1584 lines
211 KiB
Plaintext
1584 lines
211 KiB
Plaintext
\id 1KI
|
|
\ide UTF-8
|
|
\h 1ኛ ነገስት
|
|
\toc1 1ኛ ነገስት
|
|
\toc2 1ኛ ነገስት
|
|
\toc3 1ki
|
|
\mt 1ኛ ነገስት
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 1
|
|
\p
|
|
\v 1 ንጉስ ዳዊትም ሸምግሎ እና እድሜውም ገፍቶ ነበር። ምንም እንካ ልብስ ቢድርቡለትም፣ ሊያሞቀው አልቻለም።
|
|
\v 2 ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ "ለንጉስ አንዲት ወጣት ልጃገረድ እንፈልግለት እና ታገልግለው ትንከባከበውም። ንጉሱም እንዲሞቀው ክንዱ ውስጥ ትተኛ፣' አሉት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ስለዚህም አንዲት ቆንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፈለጉ። ሱነማዊቱን አቢሳን አገኙ፤ ወደ ንጉሡም አመጡአት።
|
|
\v 4 እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች፤ እርስዋም ንጉሡን አገለገለችው፣ ተንከባከበችውም፤ ነገር ግን ንጉሡ ከእርስዋ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አላደረገም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 በዚያን ጊዜ የአጊት ልጅ አዶንያስ “ንጉሥ እሆናለሁ” በማለት ራሱን ከፍ አደረገ። ስለዚህ በፊቱ የሚሮጡ ሃምሳ ፈረሰኞችንና ሠረገሎችን ለራሱ አዘጋጀ።
|
|
\v 6 አባቱም ይህን ወይም ያንን ለምን ታደርጋለህ ብሎ ገስጾት አያውቅም ነበር። አዶንያስም ከአቤሴሎም በኋላ የተወለደ፣ እጅግ መልከ መልካም ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 እርሱም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሤረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ረዱት።
|
|
\v 8 ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ነቢዩ ናታን፣ ሳሚ፣ ሬሲምና ዳዊትን የሚደግፉ ኃያላን አዶንያስን አልተከተሉትም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 አዶንያስም ዓይንሮጌል አቅራቢያ ባለው በዞሔሌት ድንጋይ ላይ በጎችን፣ በሬዎችንና የሰቡ ወይፈኖችን ሠዋ። እርሱም፣ የንጉሡን ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፣ የይሁዳን ሰዎች ሁሉና የንጉሡን አገልጋዮች ጋበዛቸው።
|
|
\v 10 ነገር ግን ነቢዩ ናታንን፣ በናያስን፣ ኃያላን ሰዎችን፣ ወይም ወንድሙን ሰሎሞንን አልጋበዛቸውም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ከዚያም ናታን፣ ለሰሎሞን እናት ለቤርሳቤህ እንዲህ ሲል ነገራት፦ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ መንገሡን አልሰማሽምን?
|
|
\v 12 ስለዚህ የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት ለማትረፍ እንድትችዪ ልምከርሽ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ወደ ንጉሥ ዳዊት ሂጂ፤ እንዲህም በዪው፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣’ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ ምለህልኝ አልነበረምን? ታዲያ አዶንያስ የሚነግሠው ለምንድን ነው?”።
|
|
\v 14 በዚያም ከንጉሡ ጋር በመነጋገር ላይ እያለሽ እኔም ካንቺ በኋላ እገባና የተናገርሽው ሁሉ እውነት መሆኑን አረጋግጣለሁ” አላት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ስለዚህ ቤርሳቤህ ወደ ንጉሡ ክፍል ሄደች። ንጉሡ እጅግ ስለ ሸመገለ ሱነማይቱ አቢሳ ታገለግለው ነበር።
|
|
\v 16 ቤርሳቤህም ራስዋን ዝቅ አድርጋ ለንጉሡ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት፡፡
|
|
\v 17 እርሷም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ለአገልጋይህ፣ ‘በእርግጥ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በአምላክህ በጌታ እግዚአብሔር ስም ምለህ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ይኸው አሁን አዶንያስ ነግሦአል፤ አንተም ጌታዬ ንጉሡ ይህንን አታውቅም።
|
|
\v 19 ስለዚህ በሬዎችን፣ የሰቡ ኮርማዎችንና ብዙ በጎች ሠውቷል። ደግሞም የንገሡን ልጆች፣ ካህኑን አብያታርንና የሠራዊቱን አዛዥ ኢዮአብን ጋብዟቸዋል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጋበዘውም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ከአንተ ከጌታዬ በኋላ በዙፋንህ የሚቀመጠው ማን መሆኑን አንድታስታውቀው በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡
|
|
\v 21 አለበለዚያ ግን ጌታዬ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎሞን እንደ ወንጀለኛ እንቆጠራለን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 እርስዋ ለንጉሡ በመናገር ላይ እያለች ነቢዩ ናታን ገባ።
|
|
\v 23 አገልጋዮቹም ለንጉሡ፣ “ነቢዩ ናታን እዚህ ነው” ብለው ነገሩት። እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በቀረበ ጊዜ በግምባሩ ምድር ላይ በመደፋት ለንጉሡ ሰላምታ አቀረበ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ናታንም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ‘አዶንያስ ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለሃልን?
|
|
\v 25 እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችን፣ የሰቡ ጥጆችንና በጎችን ሠውቷል፤ ደግሞም የንጉሡን ልጆች ሁሉ፣ የሠራዊቱን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዟል። ንጉሥ አዶንያስ ለዘላለም ይኑር! በማለት በፊቱ በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ነገር ግን እኔን አገልጋይህን፣ ካህኑን ሳዶቅን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስንና አገልጋይህን ሰሎሞንን ወደ ግብዣው አልጠራንም።
|
|
\v 27 ከአንተ በኋላ በዙፋንህ ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ ለእኛ ለአገልጋዮችህ ሳትነግረን ይህንን ያደረግኸው ጌታዬ ንጉሡ ነህን?”
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 ከዚያም ንጉሡ ዳዊት፣ “ቤርሳቤህን ጥሩልኝ” አለ። እርስዋም ንጉሡ ወዳለበት መጥታ በፊቱ ቆመች።
|
|
\v 29 ንጉሡም ማለና፣ “ከደረሰብኝ መከራ ሁሉ የታደገኝ ጌታ እግዚአብሔር ሕያው የመሆኑን ያህል፤
|
|
\v 30 ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ላይ በእኔ ቦታ ይቀመጣል’ ብዬ በእስራኤል አምላክ በጌታ እግዚአብሔር ስም የማልኩትን መሓላ ዛሬ እፈጽመዋለሁ” አላት።
|
|
\v 31 ቤርሳቤህም ወደ መሬት በግንባሯ በመደፋት ለንጉሡ አክብሮቷን ካሳየች በኋላ፣ “ጌታዬ ንጉሡ ዳዊት ለዘለዓለም ይኑር!” አለች።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 32 ንጉሥ ዳዊትም፣ “ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንን እና የዮዳሄን ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። እነርሱም በንጉሡ ፊት ቀረቡ።
|
|
\v 33 ንጉሡም እንዲህ አላቸው፡- የጌታችሁን አገልጋዮች ከእናንተ ጋር ውሰዱ፤ ልጄን ሰሎምንንም እኔ በምቀመጥባት በቅሎ አስቀምጡትና ወደ ግዮን አውርዱት።
|
|
\v 34 ካህኑ ሳዶቅና ነቡዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡትና መለከት በመንፋት “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!” በሉ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 35 ከዚያም ተከትላችሁት ትመጣላችሁ፣ እርሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል፤ በእኔ ምትክ ይነግሣልና። በእስራኤልና በይሁዳ ላይ እንዲገዛ ሾሜዋለሁ”።
|
|
\v 36 የዮዳሄ ልጅ በናያስም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፡- “ይሁን! ይህንንም የጌታዬ የንጉሡ አምላክ ጌታ እግዚአብሔር ያጽናው።
|
|
\v 37 ጌታ እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር እንደ ሆነ እንዲሁ ከሰሎሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው” አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 38 ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ወረዱ፤ ሰሎሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ ወደ ግዮን አመጡት።
|
|
\v 39 ካህኑ ሳዶቅ ዘይት ያለበትን ቀንድ ከድንኳን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው። በዚያን ጊዜ መለከት ነፉ፣ ሕዝቡም፣ “ንጉሥ ሰሎሞን ለዘላለም ይኑር!” አሉ።
|
|
\v 40 ሕዝቡም ሁሉ ተከትሎት ወጣ፣ ሕዝቡም እምቢልታ እየነፉ በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው፣ ከድምፃቸው የተነሣ ምድር ተንቀጠቀጠች።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 አዶንያስና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንግዶች ሁሉ ምግባቸውን እንደጨረሱ ይህንን ድምፅ ሰሙ። ኢዮአብ የእምቢልታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፣ “ይህ በከተማ ውስጥ የሚሰማው ሁካታ ምንድን ነው?” አለ።
|
|
\v 42 እርሱ ገና በመናገር ላይ እያለ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ። አዶንያስም፣ “ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 43 ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ሲል መለሰለት፡- “ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን እንግሦታል፤
|
|
\v 44 ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ ከሊታውያንን እና ፈሊታውያንን ልኳል። እነርሱም ሰለሞንን በንጉሡ በቅሎ ላይ አስቀመጡት።
|
|
\v 45 ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታንም በግዮን ቀብተው አነገሡት፤ ደስ እያላቸውም ከዚያ ወጡ፣ በከተማው ሁካታ የሆነው ለዚህ ነው። የሰማችሁት ድምፅም ይኸው ነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 46 ደግሞም ሰሎሞን በመንግሦቱ ዙፋን ላይ ተቀምጧል።
|
|
\v 47 ከዚህም በላይ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ባለሟሎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ዳዊት ቀርበው አምላክህ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ከአንተ ይበልጥ ዝናውን ያግንነው፣ መንግሥቱንም ይበልጥ ታላቅ ያድርገው ሲሉ አክብሮታቸውን ገልጠዋል፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በአልጋው ላይ ሳለ ለእግዚአብሔር ሰገደ፡፡
|
|
\v 48 ዛሬ ከእኔ ዘሮች መካከል አንዱ በእኔ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ ያደረገና ይህን ለማየት ያበቃኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 49 አዶንያስ የጠራቸው ተጋባዦች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ሁሉም ተነሡ፤ እያንዳኑዱም በየፊናው ተበተነ፤
|
|
\v 50 አዶንያስም ሰሎሞንን ስለፈራ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ የመሠዊያውን ቀንዶች በመያዝ ተማጠነ፡፡
|
|
\v 51 ሰዎቹም ሰሎሞንን፣ አዶንያስ አንተን ከመፍራቱ የተነሣ የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ከሁሉ በፊት ንጉሥ ሰሎሞን የማይገድለኝ መሆኑን በማረጋገጥ በመሐላ ቃል ይግባልኝ በማለት እየተማጠነ ነው ሲሉ ነገሩት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 52 ንጉሥ ሰሎሞንም መልካም ሰው ከሆነ ከራስ ጠጉሩ አንዲት እንኳን አትነካበትም፤ ክፉ ሆኖ ከተገኘ ግን ይሞታል ሲል መለሰ።
|
|
\v 53 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን አዶንያስን ከመሠዊያው አውርደው ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ፤ አዶንያስ ወደ ንጉሡ ፊት በመቅረብ ወደ መሬት ራሱን ዝቅ አድርጎ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም ወደ ቤትህ ሂድ አለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 2
|
|
\p
|
|
\v 1 ዳዊት የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፤
|
|
\v 2 እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እንግዲህ በርታ ቆራጥ ሰው ሁን፡፡
|
|
\v 3 አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፣ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ትእዛዝ፣ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፡፡
|
|
\v 4 በዚህ ሁሉ ታዛዥ ሆነው ቢኖሩ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በእኔና የእስራኤል ሕዝብ የጦር መሪዎች በነበሩት በሁለቱ፣ በኔር ልጅ በአበኔርና በዬቴር ልጅ በአሜሳይ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ ሁለቱ በጦርነት ጊዜ ላፈሰሱት ደም ተበቅሎ በሰላም ጊዜ እነርሱን በመግደል የወገቡን ቀበቶና የእግሩን ጫማ በደም በከለ።
|
|
\v 6 እንግዲህ ባለህ ጥበብ በኢዮአብ ላይ ልትፈጸምበት የሚገባውን አድርግ፤ ዕድሜ ጠግቦ በሰላም እንዲሞት አትፍቀድለት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ይሁን እንጂ የገለዓዳዊው የቤርዜሊ ልጆች ከወንድምህ ከአቤሌሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ወደ እኔ መጥተው የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ፣ መልካም አድርግላቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡ መካከል ይሁኑ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ከዚህም ጋር መረሳት የሌለበት የብንያም ክፍል በሆነችው በባሑሪም ከተማ ውስት የሚኖረው የጌራ ልጅ ሳሚ ወደ መሃናይም በሄድኩበት ቀን በእኔ ላይ የስደብ ውርጅብኝ አውርዶብኛል፤ ይሁን እንጂ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባገኘኝ ጊዜ እንደማላስገድለው በእግዚአብሔር ስም ምየለታለሁ።
|
|
\v 9 ስለዚህ አንተ እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው። አንተ ጥበበኛ ሰው ስለሆንህ ምን መደረግ እንዳለበት ታውቃለህ። በሸመገለም ጊዜ በሞት ትቀጣዋለህ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ።
|
|
\v 11 ዳዊት በኬብሮን ሰባት ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በድምሩ አርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ነገሠ።
|
|
\v 12 ሰሎሞንም በአባቱ ዙፋን ተተክቶ ነገሠ፤ የመንግሥቱም ሥልጣን እጅግ የጸና ሆነ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 የአጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ። ቤርሳቤህም ወደ እኔ የመጣኸው በሰላም ነውን? ስትል ጠየቀችው፤ እርሱም አዎን በሰላም ነው ሲል መለሰላት።
|
|
\v 14 ቀጠል አድርጎም እኔ የምጠይቅሽ ጉዳይ አለኝ አላት። እርስዋም ጉዳይህን ተናገር አለችው።
|
|
\v 15 አዶንያስም እንዲህ አላት፣ ንጉሥ መሆን የሚገባኝ እኔ እንደ ነበርኩና ይህንንም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በተስፋ ይጠባበቅ እንደ ነበር አንቺ ታውቂያለሽ። ነገር ግን ጉዳዩ ከእግዚአብሔር ስለ ተወሰነ ነገሩ ተለውጦ መንግሥቱ ለወንድሜ ተሰጥቶአል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 አሁንም የምጠይቅሽ አንድ ጉዳይ ስላለኝ እምቢ በማለት አታሳፍሪኝ። ቤርሳቤህም ጉዳይህን ተናገር አለችው።
|
|
\v 17 እርሱም እንዲህ አላት፡- ንጉሥ ሰሎሞን አንቺን እምቢ እንደማይልሽ አውቃለሁ፤ ስለዚህ አቢሳ ተብላ የምትጠራውን ሱነማይት ልጃገረድ ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እንዲሰጠኝ እባክሽ አማልጅኝ አላት።
|
|
\v 18 እርስዋም መልካም ነው፤ ይህን ለንጉሡ እነግርልሃለሁ አለችው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 ስለዚህ ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሡ ገባች። ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት። እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት።
|
|
\v 20 እርስዋም እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፣ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ አለችው። ንጉሡም እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ጠይቂኝ አላት።
|
|
\v 21 እርስዋም ወንድምህ አዶንያስ አቢሳን እንዲያገባት ፍቀድለት አለችው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 ንጉሡም አቢሳን ለሚስትነት እንድሰጠው ብቻ ለምን ትጠይቂኛሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምንስ ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም? አላት።
|
|
\v 23 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን፣ በእግዚአብሔር ስም እንዲህ ሲል ማለ፡- አዶንያስ ይህን በመናገሩ በሕይወቱ እንዲከፍል ባላደርግ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ በበለጠም ይቅጣኝ አለ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 እግዚአብሔር በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ አስቀምጦኝ መንግሥቴን የጸና አድጎልኛል፤ ይህን መንግሥት ለእኔና ለዘሮቼ በመስጠት ቃሉን ጠብቆአል፤ እንግዲህ አዶንያስ በዚህ በዛሬው ቀን በሞት እንደሚቀጣ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።
|
|
\v 25 ስለዚህ አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያስ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያስም ሄዶ አዶንያስን ገደለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው፡- በአናቶት ወዳለው እርሻህ ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፣ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለተሸከምህ፣ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም።
|
|
\v 27 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን አብያታርን የእግዚአብሔር ካህን ሆኖ ከሚያገለግልበት የክህነት ሥልጣን ሽሮ አባረረው፤ በዚህም ዓይነት እግዚአብሔር በሴሎ ስለ ካህኑ ዓሊ፣ ስለ ትውልዱ የተናገረው ቃል ተፈጸመ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 የአቤሌሎም ደጋፊ ባይሆንም የአዶንያስ ደጋፊ የነበረው ኢዮአብ፣ ይህን የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ።
|
|
\v 29 ኢዮአብ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያስ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 30 እርሱም ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል አለው። ኢዮአብ ግን፣ አልወጣም እዚሁ እሞታለሁ አለ። በናያስም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው።
|
|
\v 31 ሰሎሞን በናያስን እንዲህ አለው፡- ኢዮአብ እንዳለህ ግደለውና ቅበረው፤ በዚህ ሁኔታ ኢዮአብ ካፈሰሰው ንጹሕ ደም የእኔንና የአባቴን ቤት የነጻን ታደርገናለህ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 32 አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሁለት ሰዎች ደም እግዚአብሔር ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የአስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር ኣዛዥ አሜሳይ ነበሩ።
|
|
\v 33 ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ ደማቸው በእርሱና በዘሮቹ ለዘለዓለም ይመለስባቸው። ነገር ግን ለዳዊትና ለዘሮቹ፣ ለቤቱና በዙፋኑ ለሚቀመጡት የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 ስዚህ በናያስ በታዘዘው መሠረት ኢዮአብን ገደለው፤ በቤቱም አጠገብ በሚገኘው በረሓ ተቀበረ።
|
|
\v 35 ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያስን የሠራዊት አዛዥ፣ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾማቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ሳሚን አስጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፡- በዚህ በኢየሩሳሌም የራስህን መኖሪያ ቤት ሠርተህ ተቀመጥ፤ ከዚያ የትም እንዳትሄድ፤
|
|
\v 37 ከከተማይቱ ወጥተህ የቄድሮንን ወንዝ ተሻግረህ ብትገኝ በእርግጥ ትሞታለህ፤ ለደምህም ተጠያቂው ራስህ ነህ።
|
|
\v 38 ሳሚም ንጉሥ ሆይ፣ ውሳኔህ መልካም ነው። አገልጋይህ አንተ ጌታዬ እንዳልከው አደርጋለሁ ሲል መለሰ። ስለዚህ በኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ ተቀመጠ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 39 ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ሁለቱ የሳሚ አገልጋዮች የመዓካ ልጅ ወደ ሆነው አንኩስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጌት ንጉሥ ኮብልለው ሄዱ፤ ሳሚም ባሪያዎቹ በጌት መኖራቸው ተነገረው።
|
|
\v 40 ሳሚም አህያውን ጭኖ እነርሱን ለመፈለግ በጌት ወደሚኖረው ወደ ንጉሥ አንኩስ ሄደ፤ እነርሱንም በዚያ ስላገኛቸው ወደ ቤት መልሶ አመጣቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 ንጉሥ ሰሎሞን ሳሚ ከኢየሩሳም ወደ ጌት ሄዶ መመለሱን ሰማ።
|
|
\v 42 ንጉሡም ሳሚን አስጠርቶ ከኢየሩሳሌም እንዳትወጣ በእግዚአብሔር ስም አስምዬህ አልነበረምን? ወጥተህ ብትገኝ ግን በእርግጥ እንደምትሞት አስታውቄህ አልነበረምን? በዚህስ ተስማምተህ ትእዛዜን እንደምትፈጽም ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? አለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 43 ታዲያ በእግዚአብሔር ስም ከማልህ በኋላ ትእዛዜንስ ስለምን አላከበርክም?
