit;;inherit;;inherit>መንገድ እኛ አንተን የደገፍንህ መሆናችንን ወይም የዚህን</font> መጽሐፍ<font inherit/inherit;;inherit;;inherit>አጠቃቀምህን የሚመለከት ዐሳብ የሚገልጽ መሆን የለበትም፡፡</font>
[*](http://openbiblestories.com.)<font inherit/inherit;;inherit;;inherit>ለሌሎች እኩል አካፍል - መጽሐፉን እንደገና ብትቀላቅለው፣ ብትቀይረው፣ ወይም ብታዳብረው፣ በመጀመሪያው ፈቃድ ሥር እንዳለው ጽሑፍህን ማሠራጨት አለብህ፡፡</font>
የንግድ ምልክቶች አጠቃቀም፡- የተገለጠ ቃል የዲስታንት ሾርስ ሚዲያ የንግድ ምልክት ነውና ከዚህ በፊት በተዘጋጁ በማናቸውም የሥራዎቹ መገኛዎች ላይ ላይካተቱ ይችላሉ፡፡ ከ [http://openbiblestories.com](http://openbiblestories.com) የሆነው ያልተለወጠው ይዘት ለሌች በሚሠራጭበት ጊዜ የተገለጠው ቃል ዓርማን ማካተት አለበት፡፡ ነገር ግን በማንኛውም መንገድ ይዘቱን ብትለውጥ ሥራህን ከማሠራጨትህ በፊት የተገለጠውን ቃል ዓርማ ማስወገድ አለብህ፡፡
የሥዕል ሥራ ባለቤትነት፡- በእነዚህ ታሪኮች ጥቅም ላይ የዋሉ ሥሎች ሁሉ የ © Sweet publishing ([www.sweetpublishing.com](http://www.sweetpublishing.com)) ሲሆኑ በክርኤቲቭ ኮመንስ አትሪቡሽን ሼር አላይክ ላይሰንስ ሥር እንዲገኙ ተደርገዋል ([http://creativecommons.org/licenses/by-sa/3.0](http://creativecommons.org/licenses/by-sa/3.0)).
በመላው ዓለም ላሉ በክርስቶስ ወንድሞቻችንና እኅቶቻቸን - ዓለም አቀፋዊቱ ቤተ ክርስቲያን፡፡ እግዚአብሔር ይህን የቃሉን ሥዕላዊ አጭር መግለጫ እናንተን ለመባረክ፣ ለማጠንከርና ለማበርታት ይጠቀምበት ዘንድ ጸሎታችን ነው፡፡

43
manifest.yaml Normal file
View File

@ -0,0 +1,43 @@
checking:
checking_entity:
- ''
checking_level: ''
dublin_core:
conformsto: rc0.2
contributor:
- Distant Shores Media
- Door43 World Missions Community
creator: Distant Shores Media
description: 50 key stories of the Bible, from Creation to Revelation, for evangelism
& discipleship, in text, audio, and video, on any mobile phone, in any language,
for free. It increases understanding of the historical and redemptive narrative
of the entire Bible.
format: text/markdown
identifier: obs
issued: ''
language:
direction: ltr
identifier: ''
title: Oromo, West Central
modified: '2017-09-06'
publisher: unfoldingWord
relation:
- en/tw
- en/obs-tq
- en/obs-tn
rights: CC BY-SA 4.0
source:
- identifier: obs
language: en
version: ''
subject: Bible stories
title: ''
type: book
version: ''
projects:
- categories: []
identifier: obs
path: ./content
sort: 0
title: ''
versification: ufw