|
|
\v 44 በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር እግዚአብሔር ራሱ ይቀጣሃል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 45 እኔን ግን እግዚአብሔር ይባርከኛል፤ የዳዊት መንግሥትም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።
|
|
\v 46 ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያስ ሳሚን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያስም ሄዶ ሳሚን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 3
|
|
\p
|
|
\v 1 ሰሎሞን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ሴት ልጅ በማግባት ከንጉሡ ጋር ወዳጅነት መሠረተ። የፈርዖንንም ልጅ አምጥቶ ቤተ መንግሥቱን፣ ቤተ መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጥር ዙሪያውን ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አኖራት።
|
|
\v 2 በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደሱ ገና አልተሠራም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በየኮረብታው መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።
|
|
\v 3 ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኮረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብና ዕጣንም ያጥን ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለነበር አንድ ቀን ንጉሥ ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ። በዚያም መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።
|
|
\v 5 እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት በገባዖን ለሰሎሞን በሕልም ተገለጠለትና ምን እንድሰጥህ ትፈልጋህ? ጠይቅ አለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፡- አገልጋይህ የነበረው አባቴ ዳዊት፣ ታማኝና ቅን ሰው በመሆኑ ጽኑ ፍቅርህን አሳይተኸዋል። ዛሬም በእርሱ ፈንታ በዙፋኑ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት ታላቅና ጽኑ የሆነውን የማያቋርጥ ፍቅርህን ገልጠህለታል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ እነሆ እኔ በዕድሜዬ ልጅ ብሆንም በአባቴ ቦታ ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል። እኔም መግባትንና መውጣትን የማልችል ነኝ።
|
|
\v 8 እነሆ፣ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቆጠር በማይችል ሕዝብ መካከል አለሁ።
|
|
\v 9 ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በማስተዋል በትክክኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ። ይህ ካልሆን ይህን ታላቅ ሕዝብህን ሊመራ ማን ይችላል?
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ይህ የሰሎሞን ጥያቄ እንግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤
|
|
\v 11 ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ጠይቀሃል።
|
|
\v 12 እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊት ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ ሰጥቼሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማናቸውም ንገሥታት ያላገኙትን ብጽግናና ክብር አሰጥሃለሁ።
|
|
\v 14 አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድ ለእኔም ብትታዘዝ ሕጌንና ትእዛዞቼንም ብትፈጽም ረጅም ዕድሜ እሰጥሃሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ከዚህም በኋላ ለአገልጋዮቹ ሁሉ ግብዣ አደረገ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 አንድ ቀን ሁለት ሴተኛ አዳሪዎች መጥተው በሰሎሞን ፊት ቀረቡ፡፡
|
|
\v 17 ከእነርሱም አንደኛይቱ እንዲህ አለች ንጉሥ ሆይ ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት አብረን ስንኖር፣ በዚያውም በምንኖርበት ቤት ወንድ ልጅ ወለድኩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 እኔ በወለድኩ በሦስተኛው ቀን እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደች። በዚያ ቤት ውስጥ ከሁለታችን በቀር ሌላ ማንም አልነበረም።
|
|
\v 19 ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት በላዩ ላይ ተኝታበት ስለ ታፈነ ልጇ ሞተ።
|
|
\v 20 እኔ ተኝቼ ሳለሁ ሌሊት ተነሥታ ታቅፌው የተኛሁትን ልጄን ወስዳ በእርስዋ አልጋ ላይ ካስተኛች በኋላ የሞተውን ልጅዋን አምጥታ በእኔ አልጋ ላይ በጎኔ አስተኛችው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 በማግስቱ ማለዳ ተነሥቼ ልጄን ለማጥባት ስዘጋጅ ሞቶ አገኘሁት፤ ትኩር ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብኩ።
|
|
\v 22 ሁለተኛይቱ ሴት ግን አይደለም፣፣ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፣ የሞተው ግን የአንቺ ነው አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት አይደለም የሞተው የአንቺ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው አለች። በዚህ ዓይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን አንደኛዋ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፣ የሞተው ግን የአንቺ ነው ትላለች፤ ሌላይቱም ደግሞ አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቶአል፤ የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው ትላታለች አለ።
|
|
\v 24 ንጉሡም ሰይፍ እንዲያመጡለት አዘዘ፤ ሰይፍም አመጡለት።
|
|
\v 25 በሉ እንግዲህ በሕይወት ያለውን ልጅ ለሁለት ቁረጡና ለእያንዳንዱ ሴት ግማሽ አካሉን ስጡ ሲል አዘዘ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 እውነተኛይቱ ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ልጁን አትግደለው፤ ለእርስዋ ይሰጣት አለች። ሌላይቱ ሴት ግን፣ ለእኔም ለእርስዋም አይሁን፤ ለሁለት ይቆረጥ አለች።
|
|
\v 27 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ሕፃኑን አትግደሉት፤ እውነተኛይቱ እናት እርስዋ ስለሆነች ለመጀመሪያይቱ ሴት ስጡአት ሲል አዘዘ።
|
|
\v 28 እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 4
|
|
\p
|
|
\v 1 ንጉሡ ሰሎሞን በመላው አስራኤል ላይ ነግሦ ነበር።
|
|
\v 2 ንጉሡም የሾማቸው ባለሥልጣኖች እነዚህ ናቸው። እነርሱም፡- ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፡- ካህን ነበር።
|
|
\v 3 ኤልያፍና አኪያ የተባሉ የሴባ ልጆች የቤተ መንግሥት ጻሐፊዎች ነበሩ። ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ ታሪክ ጻሐፊና የመዛግብት ኃላፊ ነበር።
|
|
\v 4 በናያስ የተባለው የዮዳሄ ልጅ የጦር ሠራዊት አዘዥ ነበር። ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፡- የክፍለተ አገራት ገዢዎች የበላይ ኃላፊ ነበር። የናታን ልጅ ዛቡድ፡- ካህንና የንጉሡ አማካሪ ነበር።
|
|
\v 6 አሒሳር የተባለው፡- የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኃላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፡- የግዳጅ ሥራ ተቆጣጣሪና ኃላፊ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ንጉሡ ሰሎሞንም በመላው እስራኤል ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተ ሰብ ቀለብ የሚያዘጋጁ ዐሥራ ሁለት ባለሥልጣኖች ነበሩት፡፡ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው፡፡
|
|
\v 8 የእነዚህም ዐሥራ ሁለት ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸው ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፡- ቤንሑር፡- ኮረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤
|
|
\v 9 ቤንዴር፡- የማቃጽ የሻዓልቢም፤ የቤትሻሜሽ፡- የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዢ፤
|
|
\v 10 ቤንሔሴድ፡- የአሩቦትና የሶኮ ከተሞችና የመላው የሐፌር ግዛት አስተዳዳሪ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ጣፋት የተባለችውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው ቤን አሚናዳብ የመላው የዶር ግዛት አስተዳዳሪ፤
|
|
\v 12 በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፡-የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፤ እንዲሁም በቤትሳን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ በጸርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተደቡብ ያለው ግዛት፤ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅምዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ፤
|
|
\v 13 በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የኢያዕር ጎሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፤ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጥር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስልሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤
|
|
\v 14 አሒናዳብ የተባለው የዔዶ ልጅ፡- የመሃናይም ክፍለ አገር ገዢ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 መካከል ባስማት ተብላ የምትጠራውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው አኪማአስ፡- የንፍታሌም ግዛት አስተዳዳሪ፤
|
|
\v 16 በዓና የተባለው የሔሻይ ልጅ፡- የአሴር ግዛትና የበዓሎት ከተማ ገዢ፤
|
|
\v 17 ኢዮሣፍጥ የተባለው የፋሩሕ ልጅ፡- የይሳኮር ግዛት አስተዳዳሪ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ሳሚ የተባለው የኤላ ልጅ፡- የብንያም ግዛት አስተዳዳሪ፤
|
|
\v 19 ጊቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፡- በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ፤ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቆጣጠር በመላ አገራቱ ሌላ አንድ የበላይ ኃላፊ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ እየተሰኙ ነበር፡፡
|
|
\v 21 የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፣ ከዚያም አልፎ እስከ ግብፅ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር፡፡
|
|
\v 22 ሰሎሞንም በየቀኑ ለቀለብ የሚሆን አምስት ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ምርጥ ዱቄት፤ ዐሥር ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ነበር፡፡
|
|
\v 23 በበረት ውስጥ እየተመገቡ የደለቡ ዐሥር ሰንጋዎችና በግጦሽ መስክ ተሰማርተው የተመገቡ ሃያ ፍሪዳዎች፣ አንድ መቶ በጎች፤ ከዚህም ሌላ አጋዘኖች፣ የሜዳ ፍየሎች፤ ሚዳቆዎችና ምርጥ ወፎች ያስፈልጉት ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ሁሉ ከቲፍሳ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጎረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር፡፡
|
|
\v 25 በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳር እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለ ስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ለራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ሰሎሞን ሠረገላ የሚስቡ አርባ ሺህ ፈረሶች፣ ለጦርነት የሚያገለግሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት፡፡
|
|
\v 27 ለሰሎሞንና በቤተ መንግሥቱ ለሚቀለቡት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብ የሚያቀርቡ ዐሥራ ሁለቱ ገዢዎች እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ወር ምንም ነገር ሳያጓድሉ በወቅቱ ያመጡ ነበር፡፡
|
|
\v 28 ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደሚችለው ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገለባ ያቀርብ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 እግዚአብሔር ለሰሎሞን አጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተተዋይነትን እንዲሁም እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፡፡
|
|
\v 30 የሰሎሞንም ጥበብ ከምሥራቅ አገርና ከግብፅም ጥበበኞች እጅግ የላቀ ነበረ፡፡
|
|
\v 31 እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ኤታን፣ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሮማን ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጎረቤት ሕዘቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 32 ሦስት ሺህ ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት የመዝሙር ድርስቶች ነበሩት፡፡
|
|
\v 33 ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች ምሳሌዎችን ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፣ ወፎች፣ በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለዓሣዎች አስተምሮአል፡፡
|
|
\v 34 በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ለመስማት ይመጡ ነበር፡፡ ስለ ጥበቡም የሰሙት ከምድር ነገሥታት ሁሉ ወደ እርሱ መጥተዋል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 5
|
|
\p
|
|
\v 1 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቆይቶ ነበር፤ እርሱም ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት ፈንታ መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ፡፡
|
|
\v 2 ሰሎሞንም ወደ ኪራም እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፡፡
|
|
\v 3 አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት ከብዙ ጦርነቶች የተነሣ ለእግዚአብሕሔር አምላክ በስሙ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉን ታውቃለህ፤ እግዚአብሔርም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች አንበረከካቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 አሁን ግን አምላኬ እግዚአብሔር በሁሉም ድንበር እረፍት ሰጥቶኛል፡፡ ምንም ዓይነት ጠላት ወይም አደጋ የሚጥል የለብኝም፡፡
|
|
\v 5 ስለዚህ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፡- ከአንተ በኋላ የማነግሠው ልጅህ ለእኔ በስሜ ቤተ መቅደስ ይሠራልኛል ሲል ተናግሮት ስለነበር፤ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በስሙ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አሁን አቅጃለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ስለዚህም የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቆርጡ ሰዎች ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፡፡ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደረጋለሁ፤ ለአንተም ሰዎች የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተም እንደምታውቀው፣ የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቆራረጥ የአንተን ሰዎች ያህል ዕውቀት የላቸውም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ኪራም የሰሎሞን መልእክት ሲደርሰው እጅግ ተደሰቶ፣ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ እንዲነግሥ ይህን የመሰለ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠው እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለ፡፡
|
|
\v 8 ከዚህ በኋላ ኪራም ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለሰሎሞን ላከ፤ የላክልኝን መልእክት ሰምቻለሁ፤ የምትፈልገውን ሁሉ፣ የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባውን ግንድ አዘጋጅልሃለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 የእኔ ሰዎችም ግንዶችን ከሊባኖስ ወደ ባሕር ያወርዳሉ፤ አስረውም አንተ ወደምትፈልገው ጠረፍ በውኃ ላይ ተንሳፍፈው እንዲደርሱ ያደርጋሉ፤ በዚያም የእኔ ሰዎች ማሰሪያውን ፈተው ለአንተ ሰዎች ያስረክቡአቸዋል፤ አንተም በበኩልህ ለቤተ ሰቤ ምግብ በመስጠት ፍላጎቴን ትመልስልኛለህ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 በዚህ ዓይነት ኪራም ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባ ግንድ ሁሉ ሰጠው፡፡
|
|
\v 11 ሰሎሞንም በበኩሉ ለኪራም ቤተ ሰቦች ቀለብ የሚሆን ሃያ ሺህ መስፈሪያ ስንዴና ሃያ መስፈሪያ ንጹሕ ዘይት ሰጠ፡፡ ይህንንም በየዓመቱ ይሰጥ ነበር፡፡
|
|
\v 12 እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብ ሰጠው፤ በሰሎሞንና በኪራም መካከል ሰላም ነበር፤ ሁለቱም የጋራ ስምምነት አደረጉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል ሠራተኞችን መለመለ፤ የግዳጅ ሠራተኞችም ሠላሳ ሺህ ነበሩ፡፡
|
|
\v 14 ዐሥር ሺህ የሚያህሉትን ለአንድ ወር ወደ ሊባኖስ በፈረቃ ላካቸው፡፡ ለአንድ ወር በሊባኖስ ሁለት ወር በቤታቸው ነበሩ፡፡ አዶኒራም የተባለው ሰው በግዳጅ ሠራተኞች ላይ ኃላፊ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ንጉሥ ሰሎሞን በኮረብታማው አገር ድንጋይ የሚፈልጡ ሰማኒያ ሺህ፣ የተፈለጠውን ድንጋይ ተሸክመው የሚያመጡ ሰባ ሺህ ሰዎች ነበሩት፡፡
|
|
\v 16 የእነዚህ ሠራተኞች የበላይ ሆነው ሥራውን የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰዎች ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 በዚህ ዓይነት ሠራተኞቹ በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ ለቤተ መቅደሱ መሠረት የሚሆን ታላላቅ ድንጋዮችን ፈለጡ፡፡
|
|
\v 18 የሰሎሞንና የኪራም አናጢዎችና ግንበኞች የጌባላውያንም ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የሚያስችላቸውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ አዘጋጁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 6
|
|
\p
|
|
\v 1 ስለዚህ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ፡፡ ይህም የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ፣ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር ነበር፡፡
|
|
\v 2 ቤተ መቅደሱም በውስጥ በኩል ርዝመቱ ሃያ ሰባት ሜትር፣ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፣ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፣ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር፡፡
|
|
\v 4 የቤተ መቅደሱም ሕንፃ ከውስጥ ሰፋ፣ ከውጪ ጠበብ ያሉ መስኮቶች ነበሩት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 በቤተ መቅደሱን ሕንፃ ፊት ለፊት ግድግዳ ዙሪያ ክፍሎችን ሠራ፤ በዋናው መግቢያ በር በውጪና በውስጥ ክፍሎች ሠራ፤ በዙሪያውም ክፍሎችን አደረገ፡፡
|
|
\v 6 የታችኛው ፎቅ ክፍል ወርዱ አምስት ክንድ፣ የመካከለኛ ፎቅ ክፍል ስድስት ክንድ፣ የሦስተኛው ፎቅ ክፍል ወርድ ሰባት ክንድ ነበር፤ የእንያዳንዱ ወለል ግንብ ከታች በኩል ካለው የወለል ግንብ የሳሳ ነበር፤ ሠረገሎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግድግዳ እንዳይገቡ ለማድረግ ከቤተ መቅደሱ ግድግዳ ውጪ ዐረፍቶችን አደረገ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ቤተ መቅደሱ የታነጸባቸው ድንጋዮች ተጠርበው የተዘጋጁት በዚያው በተፈለጡበት ቦታ ነበር፤ ቤተ መቅደሱ በሚሠራበት ጊዜ የመዶሻ፣ የመጥረቢያ ወይም የሌላ ብረት ነክ መሣሪያ ድምፅ አይሰማም ነበር፡፡
|
|
\v 8 ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ በኩል በምድር ደረጃው ላይ መግቢያ በር ነበር፡፡ ከዚያ በደረጃዎቹ መካከለኛ ደረጃ ወደ ላይ ያስኬዳል፡፡ እንዲሁም ከመካከለኛው ደረጃ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ይወስዳል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 በዚህ ሁኔታ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንፃ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ቤቱን ሸፈነው፡፡
|
|
\v 10 የእያዳንዱ ፎቅ ቁመት አምስት ክንድ ከፍታ ሆኖ ከውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ተጠግቶ የተሠራው ባለ ሦስት ፎቅ ተጨማሪ ሕንፃ ከዋናው ሕንፃዎች ከሊባኖስ ዛፍ በተሠሩት አግዳሚ ወራጆች የተያያዘ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሰሎሞን እንዲህ ሲል መጣ፡-
|
|
\v 12 እየተሠራ ያለውን ቤተ መቅሰደስ በተመለከተ፣ በትእዛዜ መንገድ ብትሄድና ቅን ፍርድ ብታደርግ ለአባትህ ለዳዊት እንዳደረግሁ የሰጠሁትን ተስፋ አጸናልሃለሁ፡፡
|
|
\v 13 በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እኖራለሁ፣ ከቶም አልተዋቸውም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ስለዚህ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ጨረሰ፡፡
|
|
\v 15 ከዚያ የቤተ መቅደሱን የውስጥ ግድግዳዎች በሊባኖስ ዝግባ ሠራ፤ ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርበው በተሠሩ ሳንቃዎች ለበደ፤ የወለሉም ጣውላ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ውስጣዊ ክፍል ከቤተ መቅደሱ በስተ ኋላ ገባ ብሎ ተሠራ፣ የእርሱም ርዝመት ዘጠኝ ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተከፈለ ነበር፤ ይህንን ክፍል ቅድሰተ ቅዱሳን ውስጠኛ ክፍል እንዲሆን ነው፡፡
|
|
\v 17 ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የሚገኘውም የተቀደሰ ክፍል ርዝመት አርባ ክንድ ነበር፡፡
|
|
\v 18 የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበጠ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 ሰሎሞንም ከቤተ መቅደሱ ውስጥ በስተኋላ በኩል የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚቀመጥበት ውስጣዊ ክፍል አዘጋጀ፡፡
|
|
\v 20 ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፣ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፣ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር ሲሆን፣ በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበጠ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ እርሱም ክፈፉን በተሸጋገሩ የወርቅ ሰንሰለቶች አስጌጠው፡፡
|
|
\v 22 የቅድስት ቅዱሳኑ ውስጠኛ በወርቅ ለበጠው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ሰሎሞንም እያንዳንዱ ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት በሁለት ኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሠራ፡፡
|
|
\v 24 የኪሩቡ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ፤ የኪሩቡም ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ፡፡
|
|
\v 25 ሁለተኛውም ኪሩብ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁለቱም ኪሩቤል ቅርጽና መጠን ተመሳሳይ ነበር፡፡
|
|
\v 26 የአንዱ ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁለተኛውም ኪሩብ እንዲሁ ነበረ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 ኪሩቤልንም በቅድስት ቅዱሳኑ ውስጥ እንዲቆሙ አደረገ፤ ስለዚህም የተዘረጉ ሁለቱ ክንፎቻቸው በክፍሉ መካከለኛ ቦታ ላይ ተገናኝተው ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ በተዘረጉበት አቅጣጫ ግንቦቹን ይነኩ ነበር፡፡
|
|
\v 28 ሰሎሞንም ሁለቱን ኪሩቤል በወርቅ ለበጣቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 የዋናውን ክፍልና የውስጠኛውን ክፍል ግንቦች በሙሉ በኪሩቤል፣ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፡፡
|
|
\v 30 እርሱም ከውስጥና ከውጪ በኩል ያሉትን ክፍሎች ወለል በወርቅ ለበጣቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 ከወይራ እንጨት የተሠራ ሁለት ተካፋች በር በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ እንዲቆም አደረገ፤ በሩም አምስት ማእዘን ያለው ሆኖ አናቱ ላይ ቀጥ ብሎ የተሠራ ቅስት ነበር፡፡
|
|
\v 32 ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፤ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፣ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎቹንና ቅርጾቹን በወርቅ ለበጣቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 በዚህ ዓይነት ሰሎሞን ደግሞ ወደ ዋናው ክፍል ለሚያደርሰው መግቢያ በር ከወይራ እንጨት የተሠራ ባለ አራት ማእዘን ክፈፍ አበጀለት፡፡
|
|
\v 34 ሁሉቱንም በሮች ከዝግባ እንጨት ሠራ፤ አንዱ በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፤ ሁለተኛውም በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፡፡
|
|
\v 35 እነርሱን ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፣ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 37 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረቱ የተጣለው ሰሎሞን በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር ነበር፡፡
|
|
\v 38 ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሁሉም ክፍሎችና ሁሉም ንድፍ ተጠናቀቀ፡፡ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ሰባት ዓመት ወሰደበት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 7
|
|
\p
|
|
\v 1 ሰሎሞንም ለራሱ የሚሆን ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ቤተ መንግሥቱንም ለመሥራት ዐሥራ ሦስት ዓመት ፈጀበት፡፡
|
|
\v 2 እርሱም የሊባለኖስ ጫካ ተብሎ የተጠራውን ቤተ መንግሥት ሠራ፡፡ ርዝመቱም ወርዱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱም አምሳ ክንድ፤ ቁመቱም ሠላሳ ክንድ ነበር፡፡ ቤተ መንግሥቱ አራት ረድፍ ሆኖ ከዝግባ እንጨት ምስሶዎች የተሠሩ ሲሆን፣ በምስሶዎቹ ላይ አግዳሚ ሠረገላዎች ተጋድመው ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 የእነዚህ ዕቃ ቤቶች ጣራ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፡፡ በምስሶዎቹም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዝግባ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፡፡ ምስሶዎቹም በአንዱ ረድፍ ዐሥራ አምስት፣ በአንዱ ረድፍም አምስት እየሆኑ አርባ አምስት ነበሩ፡፡
|
|
\v 4 ትይዩ የሆኑት የሕንፃው ሁለት ግንቦች እያንዳንዳቸው በመደዳ ሦስት፣ ሦስት መስኮቶች ነበሩአቸው፡፡
|
|
\v 5 በሮቹና መስኮቶቹ ሁሉ ባለአራት ማእዘን መቃኖች ነበሩአቸው፤ ለእያንዳንዱ ግንብ በረድፍ የተሠሩ ሦስት ሦስት መስኮቶች ነበሩት፤ የእያንዳንዱ ግንብ መስኮቶች ከሌላው ግንብ መስኮቶች ጋር ትይዩ ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ምሶሶዎች ያሉበትን ቤት ሠራ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፣ ስፋቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእርሱም ፊት ደግሞ ምሶሶና መድረክ ያለበት ወለል ነበረ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ሰሎሞን ችሎት ተቀምጦ የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበትም የዙፋን አዳራሽ ሠራ፡፡ ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ሳንቃ የተሸፈነ ነበር፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ከችሎቱም አዳራሽ በስተ ኋላ በሚገኘው ሌላ አደባባይ ሰሎሞን የሚኖርበትን ሕንጻ እንደ ሌሎቹ ሕንጻዎች አድርጎ አሠራ፤ የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ ለነበረቸው ሚስቱም ተመሳሳይ መኖሪያ ቤት አሠራላት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 እነዚህ ሁሉ ሕንፃዎችና ታላቁ አደባባይ ጭምር ከመሠረታቸው እስከ ድምድማታቸው በጥሩ ታላላቅ ድንጋዮች አጊጠው የተሠሩ ነበሩ፣ ድንጋዮቹም በዚያ በድንጋይ መፍለጫ ስፍራ በፊትም በኋላም በልክ ተፈልፍለውና ተጠርበው የመጡ ነበር፡፡
|
|
\v 10 የቤቱ መሠረት የተሠራው በጣም ታላላቅና ውድ በሆኑ ስምንትና ዐሥር ክንድ ርዝመት ባላቸው ድንጋዮች የተሠሩ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 እነዚህም ውድና በልክ ከተፈለፈሉ ድንጋዮችና ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠሩ አግዳሚ ሠረገሎች ነበሩ፡፡
|
|
\v 12 የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባው በር በእያንዳንዱ ባለ ሦስት ረድፍ የጥርብ ድንጋይ ሕንፃ ላይ አንዳንድ ረድፍ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሠረገላ የተጋደመባቸው ግንቦች ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ንጉሡ ሰሎሞንም ሔራም የተባለውን ሰው ከጢሮስ ከተማ አመጣ፡፡
|
|
\v 14 ሔራም እናቱ ባል የሞተባት የንፍታሌም ነገድ ተወላጅ ነበረች፣ አባቱም የጢሮስ ተወላጅ ሲሆን እርሱም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሙያ ነበር፡፡ ሔራም በእጅ ጥበብ ብዙ ልምድ ያለው ብልህ ሰው ነበር፤ እርሱም የነሐስ ጥበብ ሥራ ለንጉሡ ለመሥራት ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መጣ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ሔራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ የዙሪያ ስፋታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ ሁለት የነሐስ ምሶሶዎችን ሠራ፡፡
|
|
\v 16 እንዲሁም በምሶሶዎቹ ላይ የሚቆሙ የእያንዳንዳቸው ቁመት አምሰት ክንድ የሆነ ሁለት የነሐስ ጉልላቶችን ሠራ፡፡
|
|
\v 17 በምሶሶዎቹም ራስ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ያስጌጡ ዘንድ በሰባት ረድፍ የተሠሩ መረቦችን ሠራ፡፡ አንዱን መረብ ለአንድ ጉልላት ሁለተኛውን መረብ ለሁለተኛው ጉልላት አደረገ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ስለዚህም ሔራም ምሶሶዎቹ ጫፍ ላይ ያሉትን ጉልላቶች ለማስጌጥ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ፡፡ ለየእያንዳንዱም ጉልላት እንዲሁ አደረገ፡፡
|
|
\v 19 በወለሉ ምሶሶዎች አናት ላይ ያሉት ጉልላቶች ቁመታቸው አራት ክንድ ሲሆን የሱፍ አበባን በሚመስል ሥራ ተጊጠው ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 እነርሱም ከመረቡ በላይ ባለው ክብ ስፍራ እንዲቆሙ ተደረገ፤ በእያንዳንዱም ጉልላት ዙሪያ በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ሁለት መቶ የሮማን ቅርጾች ነበሩ፡፡
|
|
\v 21 ሔራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምስሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፡፡ ከቤተ መቅደሱም መግቢያ በር በስተደቡብ በኩል የቆመው ምሶሶ «ያኪን» ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሶሶ ደግሞ «ቦዔዝ» ተባለ፡፡
|
|
\v 22 በምሶሶዎቹ ጫፍ ላይ የሱፍ አበባ የሚመስሉ ከነሐስ የተሠሩ ጉልላቶች ነበሩ፡፡ የምስሶዎቹም ሥራ በዚህ ዓይነት ተፈጸመ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ሔራም ዐሥር ክንድ ጥልቀት፣ የክብ ማእከል ርዝመት አምስት ክንድ ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ፡፡ ባሕሩም ዙሪያው ሠላሳ ክንድ ነበር፡፡
|
|
\v 24 የገንዳው አፍ ውጪኣዊ ክፈፍ ሁሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በቅል አምሳል ከነሐስ የተሠሩና በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ቅርጾች ነበሩት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬ ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ። ኮርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፤ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር፡፡
|
|
\v 26 የገንዳውም ጎኖች ውፍረት አንድ መዳፍ ነበር፤ የጽዋ ቅርጽ ያለው አበባ የሚመስል የአፉ ክፈፍ የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበረው፤ ይህም ገንዳ አርባ ሺህ ሊትር ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 ሔራም ዐሥር መቀመጫዎችን ከነሐስ ሠራ፡፡ የእያንዳንዱ ርዝመት አራት ክንድ፣ ቁመቱ አራት ክንድ፣ ሦስት ክንድ ስፋት ነበር፡፡
|
|
\v 28 የመቀመጫዎቹ ሥራም እንዲህ ነበር፡፡ የዕቃ መቀመጫዎቹም የተሠሩት በክንፎቹ መካከል ልሙጥ በሆነ ነገር ነበር፡፡
|
|
\v 29 ልሙጥ በሆነውም ነገር ላይ በአንበሶች፣ በበሬዎችና በኪሩቤል አምሳል የተቀረፁ ምስሎች ነበሩ፡፡ ከአንበሶቹ፣ ከበሬዎቹና ከኪሩቤሉ ቅርፆች ራስጌና ግርጌ የአበባ ጉንጉን የሚመስሉ ቅርፆች ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 30 እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ከነሐስ የተሠሩ አራት መንኮራኩሮች ነበሩባቸው፡፡ መንኮራኩሮቹም የሚሽከረከሩበት የነሐስ ወስከምቶች ነበራቸው፤ እንዲሁም በአራቱ ማእዘኖች የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበሩ፤ መደገፊያዎቹም የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርፆች አጊጠው ነበር፡፡
|
|
\v 31 የመታጠቢያ ገንዳውም አንገት አንድ ክንድ ነበር፤ እርሱም ክብ ነበር፤ ቁመቱም አንድ ክንድ ነበር፤ በአንገቱም ላይ ማስጌጫ ቅርፅ ነበረበት፤ የገንዳው ተሸካሚ ግን አራት ማእዘን ነበር እንጂ ክብ አልነበረም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 32 የመንኮራኩሮቹም ቁመት አንድ ተኩል ክንድ ነበር፤ መንኮራኩሮችም በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ነሐስ ሥር ነበሩ፤ የመንኮራኩሮቹም ወስከምቶች ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፡፡
|
|
\v 33 መንኮራኩሮቹም የሠረገላ መንኮራኩሮችን ይመስሉ ነበር፡፡ ወስከምቶቻቸው፣ ቅርጾቻቸውና አቃፊዎቻቸው ሁሉም ከብረት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ማእዘን በየግርጌአቸው ከእነርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከነሐስ የተሠሩ አራት ደጋፊዎች ነበሩአቸው፡፡
|
|
\v 35 በእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ጫፍ ዙሪያ ክፈፍ ላይ ተኩል ክንድ ርዝመት ያለው አንድ ክብ ቅርፅ ነበር፤ መደገፊያዎቹና ጠፍጣፋ ነሐሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 በእነዚህ መደገፊያዎችና ጠፍጣፋ ነሐሶች መካከል ባለው ክፍት ቦታ ሁሉ በኪሩቤል፣ በአንበሶችና በዘንባባ ዛፎች አምሳል ሔራም ሠራቸው፡፡ እንዲሁም ዙሪያቸው የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርፆች አጊጠው ነበር፡፡
|
|
\v 37 እንግዲህ ዐሥሩን ባለመንኩራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎች የሠራቸው በዚህ ዓይነት ነበር፡፡ መጠናቸውና ቅርፃቸው እኩል ስለተቀረጹ ሁሉም ተመሣሣይ ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 38 ሔራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር የነሐስ መታጠቢያ ገንዳዎች ሠራ፡፡ የእያንዳንዱ ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አራት ክንድ ያህል ሲሆን፣ አርባ ሊትር ያህል ውሃ ይይዝ ነበር፡፡
|
|
\v 39 ሔራም አምስቱን የዕቃ ማስቀመጫዎች ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ፣ የቀሩትንም አምስቱን ከቤተ መቅደሱ በስተሰሜን በኩል አቆመ፡፡ ገንዳውን ደግሞ በቤተ መቅደሱ ደቡባዊ ምሥራቅ ማእዘን ላይ አቆመው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 40 ሔራምም ድስቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጎድጓዳ ሳህኖችን ሠራ፡፡ በዚህ ዓይነትም ለንጉሥ ሰለሞን ሊሠራለት የጀመረውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ፈጸመ፡፡
|
|
\v 41 ሁለቱ ምሰሶዎች፣ በምሶሶዎቹም ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚመስሉ ሳህኖችን፣ በምሶሶውም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መረቦች ሠራ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 42 በእያንዳንዱ ጉልላት ላይ በመረብ አምሳል የተሠሩት ሰንሰለቶች፣ በእያንዳንዱ ጉልላት ቅርፅ ላይ በሁለት ዘርፍ አንዳንድ መቶ ዙር የሆኑ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ቅርፆችን ሠራ፡፡
|
|
\v 43 ዐሥሩ ባለመንኮራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 44 ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፣ ገንዳውን ደግፈው የሚይዙ የዐሥራ ሁለቱን በሬዎች ቅርፅ ሠራ፡፡
|
|
\v 45 ድስቶቹን፣ መጫሪያዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ሠራ፡፡ ሌሎችንም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሔራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰለሞን የሠራለት ከተወለወለ ንፁህ ነሐስ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 46 ንጉሥ ሰለሞን እነዚህን ሁሉ ያሠራው በዮርዳኖስ ሸለቆ በሱኮትና ጻርታን መካከል በሚገኘው በሸክላ ስፍራ ነበር፡፡
|
|
\v 47 ከነሐስ የተሠራው ይህ ሁሉ ዕቃ እጅግ ብዙ ስለ ነበር፣ ሰለሞን በሚዛን እንዲለካ አላደረገውም፣ ስለዚህ ክብደቱ ምን ያህል እንደሆነ ተወስኖ አልታወቀም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 48 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰለሞን ያሠራቸው ዕቃዎች ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ያጌጡ ነበሩ፡፡ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ ናቸው፡፡
|
|
\v 49 በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተደቡብ፣ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፣ አበባዎች፣ የመብራት ቀንዲሎች፣ የእሳት መቆስቆሻዎች ሁሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 50 ሰሎሞንም ጽዋዎችን፣ የአመድ ማጠራቀሚያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳህኖችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ሳህኖችን፣ ማንደጃዎችን፣ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችንና ለቤተ መቅደሱ ውጪኣዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎችን ከንጹሕ ወርቅ አሠራ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 51 በዚህ ዓይነት ንጉሥ ሰለሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፣ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 8
|
|
\p
|
|
\v 1 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ለማምጣትና ወደ ቤተ መቅደሱ ለማስገባት የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጎሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ፡፡
|
|
\v 2 የእስራኤልም ወንዶች ሁሉ በዓሉ በሚከበርበት ኤታኒም ተብሎ በሚጠራው በሰባተኛው ወር ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ተሰበሰቡ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 መሪዎቹ ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜም ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሥተው ተሸከሙ፡፡
|
|
\v 4 ካህናቱም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት፣ የመገናኛ ድኳንና በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ንዋያተ ቅዱሳት ሁሉ አምጥተው ወደ ቤተ መቅደስ አገቡ፡፡
|
|
\v 5 ንጉሥ ሰሎሞንና መላው የእስራኤል ሕዝብ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ተሰበሰቡ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቆጠር የማይችል ብዙ በጎቸና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል፣ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፎች ሥር አኖሩት፡፡
|
|
\v 7 የተዘረጉ የኪሩቤል ክንፎችም የታቦቱን መሸከሚያ መሎጊያዎች ሸፍነው ነበር፡፡
|
|
\v 8 መሎጊያዎቹ ረጃጅሞች ስለ ሆኑ ጫፎቻቸው በቤተ መቅደሱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ለሚቆም ሰው ሁሉ በግልጽ ይታዩ ነበር፤ በሌላ አቅጣጫ የሚቆም ግን አያያቸውም፡፡ እስከ ዛሬም እዚያው ይገኛል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳ በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳን ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳን ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም፡፡
|
|
\v 10 ካህናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን እንደ ወጡ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ድንገት በደመና ተሞልቶ ነበር፡፡
|
|
\v 11 በደመናውም ውስጥ የነበረው የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ስለ ሞላ ካህናቱ ቆመው አገልግሎታቸውን ለማከናወን አልቻሉም ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 በዚህ ጊዜ ሰሎሞን እንዲህ ሲል ጸለየ፡- እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አንተ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እኖራለሁ ብለሃል፤
|
|
\v 13 እነሆ አሁን ግርማ ሞገስ ያለው ቤተ መቅደስ ለአንተ ሠርቻለሁ፤ እርሱም አንተ ለዘለዓለም የምትኖርበት ቦታ ይሆናል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 የእስራል ጉባኤ ሁሉ ቆመው ሳሉ፤ ንጉሥ ሰሎሞን ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ የእግዚአብሔር በረከት በእርሱ ላይ እንዲወርድ እንዲህ ሲል ጸለየ፤
|
|
\v 15 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን አጽንቶ ጠብቆአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፡-
|
|
\v 16 ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዓይነት ከተማ አልመረጥኩም ነበር፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መረጥኩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ቀጥሎም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስን ለመሥራት አቅዶ ነበር፤
|
|
\v 18 እግዚአብሔርም አባቴን ዳዊትን ስሜ የሚጠራበትን ቤተ መቅደስ ትሠራ ዘንድ በልብህ ማሰብህ መልካም ነው፡፡
|
|
\v 19 ነገር ግን እርሱን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው እንጂ አንተ አይደለህም፤ ከአንተ የሚወለደው ልጅ ቤተ መቅደሴን ይሠራል አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 እነሆ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህ እኔ በአባቴ ፈንታ ተተክቼ የእስራኤል ንጉሥ ሆኜአለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስን ሠርቼአለሁ፡፡
|
|
\v 21 እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ቃል ኪዳን የገባበት የድንጋይ ጽላት ለሚገኝበት ታቦት ማኖሪያ የሚሆን ቦታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘጋጅቼአለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በሕዝቡ ፊት ተነሥቶ በእግዚአብሔር መሠዊያው ፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ፡፡
|
|
\v 23 እንዲህም አለ፡- የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ከልባቸው ታማኞች እስከ ሆኑ ድረስ ፍቅሩን የሚያጸና በላይ በሰማይ በታችም በምድ እንደ አንተ ያለ አምላክ የለም!
|
|
\v 24 ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል አጽንተሃል፤ በአፍህ የተናገርከውም ቃል ሁሉ እነሆ ዛሬ በእጅህ ተፈጽሞአል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 አሁን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት አንተ ታደርገው በነበረው ዓይነት ልጆችህ ታዛዦች ቢሆኑና በፊቴም በቅንነት ቢመላለሱ ሁልጊዜ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም ስትል የተናገርከውን የተስፋ ቃል ፈጽም፡፡
|
|
\v 26 አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ! አገልጋይህ ለነበረው ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፤ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስ ምንኛ ያንስ፡፡
|
|
\v 28 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ወደ አገልጋይህ ጸሎትና ልመና ተመልክት፤ ዛሬም አገልጋይህ በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጩኸት ስማ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ስሜ ይጠራበታል ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ፡፡
|
|
\v 30 ፊታችንን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰን በምንጸልይበት ጊዜ የእኔንና የእስራኤልን ሕዝብ ጸሎት ስማ፤ ከመኖሪያህ ከሰማይ ሆነህ ስማን፤ ይቅርም በለን፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 አንድ ሰው ባልንጀራውን መበደሉን የሚገልጥ ክስ ቀርቦበት በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው መሠዊያ አምጥተውት ከበደል ንጹሕ መሆኑን በመሐላ በሚያረጋግጥበት ጊዜ፣ በሰማይ ሆነህ ስማ፤
|
|
\v 32 ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ ይኸውም በደል የሠራው ሰው በጥፋቱ መጠን እንዲቀጣ፣ ንጹሕ የሆነውም ነጻ እንዲወጣ አድርግ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 ሕዝብህ እስራኤል በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት በጠላቶቻቸው ድል ሲሆኑ ተጸጽተው ወደ አንተ በመመለስ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና የአንትን ይቅርታ ለማግኘት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትሕትና ቢለምኑህ፤
|
|
\v 34 አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በምርኮ የሚገኙትንም ሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በማለት ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሰህ አግባቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 35 የእስራኤል ሕዝብ በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፤
|
|
\v 36 አንተ በሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፣ በልብ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፣ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 37 በምድሪቱ ላይ ረሐብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፣ እንዲሁም እህላቸው በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብህ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፣
|
|
\v 38 በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብ የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፣ ጸሎታቸውን ስማ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 39 በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማት ይቅር በላቸው፤ እርዳቸውም፣ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን አሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው፡፡
|
|
\v 40 በዚህም ዓይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 በተጨማሪም የሕዝብህ የእስራኤል ወገን ያልሆነ፣ የውጪ አገር ሰው ከስምህ የተነሣ ከሩቅ ቢመጣ፤
|
|
\v 42 ስለስምህ ገናናነት፣ ስለታላቁ እጅህና ከፍ ስላለው ክንድህ ሰምተው፣ በዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና ቢጸልዩ፣
|
|
\v 43 ከምትኖርበት ከሰማይ ሆነህ የዚያን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፣ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 44 ጠላቶቻቸውን ለመዋጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፣
|
|
\v 45 በሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማ፤ በችግራቸውም እርዳቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 46 ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምታደርግበት ጊዜ፣ ሩቅ ወይም ቅርብ ቢሆን፣
|
|
\v 47 ምርኮኞች ሆነው በሚኖሩባት በዚያች አገር ሳሉ ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለና፤ ዐምፀናል ብለው በመናዘዝ ተጸጽተው ንስሓ ቢገቡ፣
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 48 ማርከው በወሰዱአቸው በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸው በእውነትና በቅን መንፈስ ተጸጽተው ንስሓ በመግባት አንተ ለቀድሞ አባቶቻችን ወደ ሰጠሃቸው ወደዚህች ምድር፣ አንተም ወደ መረጥኻት ወደዚህች ከተማ፣ እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፣
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 49 ከዚያ በመኖሪያህ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውንና እርዳታ ፈልገው ሲለምኑህ በመስማት ፍረድላቸው፤
|
|
\v 50 ኃጢአታቸውንና አንተን ያሳዘኑበትን በደል ሁሉ ይቅር በል፤ ጠላቶቻቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 51 እነርሱ እንደ እቶን እሳት ከሚያቃጥል ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸውና የመረጥካቸው ሕዝብህ ናቸው፡፡
|
|
\v 52 በጠሩህ ጊዜ ሁሉ ትሰማቸው ዘንድ ለአገልጋይህና ለሕዝብህ ልመና ዓኖችህ የተገለጡ ይሁኑ፡፡
|
|
\v 53 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! የቀድሞ አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር ባወጣህ ጊዜ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ መካከል እስራኤልን የራስህ ሕዝብ እንዲሆን የመረጥከው መሆኑን በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት ተናግረሃል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 54 ሰሎሞንም እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ በመሠዊያው ፊት ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ቆይቶ ጸሎቱን ከፈጸመ በኋለ ተነሥቶ ቆመ፡፡
|
|
\v 55 ድምፁንም ከፍ አድርጎ በዚያ ተሰብስቦ የነበረውን ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ሲል ባረከ፡-
|
|
\v 56 በገባው የተስፋ ቃል. መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠው መልካም ተስፋ አንድም የቀረ ቃል የለም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 57 አምላካችን እግዚአብሔር ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር እንደነበረ ሁሉ ከእኛ ጋርም ይኑር፡፡ ምን ጊዜም አይተወን፤ አይጣለንም፡፡
|
|
\v 58 ለቀድሞ አባቶቻችን የሰጠውን ትዕዛዞች፣ ደንቦችና ሥርዓቶች በመጠበቅ ወደ እርሱ ልባችንን በማዘንበል ለእርሱ ታዛዦች እንድንሆን ያድርገን፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 59 የእኔ የአገልጋዩና የሕዝቡ የእስራኤል የየዕለት ፍላጎት ይሟላ ዘንድ ለእግዚአብሔር ያቀረብኳቸው ልመናዎች ቀንና ሌሊት ወደ እግዚአብሔር አምላክ ይቅረቡ፡፡
|
|
\v 60 የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ መሆኑንና ከእርሱም ሌላ አምላክ አለመኖሩን ያውቃሉ፡፡
|
|
\v 61 ስለዚህም በዛሬው ቀን በድንጋጌው ለመመላለስና ትእዛዞቹንም ታከብሩ ዘንድ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ለአምላካችን በልባችሁ ታማኞች ሁኑ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 62 ስለዚህ ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡
|
|
\v 63 ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ሃያ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፡፡ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው ቀደሱት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 64 አሁንም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጎ ቀደሰው፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፣ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 65 በዚያ ቤተ መቅደስ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ ባጠቃላይ ዐሥራ አራት ቀኖች የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝበ እጅግ ብዙ ነበር፡፡
|
|
\v 66 በሚቀጥለው ቀን ሰሎሞን ሕዘቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ፣ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 9
|
|
\p
|
|
\v 1 ንጉሥ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን እንዲሁም ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣
|
|
\v 2 እግዚአብሔር ከዚህ በፊት በገባዖን እንደ ተገጠለት አሁንም እንደገና ተገለጠለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም ዓይኔና ልቤ በዚያ ይሆናል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት በፊቴ ብትመላለስ፣ ሕጌንና ሥርዓቴን ብትጠብቅ፣ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፣
|
|
\v 5 ለአባትህ ለዳዊት ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አታጣም በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ዙፋንህ በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ነገር ግን አንተ ወይም ዘሮችህ እኔን መከተል ትታችሁ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትፈጽሙና ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩና ብትሰግዱላቸው፤
|
|
\v 7 እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህንን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ ይህንን አይተው በመደንገጥ እግዚአብሔር ይህንን አገርና ይህንን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ በማለት ይሳለቁበታል፡፡
|
|
\v 9 ራሳቸው በሚሰጡት መልስ፣ የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎች አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው የሚል ይሆናል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሃያ ዓመት ነበር፡፡
|
|
\v 11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ሃያ ታናናሽ ከተሞችን ለኪራም ሰጠው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ኪራምም ሄዶ ከተሞቹን አየ፤ ነገር ግን ደስ አላሰኙትም፤
|
|
\v 13 ኪራምም ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች እነዚህ ምንድን ናቸውን? አለው፡፡ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ አካባቢው በሙሉ «ካቡል» እየተባለ ይጠራል፡፡
|
|
\v 14 ኪራም ለንጉሥ ሰሎሞን የላከለት ወርቅ አንድ መቶ ሺህ መክሊት ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን፣ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ መጥተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ዋጋ ነበር፤ እንዲሁም ሐጸር፤ መጊዶናጊዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችም እንዲሠሩለት አደረገ፡፡
|
|
\v 16 ቀደም ሲል የግብጽ ንጉሥ ፈረዖን በጌዜር ላይ አደጋ ጥሎ፣ ነዋሪዎችዋን ከነዓናውያንን ገድሎ ከተማይቱንም አቃጥሎ በቁጥጥሩ ሥር አድርጓት ነበር፤ ከዚያም በኋላ ለሴት ልጁ ለሰሎሞን ሚስት እንደ ስጦታ ሰጣት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ሰሎሞንም ጊዜርንና የታችኛው ቤት ሖሮን እንደገና አሠራ፡፡
|
|
\v 18 ባዕላት በይሁዳ በረሓማ አገር የምትገኝ ታማር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንደገና ሠራ፡፡
|
|
\v 19 እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፣ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው ከተሞችን ሠራ፡፡ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፤ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 እነዚህም ትውልዶች የእስራኤል ወገን ያልሆኑና የሚያገለግሉ አሞራውያን፣ ሒታውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡
|
|
\v 21 ለሰሎሞን የጉልበት ሥራ ይሠሩለት የነበሩት የግዳጅ ሥራ ሠራተኞች እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በወረሱ ጊዜ የገደሏቸው የከነዓን ሕዝብ ተውልዶች ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ በዚህ ፈንታ እነርሱ ባለሥልጣኖች፣ ወታደሮች፣ የጦር መኮንኖች፣ የጦር አዛዦች፣ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኃላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኃምሳ ኃላፊዎች ነበሩአቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ የነበረችው ሚስቱ ከዳዊት ከተማ ራሱ ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከተዘዋወረች በኋላ ሰሎሞን የሚሎን ከተማ ገነባ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በዓመት ሦስት ጊዜ ያቀርብ ነበር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህም ዓይነት የቤተ መቅደሱ ሥራ ተፈጸመ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ በሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮን ጋብር መርከቦችን ሠራ፡፡
|
|
\v 27 ንጉሥ ኪራምም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር የሚያገለግሉ የሠለጠኑ መርከበኞችን ላከለት፡፡
|
|
\v 28 እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘውለት መጡ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 10
|
|
\p
|
|
\v 1 ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውንም ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡
|
|
\v 2 ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫነ ሽቶ፣ የከበረ ዕንቁና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በአሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጣት፤ ከጠየቀችው ሳይመልስላት የቀረ ምንም ዓይነት እንቆቅልሽ አልነበረም፡፡
|
|
\v 4 ንግሥተ ሳባ ጥበብ የተሞላበትን የሰሎሞንን አነጋገር አዳመጠች፤ የሠራውንም ቤተ መንግሥት አየች፡፡
|
|
\v 5 በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዓይነት፣ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፣ የቤተ መንግሥቱን አሠራርና አደረጃጃት፣ የደንብ ልብሳቸውን ዓይነት፣ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም ያቀረባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀቸው በላይ ሆነባት፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ስለሥራህ ውጤትና የጥበብህ ታላቅነት በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው አለች፡፡
|
|
\v 7 ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካይ ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ሁልጊዜ በፊትህ በመገኘት ጥበብ የሞላበት ንግግርህን የሚሰሙ ሚስቶችህና አገልጋዮችህ እንዴት የታደሉ ናቸው!
|
|
\v 9 አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ለዓላማው ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ንግሥተ ሳባ ያመጣችለትን ስጦታ ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን አበረከተችለት፤ ይኸውም ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ሽቶና የከበረ ዕንቁ ነበር፤ እርስዋ ለሰሎሞን ያበረከተችው የሽቶ ብዛት ከዚያ በኋላ ከቀረበለት የሽቶ ገጸ በረከት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ከኦፊር ወርቅ ብዙ ያመጡለት የኪራም መርከቦች ከዚያው ከኦፊር ብዙ የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቁ አምጥተውለት ነበር፡፡
|
|
\v 12 ሰሎሞን ከዚሁ ከሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፤ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አይታወቅም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ንጉሥ ሰሎሞን ከተለመደው የልግሥና ስጦታ ጋር የሳባ ንግሥት የጠየቀቸውን ሁሉ ሰጣት። ከዚህ በኋላ ንጉሥተ ሳባ ከክብር አጃቢዎችዋ ጋር ወደ አገርዋ ተመልሳ ሄደች፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ንጉሥ ሰሎሞን በየዓመቱ ሃያ ሦስት ሺህ ኪሎ ያህል የሚመዝን ወርቅ ያገኝ ነበር፤
|
|
\v 15 ይህም ሁሉ ነጋዶዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፤ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ አገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ታላላቅ ጋሻዎች አሠርቶ እያንዳንዱን ጋሻ በሰባት ኪሎ ያህል ወርቅ አስለበጠው፡፡
|
|
\v 17 እንዲሁም ሦስት መቶ ታናናሽ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን በሁለት ኪሎ ያህል ወርቅ አስለበጠው፤ እነዚህንም ሁሉ ሊባኖስ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ አኖራቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ከዝሆን ጥርስ አንድ ትልቅ ዙፋን አሠርቶ በንጹሕ ወርቅ አስለበጠው፡፡
|
|
\v 19 ወደ ዙፋኑ መወጣጫ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ የዙፋኑ ጀርባ ራስጌው ክብ ነበር፤ በዙፋኑ ግራና ቀኝ የክንድ ማሳረፊያዎች ነበሩት፤ በክንድ ማሳረፊያዎቹ ጎን አንዳንድ የአንበሳ ምስሎች ቆመው ነበር፡፡
|
|
\v 20 በእያንዳንዱ ደረጃ በሁለት በኩል አንዳንድ የአንበሳ ምስል በድምሩ ዐሥራ ሁለት የአንበሳ ምስሎች ቆመዋል፡፡ ይህን የመሰለ ዙፋን በሌላ በየትኛውም አገር ተሠርቶ አያውቅም ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 በሰሎሞን ዘመን ብር ምንም ዋጋ ስላልነበረው ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎች ሁሉና የሊባኖስ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ እንጂ ከብር አልተሠሩም፤
|
|
\v 22 ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱ በየሦስት ዓመት ወርቅ፣ ብር፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ንጉሥ ሰሎሞን ከምድር ነገሥታት ሁሉ የሚበልጥ ሀበታምና ጥበበኛ ነበር፤
|
|
\v 24 በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የሞላበትን ንግግር ይሰሙ ዘንድ ወደ እርሱ መምጣት ይፈልጉ ነበር፡፡
|
|
\v 25 ወደ እርሱም የሚመጡት ሁሉ የብርና የወርቅ፣ የልብስ፣ የጦር መሣሪያዎች፣ የሽቶ፣ የፈረሶች የበቅሎዎች ስጦታዎች ያመጡለት ነበር፤ ይህም በየዓመቱ የሚደረግ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ሰሎሞንም ሠረገሎችና ፈረሶች ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሎቹን ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፣ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፡፡
|
|
\v 27 በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፣ ብዛቱም እንደ ሊባኖስ ዛፍ፣ በይሁዳ ኮረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላም ይቆጠር ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 ሰሎሞን ፈረሶችን ከግብጽና ከቀዌ ያስመጣ ነበር፤ የንጉሡም ነጋዴዎች ፈረሶችን በገንዘብ ገዝተው ከቀዌ ያመጡለት ነበር፡፡
|
|
\v 29 እያንዳንዱ ፈረስ በስድስት መቶ ጥሬ ብር፣ እያንዳንዱም ሠረገላ በአንድ መቶ ሃምሳ ጥሬ ብር ከግብጽ አገር ተገዛ፡፡ ከዚያም ለሒታውያንና ለሶርያውያን ነገሥታት ተሸጡ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 11
|
|
\p
|
|
\v 1 ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ እነዚህም፡- የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ፣ የሒታውያን፣ የሞአባውያን፣ የአሞራውያን፣ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ፡፡
|
|
\v 2 እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን፣ አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደ ሆነ በእርግጥ ወደ አማልክቶቻቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፡፡ እነዚህ ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች እግዚአብሔር እንዳያጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፡፡ ይህ ትእዛዝ ቢኖርም ሰሎሞን ግን በእነርሱ ፍቅር ተነደፈ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቁባቶች ነበሩት፡፡ ሚስቶቹም ሰሎሞንን ከእግዚአብሔር እንዲርቅ አደረጉት፡፡
|
|
\v 4 በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልእክት እንዲሰግድ አደረጉት፡፡ ሰሎሞንም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሙሉ ልቡን ለእግዘአብሔር አላስገዛም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 የሲዶናውያን ሴት አምላክ የነበረችውን ለአስታሮትንና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን ተለይቶ የሚታወቀውን የአሞናውያንን አምላክ ተከተለ፡፡
|
|
\v 6 ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በማድረጉ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው እግዚአብሔርን በቅንነት አልተከተለም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን ሠራ፡፡
|
|
\v 8 እንዲሁም የባዕዳን አገር ሚስቶቹ ሁሉ ለየአማልክቶቻቸው ዕጣን የሚያጥኑባቸውንና መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸውን ስፍራዎች ሠራ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ የተገለጠለት ቢሆንም፣ ከእርሱ እየራቀ በመምጣቱ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቆጣው፡፡
|
|
\v 10 ባዕዳን አማልክትን እንዳያመልክ አዘዘው፡፡ ነገር ግን ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ስላፈረሰክና ሕጌንም ስላልፈጸምክ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ እሰጣለሁ፡፡
|
|
\v 12 ይሁን እንጂ ለአባትህ ለዳዊት ስል ይህን የማደርገው አንተ ባለህበት ዘመን ሳይሆን በልጅህ መንግሥት ጊዜ ይሆናል፡፡
|
|
\v 13 ሆኖም ሁሉንም መንግሥት አልወስድም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለመረጥኩት ከተማ ለኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንዱን ነገድ እሰጠዋለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ስለዚህም እግዚአብሔር የኤዶማውያኑን ነገሥታት ዘር ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ እርሱም ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ነበር፡፡
|
|
\v 15 ዳዊት ከኤዶማውያን ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ፣ የጦር አዛዡ ኢዮአብ ለመቅበር ወጥቶ በነበረበት ጊዜ፣ በኤዶም ወንዶች ሁሉ ተገድለው ነበር፡፡
|
|
\v 16 ኢዮአብና የእስራኤል ሠራዊት የኤዶምን ወንዶች ልጆች ገድለው እስኪጨርሱ ድረስ ስድስት ወራት በዚያ ቆይተዋል፡፡
|
|
\v 17 ነገር ግን ከሞት የተረፉትና ሀዳድ በአባቱ አገልጋዮች ወደ ግብጽ ተወሰዱ፡፡ በዚያን ጊዜ ሀዳድ ገና ሕፃን ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ሰዎችን ወደ ግብፅ ወደወሰዱበት ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሀዳድ ቤት፣ መሬትና ምግብ ሰጠው፡፡
|
|
\v 19 ሀዳድም በንጉሡ ፈርዖን ፊት ታላቅ ሞገስ አገኘ፡፡ ስለዚህ ንጉሡም የሚስቱን የጣፍኔስን እኅት ለሀዳድ ሚስት እንድትሆነው ሰጠው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 የጣፍኔስንም እኅት ጌንባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ለሀዳድ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከፈረዖንም ወንዶች ልጆች ጋር ኖረ፡፡
|
|
\v 21 ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ፣ ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ ሲል ፈረዖንን ጠየቀ፡፡
|
|
\v 22 ከዚያም ፈረዖን ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ የፈለግከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው? አለው፡፡ ሀዳድም ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ ሲል ለንጉሡ መለሰ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳ ልጅ በሰሎሞን ላይ ሌላ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከዞአብ ንጉሥ ከሀዲድዔዚር ኮብልሎ ነበር፡፡
|
|
\v 24 ዳዊት ሀዲድዔዚርን ድል ባደረገበት ጊዜ፣ ረዞን ለራሱ ጦር ሰብስቦ የጥቂት ኃይል አለቃ ሆኖ ነበር፡፡ የረዞን ጦር ወደ ደማስቆ ሄደው እዚያ መኖር ጀመሩ፤ በኋላም ደማስቆን ተቆጣጠረ፡፡
|
|
\v 25 በሰሎለሞን ዘመነ መንግሥት ሁሉ ሀዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ነበር፡፡ ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም፣ ኤፍሬማዊው የሰሎሞን ባለሥልጣናት አንዱ የሆነው፣ ጸሬዳ ተብሎ የምትጠራው ክፍል ተወላጅ የሆነ፣ የእናቱም ስም ጽሩዓ፣ ባልዋ የሞተባት ሴት ነበረች፤ እርሱም በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፡፡
|
|
\v 27 ኢዮርብዓም በሰሎሞን ላይ እጁን ያነሣበት ምክንያት፤ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥሮች እየጠገነ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 ኢዮርብዓም ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበር፡፡ ሰሎሞንም ይህን ተመልክቶ ወጣቱ ትጉህና ብርቱ ሠራተኛ በመሆኑ በዮሴፍ ነገድ ግዛት ላይ ሁሉ ኃላፊ አድርጎ ሾመው፡፡
|
|
\v 29 በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በጉዞ ላይ ሳለ፣ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያ በመንገድ ላይ አገኘው፡፡ አኪያም አዲስ መጎናጸፊያ ለብሶ ሁለት ሰዎች ለብቻ በሜዳ ላይ ነበሩ፡፡
|
|
\v 30 አኪያም የለበሰውን አዲስ መጎናጸፊያ አውልቆ ከዐሥራ ሁለት ቆራረጠው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚያብሔር እንዲህ ይላል፡- «ዐሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ ‹መንግሥትን ከሰለሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፣
|
|
\v 32 ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰለሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ፡፡
|
|
\v 33 ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን አማልክትን፡- አስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፣ ካሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን የአሞናውያን አምላክ ስላመለከ ነው፡፡ አባቱ ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ትክክል የሆነውን፣ ሕጎቼንና ትእዛዞቼንም አልጠበቀም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 ይሁን እንጂ ከሰለሞን እጅ መንግሥትን በሙሉ አልወስድበትም፤ በዚህ ፈንታ በሕይወት እስካለም ድረስ በሥልጣን ላይ እንዲቆይ አደርገዋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ለመረጥኩትና ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ለፈፀመው ለአገልጋዬ ለዳዊት ስል ነው፡፡
|
|
\v 35 ነገር ግን መንግሥትን ከሰለሞን ልጅ ወስጄ ለአንተ ዐሥሩን ነገዶች እሰጥሃለው፡፡
|
|
\v 36 ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 37 ኢዮርብዓም ሆይ! እኔ አንተን የእስራኤል ንጉሥ አድርጌሃለሁ፤ አንተ በወደድከው ግዛት ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ፡፡
|
|
\v 38 አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍፁም ልብህ ብትታዘዘኝ፣ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፣ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፣ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዓይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ፡፡
|
|
\v 39 በሰለሞን ኃጢአት ምክንያት የዳዊትን ትውልዶች እቀጣለሁ፤ ነገር ግን የምቀጣቸው ለዘላለም አይደለም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 40 ከዚህም የተነሣ ሰለሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፡፡ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በመኮበለል አመለጠ፤ ሰለሞን እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 ሰለሞን ያደረገው ሌላው ነገር፣ ያከናወነው ተግባርና ጥበቡ ሁሉ በሰለሞን የታሪክ መጽሐፍ የተመዘገበ አይደለምን?
|
|
\v 42 ሰለሞንም በኢየሩሳሌም በመላው እስራኤል ላይ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር፡፡
|
|
\v 43 ከዚህ በኋላ ሰለሞን ሞተ፣ በአባቱ በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በአባቱ በሰለሞን ተተክቶ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 12
|
|
\p
|
|
\v 1 ሮብዓምም ወደ ሴኬም ሄደ፤ ምክንያቱም እስራኤል ሁሉ እርሱን ለማንገሥ ወደ ሴኬም መጥተው ነበር፡፡
|
|
\v 2 ከንጉሡ ሰሎሞን በመሸሽ ወደ ግብጽ ኮብልሎ በዚያው በግብጽ ይኖር የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ወሬ በሰማ ጊዜ ተመልሶ መጣ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ስለዚህ የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ወደ እርሱ ልከው ጠሩት፤ ወደ ሮብዓም ቀርበው እንዲህ አሉት፡-
|
|
\v 4 አባትህ ሰሎሞን በእኛ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር አክብዶብን ነበር፡፡ አሁን አባትህ የጫነብንን ከባድ የሥራ ሸክም አቃልልን፣ ለአንተም እንገዛልሃለን አሉት፡፡
|
|
\v 5 ሮብዓምም ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ አላቸው፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የአባቱን የሰሎሞን ዘመን አማካሪዎች የነበሩትን ሽማግሌዎች በአንድነት ሰብስቦ እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ መልስ መስጠት እንድችል ምን ትመክሩኛላችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡
|
|
\v 7 ሽማግሌዎቹም ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ታዛዥ ሆነህ ብታገለግላቸው ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ ብተሰጣቸው እነርሱም ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል ሲሉ መለሱለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ነገር ግን ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ቸል በማለት አብሮ አደጎቹ ወደነበሩት አሁን ደግሞ አማካሪዎቹ ወደሆኑት ወጣቶች ሄደ፡፡
|
|
\v 9 የአገዛዝ ቀንበር እንዳቀልላቸው ለጠየቁኝ ምን መልስ እንደምሰጣቸው ምን ትመክሩኛላችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ አንተ የምተሰጣቸው መልስ ይህ ነው፤ የእኔ ታናሽ ጣት ከአባቴ ወገብ ይበልጥ ትወፍራለች!
|
|
\v 11 አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፣ እኔ ደግሞ የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፣ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን በሚናደፍ ጊንጥ እገርፋችኋለሁ!
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ከሦስት ቀን በኋላ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ንጉሡ በሰጣቸው ቀጠሮ መሠረት ተመልሰው ወደ ሮብዓም መጡ፡፡
|
|
\v 13 ንጉሥ ሮብዓምም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ ሕዝቡን በማመናጨቅ መልስ ሰጣቸው፡፡
|
|
\v 14 ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ! ሲል መለሰላቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ይህም ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። ነጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን አሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ሕዝቡ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየቤትህ ሂድ! ዳዊት ሆይ፣ የራስህን ቤት ጠብቅ ብለው መለሱለት፡፡ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ፡፡
|
|
\v 17 ሮብዓምም በይሁዳ ግዛት በሚኖሩት ሕዝብ ላይ ብቻ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኃላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህ ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ፡፡
|
|
\v 19 ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ሰሜናዊው ክፍል እስራኤል በሚል በዳዊት ሥርወ መንግሥት ላይ ዐመፀ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባዔያቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረው የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች ተውጣጥተው የተመለሱ አንድ መቶ ሰማኒያ ምርጥ ወታደሮች ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህም የእስራኤልን ነገዶች ለመዋጋትና እንደገና መንግሥትን ወደ ሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ለመመለስ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሳማያ እንዲህ ሲል መጣ፡፡
|
|
\v 23 ለሮብዓምና ለመላው የይሁዳና የብንያም ነገዶች ለቀሩትም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ በል፡-
|
|
\v 24 ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ጋር በመዋጋት አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነው በእኔ ፈቃድ ነው ብሎ አዘዘው፡፡ እነርሱም ለእግዚብሔር ቃል በመታዘዝ ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 ኢዮርብዓምም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን ሴኬምን ከተማ አድርጎ ሠርቶ ኖረባት፡፡ ከዚያም ተነሥቶ የጵንኤልን ከተማ ሠራ፡፡
|
|
\v 26 ኢዮርብዓምም አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል ብሎ በልቡ አሰበ፡፡
|
|
\v 27 ይህ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መስዋዕት የሚያቀርብ ከሆነ፣ የሕዝቡ ልብ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ጌታቸው ወደ ሮብዓም ይመለሳል፡፡ ከዚያ እኔን ይገሉኛል፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓምም ይመለሳሉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 ስለዚህ ሮብዓም በጉዳዩ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆች ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ ከዚህ በፊት እንደምታደርጉት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ አድካሚ ነው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፡- ከግብጽ ምድር ያወጣችሁ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው! አለ፡፡
|
|
\v 29 ከዚህ በኋላ ከወርቅ የተሠሩት ሁለት የኮርማ ምስሎች አንዱን በቤቴል ሁለተኛውንም በዳን አቆመ፡፡
|
|
\v 30 ስለዚህ ይህ ድርጊት ኃጢአት ሆነ፡፡ ሰዎቹም እስከ ዳን ድረስ በጣዖቱ ፊት ተሰልፈው ሄዱ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 ኢዮርብዓምም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተ ሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ፡፡
|
|
\v 32 ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዓይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራውም ምስሎች በቤቴል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምሰሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚህም በቤተል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 ኢዮርብዓምም በዓል እንዲሆን እርሱ ራሱ በወሰነው ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ወደ ቤቴል ሄደ፡፡ በዚያ የእስራኤል ሕዝብ በዓል እንዲያከብር መስዋዕት አዘጋጅቶ ዕጣን ለማጠን ወደ መሠዊያው ሄደ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 13
|
|
\p
|
|
\v 1 የእግዚአብሔርን ቃል ይዞ አንድ ነብይ ከይሁዳ ወደ ቤቴል ደረሰ፤ ኢዮርብዓም ዕጣን ለማጠን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡
|
|
\v 2 ነቢዩም እንዲህ ሲል በጩኸት የትንቢት ቃል ተናገረበት፡- «መሠዊያ! መሠዊያ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ አንተ የሚለው ቃል ይህ ነው፡- ‹እነሆ ከዳዊት ቤተ ሰብ ኢዮአስ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ይወለዳል፤ እርሱም በኮረብታ ላይ ለተሠራው ለአህዛብ መሠዊያ አገልጋዮች ሆነው መሥዋዕት የሚያቀርቡትን ካህናት በአንተው ላይ ያርዳቸዋል፤ የሰዎችንም አጥንት በአንተ ላይ ያቃጥላል፡፡
|
|
\v 3 በዚያው ቀን ነቢዩ ምልክት ሰጠ፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ ያለው አመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካኝነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር ለመሆኑ ምልክት ይሆናል›» አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 ንጉሥ ኢዮርብዓምም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት ያዙት የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲውኑ ድርቅ ብሎ ቀረ፤ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም፡፡
|
|
\v 5 የእግዚአብሔርም ነቢይ በእግዚአብሔር ስም በተናገረው የትንቢት ቃል መሠረት የተሰጠው ምልክት ተፈጸመ፤ መሠዊያው ወዲያውኑ ተሰባብሮ ወደቀ፤ አመዱም መሬት ላይ ፈሰሰ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ንጉሡ ኢዮርብዓምም፣ እባክህ እጄ እንዲመለስልኝ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልኝ ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው፡፡ የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፡፡ እንደ ቀድሞም ሆነች፡፡
|
|
\v 7 ከዚህ በኋላ ንጉሡ ነቢዩን ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 የእግዚአብሔር ነቢይ ግን የሀብትህን እኩሌታ ብትሰጠኝ እንኳ ወደ ቤትህ ከአንተ ጋር አልሄድም፤ እህል ውሃም እዚህ ቦታ አልቀምስም አለ፡፡
|
|
\v 9 ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳልቀምስና ወደ ቤቴ ስመለስም በመጣሁበት መንገድ እንኳ እንልሄድ እግዚአብሔር አዞኛል ሲል መለሰለት፡፡
|
|
\v 10 ስለዚህ ወደ ቤቴል የመጣበትን መንገድ በመተው በሌላ መንገድ ተመልሶ ሄደ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 በዚያን ጊዜ በቤቴል የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ነበር፡፡ ወንዶች ልጆቹ ወደ እርሱ ቀርበው፣ ከይሁዳ የመጣው ነቢይ በቤቴል ስላደረገውና በንጉሥ ኢዮርብዓምም ላይ ስለ ተናገረው ቃል ሁሉ አወሩለት፡፡
|
|
\v 12 አባታቸውም ታዲያ ያ የእግዚአብሔር ነቢይ ከዚያ ተነሥቶ በየትኛው መንገድ ሄደ? ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱም የሄደበትን መንገድ በማመልከት አሳዩት፤
|
|
\v 13 ከዚህም በኋላ እርሱ አህያዬን ጫኑልኝ አላቸው፤ ልጆቹም አህያውን ጭነውለት፣ ሽማግሌው ነቢይ በአህያው ላይ ተቀምጦ፣
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው፡፡ ሽማግሌውም ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነሀን? ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም አዎን እኔ ነኝ ሲል መለሰለት፡፡
|
|
\v 15 ሽማግሌውም ወደ ቤቴ ገብተህ ከእኔ ጋር እህል ብላ አለው፡፡
|
|
\v 16 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ግን ከአንተ ጋር አብሬ ወደ ቤትህ መሄድም ሆነ በዚህ ቦታ ከአንተ ጋር ምንም ዓይነት እህል ውሃ መቅመስ አልችልም ሲል መለሰለት፡፡
|
|
\v 17 በዚህ ቦታ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳልቀምስ፣ በመጣሁበት መንገድ እንኳ ተመልሼ እንዳልሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ከዚህ በኋላ ከቤቴል የመጣው ሽማግሌው ነቢይ፣ እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል አለው፡፡ ነገር ግን ሽማግሌው ነቢይ የተናገረው በውሸት ነበር፡፡
|
|
\v 19 ስለዚህ ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ከሽማግሌው ነቢይ ጋር አብሮት ወደ ቤቱ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ተመገበ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 በገበታም ቀርበው ሳሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሽማግሌው ነቢይ መጣ፡፡
|
|
\v 21 ከይሁዳ ለመጣው የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አልታዘዝክም፡፡
|
|
\v 22 ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ወዳዚያ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተ ሰብህ መቃብር አይቀበርም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ከተመገቡም በኋላ ሽማግሌው ነቢይ ከይሁዳ መልሶ ላመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ አህያውን ጫነለት፤
|
|
\v 24 እርሱም በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ በመንገድም አንበሳ አገኘውና ገደለው፤ ሬሳውም በመንገድ ላይ ተጋደመ፤ አህያውና አንበሳውም በሬሳው አጠገብ ቆመው ነበር፡፡
|
|
\v 25 ሰዎች በዚያ በኩል ሲያልፉ አጠገቡ ከቆመው አንበሳ ጋር ሬሳው በመንገድ ላይ ተጋድሞ አዩ፣ ሽማግሌው ነቢይ ወደሚኖርበት ወደ ቤቴል ከተማ መጥተውም አወሩለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ሽማግሌው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ፣ ያ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ያልጠበቀው ነቢይ ነው፤ ስለዚህም እግዚአብሔር እንደ ተናገረው አንበሳ ቦጫጭቆ እንዲገለው አሳልፎ ሰጥቶታል ማለት ነው አለ፡፡
|
|
\v 27 ከዚህም በኋላ ልጆቹን አህያዬን ጫኑልኝ አላቸው፤ እነርሱም ጫኑለት፡፡
|
|
\v 28 በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ በነቢዩ ሬሳ አጠገብ አህያውና አንበሳው እስካሁን እንደ ቆሙ በመንገድ ላይ ተጋድሞ አገኘው፡፡ አንበሳውም የነቢዩን ሬሳ አልበላም፤ በአህያውም ላይ አደጋ አላደረሰበትም ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ሽማግሌው ነቢይ ሬሳውን አንሥቶ በአህያው ላይ ጫነው፤ እንዲለቀስለትና እንዲቀበር ወደ ቤቴል መልሶ ወሰደው፡፡
|
|
\v 30 ሽማግሌውም ነቢይ በገዛ ራሱ ቤተ ሰብ መቃብር ቀበረው፤ እነርሱም ወንድሜ ሆይ ወንድሜ ሆይ እያሉ አለቀሱለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 ከቀብሩም ሥነ ሥርዓት በኋላ ሽማግሌው ነቢይ ለልጆቹ እንዲህ አላቸው፤ እኔ ስሞት በዚህ መቃብር ቅበሩኝ፤ ሬሳዬንም ከእርሱ ሬሳ አጠገብ አጋድሙት፡፡
|
|
\v 32 በቤቴል በሚገኘው መሠዊያ ላይና በሰማርያ ታናናሽ ከተሞች በየኮረብታው ባሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ የተናገረው የትንቢት ቃል በእርግጥ ይፈጸማል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 ይህም ሁሉ ሆኖ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ከሚያደርገው ክፉ ነገር ሁሉ አልተመለሰም፤ ይልቁንም እርሱ በሠራቸው መሠዊያዎች የሚያገለግለውን ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ይሾመው ነበር፡፡
|
|
\v 34 ይህም ኃጢአቱ ለቤተ ሰቡ መጥፋትና ከምድር ገጽ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 14
|
|
\p
|
|
\v 1 በዚያን ጊዜ የንጉሥ ኢዮርብዓም ወንድ ልጅ አቢያ በጠና ታሞ ነበር፡፡
|
|
\v 2 ስለዚህ ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፡- የእኔ ሚስት መሆንሽን ማንም እንዳያውቅ ልብስሽን ለውጠሽ ሌላ ሴት በመምሰል እኔ የእስራኤል ንጉሥ እንደምሆን የትንቢት ቃል የተናገረው ነቢይ አኪያ ወደሚኖርባት ወደ ሴሎ ሂጂ፡፡
|
|
\v 3 ዐሥር እንጀራ፣ ጥቂት ሙልሙል ዳቦና አንድ ገንቦ ማር ውሰጂለት፤ ስለ ልጁ ሁኔታ እርሱ ይነግርሻል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ይህን ሁሉ አዘጋጅታ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች፡፡ ነቢዩ አኪያም በዕድሜው ከመሸምገሉ የተነሣ ዓይኖቹ ፈዘው ስለነበር ለማየት አልቻለም፡፡
|
|
\v 5 እግዘዚአብሔር ለአኪያ እንዲህ አለው፡- የኢዮርብዓም ሚስት ስለታመመው ልጅዋ ልትጠይቅህ እየመጣች ነው፡፡ የኢዮርብዓም ሚስት እዚያ በደረሰች ጊዜ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምትሞክር ይህንኑ ተናገራት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ነገር ግን ነቢዩ አኪያ ወደ በሩ ስትቀርብ የኮቴን ድምፅ ሰምቶ እንዲህ አላት፤ ግቢ፣ የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን አውቃለሁ፤ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምን ሞከርሽ? ለአንቺ እነግርሽ ዘንድ የታዘዝኩት አሳዛኝ ዜና አለ፡፡
|
|
\v 7 ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‹ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፡፡
|
|
\v 8 መንግሥትንም ከዳዊት ትውልድ ወስጄ ለአንተ ሰጠሁህ፤ ነገር ግን አንተ ታማኝ ሆኖ ትእዛዜን እንደጠበቀውና እኔ ደስ የምሰኝበትን እንዳደረገ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ሆነህ አልተገኘህም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችንና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን ለማምለክ በመነሣትህ ቁጣዬን አነሣሥተሃል፡፡
|
|
\v 10 በዚህ ምክንያት እነሆ፣ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነፃም ሆነ ባርያ ወንድ ልጅን ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 በከተማ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተ ሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞቱንም የሰማይ አሞራ ይበላቸዋል፤ ይህን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡”
|
|
\v 12 አኪያም የሚናገረውን የትንቢት ቃል በመቀጠል ለኢዮርብዓም ሚስት እንዲህ አላት፣ እንግዲህ አሁን ወደ ቤትሽ ተመልሰሽ ሂጂ፤ ወደ ከተማም እግሮችሽ እንደረገጡ ወዲያውኑ ልጁ ይሞታል፡፡
|
|
\v 13 እስራኤላውያንም ሁሉ አዝነውና አልቅሰው ይቀብሩታል፡፡ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተደሰተበት ልጅ እርሱ ብቻ ስለሆነ ከኢዮርብዓም ቤተ ሰብ ሥርዓተ ቀብር በሚገባ የሚፈፀምለት እርሱ ብቻ ይሆናል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 እግዚአብሔርም በዚያን ቀን የኢዮርብዓምን ቤት የሚያጠፋ ንጉሥ ያስነሣል፡፡ ይኸውም አሁን ነው፡፡
|
|
\v 15 እግዚአብሔር እስራኤልን ይቀጣል፤ እርሱም በውሃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸንበቆ ይወዛወዛል፡፡ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ጣዖት በመሥራት እግዚአብሔርን ስላስቆጡት፣ የእስራኤልን ሕዝብ ቀድሞ ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው መልካም ምድር ይነቅላል፤ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲበታተኑም ያደርጋል፡፡
|
|
\v 16 ኢዮርብዓም ኃጢአት ከመሥራቱ የተነሣና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ስለመራ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ይተዋል፡፡»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ተነሥታ ወደ ቲርሳ ተመልሳ ሄደች፡፡ ወደ ቤትዋ ደጃፍ አንደ ደረሰች ወዲያውኑ ልጁ ሞተ፡፡
|
|
\v 18 እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያ በኩል በነገረው መሠረት እስራኤላውያን በሐዘን አልቅሰው ቀበሩት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 ንጉሥ ኢዮርብዓም ያደረጋቸው ሌሎች ነገሮች ሁሉ፣ የተዋጋቸው ጦርነቶችና አገዛዙም እንዴት እንደ ነበር ሁሉም ነገር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
|
|
\v 20 ኢዮርብዓም ለሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ ከአባቶቹም ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ናዳብ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔር ከመላው የእስራኤል ነገዶች ለስሙ መጠሪያ እንድትሆን በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም መኖሪያውን አድርጎ ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ፡፡ የሮብዓምም እናት አሞናዊት ስትሆን፣ ስምዋም ናዕማ ነበር፡፡
|
|
\v 22 የይሁዳ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው ሲያደርጉት ከነበረው ይበልጥ ክፉ ነገር በማድረጋቸው የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፍ ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርፆችና የኤሼራን ምስሎች አቆሙ፡፡
|
|
\v 24 ከእነዚህም ሁሉ የከፋ በእነዚያ ሕዝቦች የማምለኪያ ስፍራዎች የቤተ ጣዖት አመንዝራዎች ነበሩ፡፡ አሕዛብ ይፈፅሙት የነበረውን እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ነቃቅሎ ያባረራቸውን አሳፋሪ ነገር ሁሉ ይፈፅሙ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ፡፡
|
|
\v 26 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፣ ሰለሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 እነርሱንም ለመተካት ንጉሥ ሮብዓም ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጥር በር በሚጠብቁ አለቆች እንዲጠበቁ አደረገ፡፡
|
|
\v 28 ንጉሡ ወደ ቤተ መቅደሱ በመጣ ቁጥር፣ የቤተ መቅደሱ ዘበኞች ጋሻዎችን አንግበው ይቀበሉታል፤ ከሄደም በኋላ ጋሻዎቹን መልሰው ዘበኞች በሚጠበቁበት ማከማቻ ያኖሩ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
\v 30 በዚህም ዘመን ሁሉ ሮብዓምና ኢዮርብዓም እርስ በርሳቸው በማያቋርጥ ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡
|
|
\v 31 ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታቱ መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ ልጁም አቢያ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 15
|
|
\p
|
|
\v 1 ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አቢያ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
|
|
\v 2 እርሱም በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ማዕካ ሲሆን፣ እርስዋም የአቤሴሎም ልጅ ነበረች፡፡
|
|
\v 3 አቢያም እንደ ቀደሙት አባቶቹና እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ ፍፁም ታማኝ ሆኖ አልተገኘም፡፡ አባቱ ሮብዓም ይፈፅመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራት ቀጠለ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 የሆነ ሆኖ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም እንዲያጠናክር አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው፡፡
|
|
\v 5 እግዚአብሔር ይህንን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሂታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር በእግዚአብሔር ፊት በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ትክክለኛ ነገር አድርጎአል፤ ከትእዛዙም ፈቀቅ አላለም፡፡
|
|
\v 6 በሮብዓምና ኢዮርብዓም ዘመን ተጀምሮ የነበረው ጦርነት፣ በአቢያ ዘመነ መንግሥትም ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 አቢያ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
\v 8 አቢያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ልጁ አሳ ተተክቶ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በሃያኛው ዓመት አሳ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
|
|
\v 10 እርሱም በኢየሩሳሌም አርባ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ አያቱም ማዕካ ተብላ የምትጠራ የአቤሌሎም ልጅ ነበረች፡፡
|
|
\v 11 አሳም አያቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኝ ነገር ሠራ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ንጉሥ አሳ የቤተ ጣዖት አመንዝራዎችን ሁሉ ከአገሩ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖታት ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ፡፡
|
|
\v 13 አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አስጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሽሮ ከቤተ መንግሥት አስወጣት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 አሳ በኮረብቶች ላይ የሚገኙ የአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎችን በሙሉ አላስወገደም፤ ይሁን እንጂ በዘመኑ ሁሉ የአሳ ልብ ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ፍጹም ነበር፡፡
|
|
\v 15 አባቱ ለእግዚአብሔር ቤት የተለዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸውንና እርሱም ራሱ የለያቸውን ወርቅና ብር አሠርቶ ንዋያተ ቅዱሳትን ሁሉ በቤተ መቅደስ አኖረ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 የይሁዳ ንጉሥ አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በሥልጣን በነበሩበት ዘመን ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነት ነበር፡፡
|
|
\v 17 የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ማንም ሰው አሳ በሚገዛበት በይሁዳ ምድር እንዳይወጣና እንዳይገባ ለመከላከል ራማን ምሽግ አድርጎ መሥራት ጀመረ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ከዚያም ንጉሥ አሳ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ የተረፈውን ወርቅና ብር ሁሉ ወሰደ፡፡ እርሱም በአገልጋዮቹ እጅ በደማስቆ ከተማ ለነበረው የአዚን ልጅ የጣብሪሞን ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ ስጦታ አድርጎ ላከለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፡-
|
|
\v 19 የእኔ አባትና የአንተ አባት ያደርጉት በነበረው ዓይነት በመካከላችን ቃል ኪዳን ይኑር፡፡ እነሆ ብርና ወርቅ ስጦታ እንዲሆንህ ልኬልሃለሁ፡፡ የእሰራኤል ንጉሥ ባኦስ እኔን እንዲለቀኝ ቀደም ሲል ከእርሱ ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን አሁን እንድታቋርጥ ይሁን፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 ንጉሥ ቤን ሀዳድም አሳ ባቀረበው አሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላከ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፡፡ እነርሱም ዒዮን፣ ዳን፣ አቤልቤተማሪካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩ ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘው አገርና የንፍታሌም ግዛት ሁሉ ናቸው፡፡
|
|
\v 21 ንጉሥ ባኦስ የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ የራማን ምሽግ መሠራት እንዲቆም አድርጎ ወደ ቲርጻ ሄደ፡፡
|
|
\v 22 ከዚህም በኋላ ንጉሥ አሳ ባኦስ ራማን ለመመሸግ አከማችቶት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ከዚያ ለማንሣት እንዲረዳው ሕዝቡ አንድም ሳይቀር እንዲመጣ ወደ ይሁዳ ግዛቶች ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ንጉሥ አሳ ከዚያ የተገኘውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ወስዶ በምጽጳና በብንያም ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የጌባዕን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራበት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ንጉሥ አሳ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራውና የሠራቸውም ከተሞች በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? ንጉሥ አሳ በዕድሜ በሸመገለ ጊዜ ከእግሩ ሕመም የተነሣ ሽባ ሆኖ ነበር፡፡
|
|
\v 24 ንጉሥ አሳም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መቃብር ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮሣፍጥ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የአዮርብዓም ልጅ ናዳብ የእስረኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡
|
|
\v 26 ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት በመሥራት የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባኦስ ናዳብን ድል አድርጎ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ፡፡
|
|
\v 28 ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነው፤ በዚህ ዓይነት ባኦስ በናዳብ ፈንታ ተተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ንጉሥ ባኦስ እንደነገሠ ወዲያውኑ የኢዮርብዓምን ቤተ ሰብ በሙሉ ገደለ፡፡ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሴሎኣዊው በነቢዩ አኪያ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት የኢዮርብዓም ወገን በሙሉ ተገደሉ፡፡ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም፤
|
|
\v 30 ይህም የሆነበት ምክንያት ኢዮርብዓም ራሱ በሠራው ኃጢአትና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ ስላነሣሣ ነው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 ናዳብ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
\v 32 የይሁዳ ንጉሥ አሳ እና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በሥልጣን ዘመናቸው ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፡፡ እርሱም በቲርጻ ሃያ አራት ዓመት ገዛ፡፡
|
|
\v 34 ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ባኦስ ኃጢአት በመሥራትና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 16
|
|
\p
|
|
\v 1 በሐናኒ ልጅ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት እግዚአብሔር ስለ ባኦስ የተናገረው ቃል እንዲህ ሲል መጣ፡-
|
|
\v 2 እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ እንድትሆን ከፍ ከፍ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቁጣ አነሣሥቶአል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ስለዚህ ኢዮርብዓምን እንዳሰወገድኩ አንተንና ቤተ ሰብህንም አስወግዳለሁ፡፡
|
|
\v 4 በከተማይቱ ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም የባኦስ ቤተ ሰብ ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውንም የሰማይ አሞራዎች ይበሉታል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ባኦስ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራዎቹም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
\v 6 ባኦስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቲርጻም ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኤላ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤተ ሰቡ ላይ የትንቢት ቃል የተናገረው፣ ባኦስ በፈጸመው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ በማድረጉ ነበር፡፡ ባኦስ እግዚአብሔርን ያስቆጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዓይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተ ሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ስድስተኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላ በእስራኤል መንገሥ ጀመረ፡፡ በቲርጻም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡
|
|
\v 9 የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኃላፊ የሆነ ዚምሪ ከጦር መኮንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፡፡ ኤላም በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፡፡
|
|
\v 10 በዚህ ጊዜ ዚምሪ ወደዚያ ቤት ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ ፈንታ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ተተክቶ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ዘምሪም በዙፋን ላይ እንደተቀመጠ ወዲያውኑ የባኦስ ቤተ ሰብ አባላት የሆኑትን በሙሉ ገደለ፤ የባኦስ ዘመድና ወዳጅ የሆነውን ወንድ አንድ እንኳ ሳይቀር ሁሉንም በሞት ቀጣ፡፡
|
|
\v 12 እግዚአብሔር ነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ በተናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባኦስን ቤተ ሰብ በሙሉ ፈጀ፡፡
|
|
\v 13 ይህም የሆነበት ምክንያት ባኦስና ልጁ ኤላ ጣዖት በማምለካቸውና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራታቸው፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ በማነሣሣታቸው ነው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ኤላ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀኖች ብቻ በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡ በዚያን ጊዜ የአስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከበው ነበር፡፡
|
|
\v 16 ዘምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን በሰሙ ጊዜ በዚያው እንዳሉ ወዲያውኑ የጦር አዛዥ የነበረውን ዖምሪን አነገሡ፡፡
|
|
\v 17 ዖምሪና ወታደሮቹ የገባቶንን ከበባ አቆሙ፤ ከዚያም ገሥግሠው ሄደው ቲርጻን ከበቡ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ዘምሪ ከተማይቱ እንደተያዘች ባየ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ ክፍል ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበት፤ እርሱም በእሳት ነበልባል ተቃጥሎ ሞተ፡፡
|
|
\v 19 ይህ የሆነው እርሱ በሠራው ኃጢአትና እስራኤልንም ወደ ኃጢአት በመምራቱ ምክንያት ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም እግዚአብሔርን ስላስቆጣው ነው፡፡
|
|
\v 20 ዘምሪ የሠራው ሌላው ነገር ሁሉና ያደረገውም ሤራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ የሚገኝ አይደለምን?
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ከሁለት ተከፍለው ነበር፡፡ ከዚህም የተነሣ አንደኛው ክፍል ታምኒን ተብሎ የሚጠራውን የጎናትን ልጅ ለማንገሥ ሲፈልግ ሌላው ክፍል ደግም ዖምሪን ለመደገፍ ይፈልግ ነበር፡፡
|
|
\v 22 ነገር ግን የዖምሪ ተከታዮች ከጎናት ልጅ ታምኒን ይልቅ ጠንካራ ነበሩ፡፡ ስለዚህም ታምኒን ተገደለ፤ ዖምሪም ንጉሥ ሆነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 በዚህ ዓይነት አሳ በይህዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መቀመጫውን በቲርጻ አድርጎ ነበር፡፡
|
|
\v 24 ከዚያም በኋላ ሳምር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያ ኮረብታን በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛው፡፡ ዖምሪ በኮረብታው ላይ ከተማ ቆረቆረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ሰየማት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 ዖምሪ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ነገሥታት ይበልጥ የከፋ ኅጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
|
|
\v 26 እርሱ በሠራው ኃጢአትና አስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራት ዋጋ ወደሌላው ጣዖት አምልኮ መምራቱ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 ዖምሪ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉና ያከናወነውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
\v 28 ዖምሪም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አክዓብ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ነገሠ። የዖምሪ ልጅ አክዓብ በሰማርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ፤
|
|
\v 30 የዖምሪ ልጅ አክዓብ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ የባሰ ክፉ ነገር በያህዌ ፊት አደረገ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 አክዓብ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኅጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም፡፡
|
|
\v 32 በሰማርያ ለባዓል ቤተ መቅደስ አሠርቶ መሠዊያ ሠራለት፡፡
|
|
\v 33 አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስል አቆመ፤ ከእርሱ በፊት ከነበሩትም የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚያነሣሣ ኃጢአት ሠራ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 በአክዓብ ዘመነ መንግሥት አኪኤል ተብሎ የሚጠራ የቤቴል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት አኪኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ በነዌም ልጅ በኢያሱ እንደ ተነገረው እንደ እግዚብሔር ቃል፣ የበኩር ልጁ አቢሮን ሞተበት፤ የቅጥርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 17
|
|
\p
|
|
\v 1 በገለዓድ የምትገኘው ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ነጉሥ አክዓብን በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 2 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
|
|
\v 3 ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ እዚያም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ኮራት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሽግ፡፡
|
|
\v 4 የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቁራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ኤልያስም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሄዶ በኮራት ሸለቆ ተቀመጠ፡፡
|
|
\v 6 ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቁራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፡፡
|
|
\v 7 ነገር ግን ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 የእግዚአብሔርም ኤልያስን እንዲህ አለው፡-
|
|
\v 9 እንግዲህ አሁን ከዚህ ተነሥተህ ሂድ፤ በሲዶና በምትገኘው በስራፕታ ከተማ ተቀመጥ፤ እነሆ በዚያ የምትኖር አንዲት መበለት እንድተመግብህ እዝዣለሁ አለው፡፡
|
|
\v 10 ስለዚህ ኤልያስ ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም ቅጥር በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባልዋ የሞተባት ሴት እንጨት ስተለቅም አይቶ እባክሽ የምጠጣው ውሃ አምጪልኝ አላት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ውሃም ልታመጣለት በመሄድ ላይ ሳለች ወዲያውኑ ጠርቶ እባክሽ በተጨማሪ ትንሽ እንጀራ አምጪልኝ አላት፡፡
|
|
\v 12 እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፡- ምንም እንጀራ እንደሌለኝ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ በዱቄት ዕቃዬ ውስጥ ካለችው ከአንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮዬ ውስጥ ካለችው ከጥቂት የወይራ ዘይት በቀር ምንም የለኝም፤ ወደዚህ የመጣሁት ትንሽ እንጨት ለቃቅሜ ቤቴ በመመለስ ይህችኑ ትንሽ ዱቄት ለእኔና ለልጄ ለመጋገር ነው፤ ይህችም የመጨረሻ ምግባችን ናት፤ ከዚያ በኋላ ይህችኑ በልተን እንሞታለን፡፡
|
|
\v 13 ኤልያስም እንዲህ አላት፣ አይዞሽ አትጨነቂ፤ ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚች ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጎቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማስቀመጫው ዕቃ፣ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም ሲል ተናግሮአል፡፡
|
|
\v 15 አርስዋም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ እርስዋ፣ ቤተ ሰብዋና ኤልያስ ለብዙ ቀን የሚሆን በቂ ምግብ አገኙ፡፡
|
|
\v 16 እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፣ ዘይቱም ከማሰሮው አላለቀም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ከጥቂት ጊዜም በኋላ የዚያች ባልዋ የሞተባት ሴት ልጅ ታመመ፤ ሕመሙም እየባሰበት ስለ ሄደ በመጨረሻ ሞተ፡፡
|
|
\v 18 እርስዋም ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን? ስትል ጠየቀችው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 ኤልያስም ልጅሽን ወደ እኔ አምጪው አላት፡፡ ልጁንም ከዕቅፍዋ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት አውጥቶ በአልጋው ላይ አጋደመው፡፡
|
|
\v 20 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ስለምን በዚህች ባልዋ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርስዋ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጅዋ እንዲሞት አደረግህ ሲል ጸለየ፡፡
|
|
\v 21 ከዚህ በኋላ ኤልያስ በልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ተዘርሮ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ይህን ልጅ ከሞት አስነሣው ሲል ጸለየ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 እግዚአብሔርም የኤልያስን ጸሎት ሰማ፤ የልጁም እስትንፋስ እንደገና ተመልሶለት ዳነ፡፡
|
|
\v 23 ኤልያስም ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ ሰጣትና እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል! አላት፡፡
|
|
\v 24 እርስዋም እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና እግዚአብሔርም በአንተ አማካይነት የተናገረው እውነት መሆኑን አሁን ዐወቅሁ! ስትል መለሰችለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 18
|
|
\p
|
|
\v 1 ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡- ሄደህ ራስህን ለንገሥ አከዓብ ግለጥለት እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ አለው፡፡
|
|
\v 2 ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አከዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሃብ እጅግ ጸንቶ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራው፤ አብድዩ እግዚአብሔርን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነበር፡፡
|
|
\v 4 ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረበት ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ መግቦአቸው ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 አከዓብ አብድዩን ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፡፡ ምናልባት እንስሳትን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል አለው፡፡
|
|
\v 6 እያንዳንዳቸው በአገሪቱ ወደየትኛው ክፍል ሄደው መፈለግ እንዳባቸው ከተስማሙ በኋላ አክዓብና አብድዩ ለየብቻቸው በሁለት አቅጣጫ ተሰማሩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 አብድዩ በሚሄድበት መንገድ ላይ ሳለ በድንገት ኤልያስን አገኘው፤ ኤልያስ መሆኑንም ስላወቀ በግንባሩ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ከነሣው በኋላ ጌታዬ ኤልያስ በእውነት አንተ ነህን? ሲል ጠየቀው፡፡
|
|
\v 8 ኤልያስም አዎን እኔ ነኝ፤ እዚህ መሆኔን ሄደህ ለጌታህ ንገረው ሲል መለሰለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 አብድዩም እንዲህ አለው፤ ንጉሥ አክዓብ እኔን ባሪያህን ይገድለኝ ዘንድ በእጁ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን በደል ሠርቼ ነው?
|
|
\v 10 ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርህን ለንጉሥ አክዓብ በመሐላ እያረጋገጠለት ቆይቶአል፡፡
|
|
\v 11 አሁን አንተ ግን ኤልያስ ተገኝቶአል ብለህ ለጌታህ ንገር ትለኛለህ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርህን ለአከዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ፡፡
|
|
\v 13 ደግሞስ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን?
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ታዲያ፣ አሁን አንተ እዚህ መሆንህን ሄደህ ለንጉሥ አክአብ ንገር ትለኛለህን? ይህን ባደርግ ንጉሡ ይገድለኛል!»
|
|
\v 15 ኤልያስም «ዛሬ ለንጉሡ እንደምገለጥለት በማገለግለውና ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዞአብሔር ስም ቃል እገባልሃለሁ!» ሲል መለሰለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ከዚህ በኋላ አብድዩ ሄዶ ለንጉሥ አክዓብ ነገረው፤ አክዓብም ተነሥቶ ኤልያስን ለመገናኘት ሄደ፤
|
|
\v 17 አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜም «በእስራኤል ላይ ይህን ችግር ያመጣህ አንተ እዚህ ነህን?» አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፡- «የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተ ሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
|
|
\v 19 ይልቅስ እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው አራት መቶ ሃምሳ የበዓል ነቢያትንና በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ የኤሼራ ነቢያትን በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፡፡»
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 ስለዚህም አክዓብ ለእስራኤላውያን ሁሉና ለነቢያት በሙሉ ጥሪ አድርጎ በቀርሜሎስ ተራራ እንዲሰበሰቡ አስደረገ፡፡
|
|
\v 21 ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፡- «እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!» አላቸው፡፡ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፡- «ከእግዚአብሔር ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፡፡
|
|
\v 23 እንግዲህ ሁለት ኮርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቆራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን እሳት አያድርጉበት፡፡ እኔም ሁለተኛውን ኮርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ፡፡
|
|
\v 24 ከዚህ በኋላ የባዓል ነቢያት ወደ አምላካቸው ይጸልዩ፤ እኔም ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እሳትን ወደ መሥዋዕቱ በመላክ መልስ የሚሰጥ እርሱ እውነተኛ አምላክ ይሁን፡፡ ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድረጎ ይህ መልካም ነው በማለት መልስ ሰጡ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 ከዚህ በኋላ ኤልያስ የባዓልን ነቢያት እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ኮርማ መርጣቸሁ በማረድ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ፤ ነገር ግን እንጨቱ ላይ እሳት አታደርጉበት አላቸው፡፡
|
|
\v 26 እነርሱም የመጣላቸውን ኮርማ ወስደው በመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ፡፡ ባዓል ሆይ እባክህ ስማን! እያሉ ጮኹ፡፡ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እየዘፈኑ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 እኩለ ቀን ሲሆን ኤልያስ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ! እርሱ አምላክ አይደለም እንዴ? እርሱ በአሳብ ተውጦ ይሆናል! ወይም ራሱን ያዝናና ይሆናል! ወይም ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ይሆናል! ወይም ተኝቶ ያንቀላፋ ይሆናልና እንዲነቃ ቀስቅሱት! እያለ ያፌዝባቸው ጀመር፡፡
|
|
\v 28 ስለዚህም ነቢያቱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየጸለዩ በሥርዓታቸው መሠረት ደማቸው እስኪፈስ ድረስ በቢላዋና በጩቤ ሰውነታቸውን ያቆስሉ ነበር፡፡
|
|
\v 29 እኩለ ቀን ካለፈም በኋላ የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ እየተራወጡ ይቀባጥሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ምንም መልስ አላገኙም፤ ድምፅም አልተሰማም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 30 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን ወደ እኔ ቅረቡ አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ በማደስ ሠራው፡፡
|
|
\v 31 እግዚአብሔር ከዚያ በፊት እስራኤል ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ ልጆች በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ፡፡
|
|
\v 32 እነዚህንም ድንጋዮች ረብርቦ በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ ሠራ፡፡ በዙሪያውም ዐሥራ አራት ሊትር ውሃ የሚይዝ ጉድጓድ ማሰ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 እንጨቱንም በመሠዊያው ላይ በመረብረብ ኮርማውን በብልት በብልቱ ቆራርጦ በእንጨቱ ላይ አኖረ፡፡
|
|
\v 34 በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት! አላቸው፡፡ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ አሁንም ጨምሩበት አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡፡
|
|
\v 35 ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጉድጓዱንም ሞላው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንህን፣ እኔም እግዚአብሔር ሆይ፣ የአንተ አገልጋይ መሆኔን፣ እኔም ይህንን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፡፡
|
|
\v 37 አምላኬ ሆይ፣ ይህ ሕዝብ አንተ እውነተኛ አምላክ መሆንህንና ወደ አንተም ያቀረብከው አንተ ራስህ መሆንህን እንዲያውቅ እባክህ መልስ ስጠኝ፤ አምላክ ሆይ ስማኝ!
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 38 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እሳትን ላከ፤ ያ እሳት መሥዋዕቱን፣ እንጨቱንና ድንጋዩን በላ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጉድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፡፡
|
|
\v 39 ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ እግዚአብሔር አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው! አሉ፡፡
|
|
\v 40 ኤልያስም የባዓል ነቢያትን ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ ሲል አዘዘ፡፡ ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጎድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው አለው፡፡
|
|
\v 42 አክዓብ እህልና ውሃ ለመቅመስ ሲሄድም ኤልያስ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ እዚያም በሁለቱ ጉልበቶቹ መካከል ራሱን ወደ መሬት ደፋ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 43 አገልጋዩን፣ ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት አለው፡፡ አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ ምንም ነገር አይታየኝም አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤
|
|
\v 44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ አለው፡፡ ኤልያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ዝናቡ ሳያቆምህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ ብለህ ንገረው ሲል አዘዘው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 45 ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ነፈሰ፤ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፡፡ ነጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤
|
|
\v 46 የእግዚአብሔርም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድረጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 19
|
|
\p
|
|
\v 1 ኤልያስ ያደረገውን ሁሉና የባዓልንም ነቢያት በሙሉ እንዴት እንደ ገደላቸው ንጉሥ አክዓብ ለሚስቱ ለኤልዛቤል ነገራት፡፡
|
|
\v 2 ስለዚህ እርስዋ በእነዚያ ነቢያት ላይ ያደረግኸውን እኔም ነገ ልክ በአሁኑ ሰዓት በአንተ ላይ ሳላደርግብህ ብቀር አማልክት በሞት ይቀሥፉኝ ስትል ወደ ኤልያስ የዛቻ መልእክት ላከች፡፡
|
|
\v 3 ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምተገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ፡፡ አገልጋዩንም በዚያ ተወው፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 ኤልያስ ራሱ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፡፡ ከዚህ በኋላ፣ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፣ ሞቱንም በመመኘት እግዚአብሔር ሆይ፣ አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ! ሲል ጸለየ፡፡
|
|
\v 5 ከዚህ በኋላ በዛፉ ሥር ጋደም እንዳለ እንቅልፍ ወሰደው፤ በድንገትም አንድ መልአክ መጥቶ በመዳሰሰ ቀሰቀሰውና ተነሥተህ ብላ! አለው፡፡
|
|
\v 6 ኤልያስ ተነሥቶ ዞሮ በተመለከተ ጊዜ በድንጋይ ሙቀት የበሰለ የዳቦ ሙልሙልና አንድ ገንቦ ውሃ በራስጌው ተቀምጦ አየ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ እንደገና ተኛ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 የእግዚአብሔርም መልአክ ተመልሶ መጥቶ የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ስለ ሆነ ተነሥተህ ብላ! ሲል ዳግመኛ ኤልያስን ቀሰቀሰው፡፡
|
|
\v 8 ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፤ ውሃውንም ጠጣ፡፡ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 እዚያም እንደ ደረሰ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ እዚያ ዐደረ፡፡ በድንገትም እግዚአብሔር፣ ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው፡፡
|
|
\v 10 ኤልያስም ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ! ሲል መለሰ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 እግዚአብሔርም ኤልያስን ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኮረብቶችን ሰነጣጠቀ፤ ዐለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፡፡ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም፡፡
|
|
\v 12 ከምድሪቱም ነውጥ በኋላ እሳት መጣ፤ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም በኋላ የሹክሹክታ ድምፅ ተሰማ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ኤልያስ የሹክሹክታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጎናጸፊያ ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው መግቢያ በር አጠገብ ቆመ፤ አንድ ድምፅም ኤልያስ ሆይ፣ እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው፡፡
|
|
\v 14 ኤልያስም ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ፣ እኔ ለአምላኬ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ ሲል መለሰ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ በደማስቆ ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓ ተመልሰህ ሂድ፤ እዚያም በደረስህ ጊዜ አዛሄልን ቀብተህ በሶርያ ላይ አንግሠው፤
|
|
\v 16 የናሜሲን ልጅ ኢዩንም ቀብተህ በእስራኤል ላይ አንግሠው፤ የአቤል ምሖላ ተወላጅ የሆነውን የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕንም ቀብተህ በአንተ ፈንታ ነቢይ እንዲሆን አድርገው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ከአዛሄል እጅ ከመገደል ተርፎ የሚያመልጠውን ማንኛውንም ሰው ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ እጅ የሚያመልጠውንም ኤልሳዕ ይገድለዋል፡፡
|
|
\v 18 ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ ለባዓል ያልሰገዱና ለምስሉም ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 ኤልያስም ከዚያ ከሄደ በኋላ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ሁለት በሬዎች ጠምዶ ሲያርስ አገኘው፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ በአሥራ አንድ ጥማድ በሬዎች የሚያርሱ ደቦኞች ነበሩ፤ ኤልሳዕም በመጨረሻ አሥራ ሁለተኛውን ጥማድ ያርስ ነበር፤ ኤልያስም መጎናጸፊያውን አውልቆ በኤልሳዕ ላይ ደረበለት፡፡
|
|
\v 20 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ተቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ አባቴና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ አለው፡፡ ኤልያስም፣ እሺ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም! ሲል መለሰለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ አረዳቸው፡፡ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 20
|
|
\p
|
|
\v 1 የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፡፡ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ያሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያ ጦርነት ገጠመ፡፡
|
|
\v 2 እርሱም ሀዳድ በከተማይቱ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ነጉሥ ወደ አክዓብ፣ ቤን ሀዳድ እንዲህ ይላል ብሎ መልእክተኞችን ላከ፡-
|
|
\v 3 ብርህና ወርቅህ ውብ የሆኑት ሚስቶችህና ልጆችህ ምርጥ የሆኑ ሁሉ የእኔ ናቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 የእስራል ንጉሥም ጌታዬ ንጉሥ አንተ እንዳልከው ይሁን ብሎ መለሰ፡፡ እኔ የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ናቸው አለ፡፡
|
|
\v 5 ከጥቂት ጊዜም በኋላ እነዚያው መልእክተኞች ከንጉሥ ቤን ሀዳድ ሌላ ትእዘዝ ይዘው እንደገና ወደ አክዓብ መጡ፤ ትዕዛዙ እንዲህ የሚል ነበር፤ ብርህን፣ ሚስቶችህንና ልጆችህን ማስረክብ እንዳለብህ መልእክት ልኬብህ ነበር፡፡
|
|
\v 6 አሁን ደግሞ ቤትህንና የአገልጋዮችህን ቤት ሁሉ ይበረብራሉ፡፡ በርብረውም በዓይናቸው ደስ ያላቸውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኮንኖቼን ነገ በዚህ ጊዜ እልካለሁ፡፡ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ የአገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ ይህ ሰው ምን ዓይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ አለ፡፡ ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፣ ብሬንና ወረቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር አላቸው፡፡
|
|
\v 8 ሽማግሌዎቹና ሕዝቡም ሁሉ እርሱ ለሚልህ ነገር ሁሉ ግምት አትስጠው፤ ከፍላጎቱ ጋር አትስማማው አሉት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ስለዚህም አክዓብ ለቤን ሀዳድ መልእክተኞች ለጌታዬ ለንጉሡ ከዚህ በፊት ባቀረብክልኝ ጥያቄ ተስማምቼ ነበር፤ አሁን ባቀረብክልኝ በሁለተኛው ጥያቄ ግን ልስማማበት አልችልም ብሎአል ብላችሁ ንገሩት አላቸው፡፡ መልእክተኞቹም ተመልሰው በመሄድ መልሱን ነገሩት፤
|
|
\v 10 ቤን ሀዳድም በሰማርያ ለእያንዳንዱ ወታደር አንዳንድ ጭብጥ ዐፈር ሊዳረስ እስከማይችል ድረስ ብዙ ወታደሮችን ባላሰልፍ አማልክት ይቅሠፉኝ ብሎ የዛቻ መልእክቱን መልሶ ላከበት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 የእስራኤል ንጉሥ መልእክተኞቹን፣ በወታደር መኩራራት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም፣ ብላችሁ ለንጉሥ ቤን ሀዳድ ንገሩት ሲል መለሰላቸው፡፡
|
|
\v 12 ቤን ሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓበ መልእክት ደረሳቸው፤ በዚህን ጊዜ ቤን ሀዳድ ለጦርነት እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ስለዚህም ፈጥነው በመንቀሳቀስ ከተማውን ለማጥቃት ቦታ ቦታቸውን ያዙ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 በዚያን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ይህንን ታላቅ ጦር አየህን? እነሆ እግዚአብሔር ዛሬ የቤን ሀዳድን ሠራዊት በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፡፡ አንተም ደግሞ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃለህ ይልሃል አለው፡፡
|
|
\v 14 አክዓብም ግንባር ቀደም ሆኖ የሚዘምተው ማን ይሁን? ሲል ጠየቀ፡፡ ነቢዩም እግዚአብሔር በአውራጃ አስተዳዳሪዎች የሚታዘዙ ወጣት ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ይዝመቱ ይላል አለው፡፡ ንጉሡም ጦርነቱን ማን ይጀምር? ሲል ጠየቀ፡፡ ነቢዩም አንተ ራስህ ጀምር አለው፡፡
|
|
\v 15 ስለዚህ ንጉሡ ብዛታቸው ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ብቻ የሆነ በአውራጃ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ሥር የሆኑትን ወጣት ወታደሮችን ጠራ፡፡ ቀጥሎም ጠቅላላ ብዛቱ ሰባት ሺህ የሆነ የእስራኤልን ሠራዊት ጠራ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 እነርሱም እኩለ ቀን ላይ ሄዱ፡፡ ቤን ሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች የሆኑ ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ በመጠጥ ሰክረው ነበሩ፡፡
|
|
\v 17 ወጣቶቹም ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ወደ ፊት አመሩ፡፡ ቤን ሀዳድ ልኮአቸው የነበሩትም ቃፊሮች አንድ የወታደር ቡድን ከሰማርያ ወጥቶ ወደዚህ እየመጣ መሆኑን ነገሩት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ቤን ሀዳድም ቃፊሮቹን፣ አመጣጣቸው ለጦርነትም ይሁን ለሰላም ይዛቸሁ አምጡልኝ ሲል አዘዘ፡፡
|
|
\v 19 ስለዚህ በእስራኤል ሠራዊት ደጀንነት በአውራጃ አስተዳደሪዎች የሚታዘዙ ወጣቶቹ ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ወጡ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፡፡ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፡፡ ቤን ሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ፡፡
|
|
\v 21 ንጉሥ አክዓብም ወደ ጦሩ ሜዳ ገብቶ የጠላትን ፈረሶችና ሠረገሎችን ማረከ፡፡ በሶርያውያን ላይ ታላቅ ጥፋት በማድረስ ድል አደረጋቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 22 ስለዚህ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ፡- የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ አለው፡፡
|
|
\v 23 አገልጋዮቹም ንጉሥ ቤን ሀዳድን እንዲህ አሉት፡- የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፡፡ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፡፡ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ስለዚህ አሁን ሠላሳ ሁለቱን ነገሥታት ከጦር አዛዥነታቸው ሽረህ በእነርሱ ቦታ ሌሎችን የጦር አዛዦች ሹም፡፡
|
|
\v 25 ከዚህ በፊት የተደመሰሰውን የሚያህል ብዙ ሠራዊትና በቀድሞዎቹ ልክ ፈረሶችንና ሠረገሎችን አደራጅ፤ ከዚያ በኋላ እስራኤላውያንን በሜዳ ተዋግተን ድል እንነሣቸዋለን፡፡ ስለዚህ ቤን ሀዳድም በእነርሱ ምክር ተስማምቶ ለመፈጸም ወሰነ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ከዚያም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ እስራኤልን ለመዋጋት ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ፡፡
|
|
\v 27 እስራኤላውያን ተጠርተው ከሚያስፈልጋቸው ስንቅና ትጥቅ ጋር ለጦርነት ተዘጋጁ፤ እነርሱም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በሁለት ቡድን ተከፍለው ከሶርያውያን ፊት ለፊት ባለው ቦታ ሰፈሩ፡፡ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር አገሩን ካጥለቀለቀው ከሶርያውያን ሠራዊት ብዛት ጋር ሲነጻጻር ከሁለት የተከፈለሉ የጥቂት ፍየሎች መንጋዎች ይመስሉ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ሶርያውያን፡- እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ የሆነውን ሠaርዊታቸውን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ስለዚህ ሶርያውያንና እስራኤላውያን ፊት ለፊት ተፋጠው በየጦር ሰፈራቸው እስከ ሰባት ቀን ቆዩ፤ በሰባተኛውም ቀን ጦርነት ጀምረው በዚያኑ ቀን እስራኤላውያን አንድ መቶ ሺህ የሶርያውያንን እግረኛ ጦር ወታደሮችን ገደሉ፡፡
|
|
\v 30 ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ሃያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጥር ተንዶባቸው አለቁ፡፡ ቤን ሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ ገብቶ ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 የቤን ሀዳድ አገልጋዮች ወደ እርሱ ቀርበው፣ የእስራኤል ነገሥታት ምሕረት አድራጊዎች መሆናቸውን ሰምተናል፤ ስለዚህ በወገባችን ማቅ ታጥቀን፣ በራሳችንም ገመድ ጠምጥመን ወደ እስራኤል ንጉሥ ሄደን ምሕረት እንድንጠይቀው ፍቀድልን፤ ምናልባትም ሕይወትህን ያተርፍ ይሆናል አሉት፡፡
|
|
\v 32 ከዚህም በኋላ እነርሱ በወገባቸው ማቅ ታጥቀው በራሳቸውም ገመድ ጠምጥመው ወደ ንጉሥ አክዓብ በመሄድ አገልጋይህ ቤን ሀዳድ ምሕረት አድርገህ ሕይወቱን እንድታተርፍለት ይማጠንሃል አሉት፡፡ አክዓብም እርሱ እስከ አሁን በሕይወት አለ ማለት ነውን? ከሆነስ መልካም ነው፤ እንግዲህ እርሱ ለእኔ እንደ ወንድም ነው ሲል መለሰላቸው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 የቤን ሀዳድ አገልጋዮችም የምሕረት መልእክት ይጠባበቄ ስለ ነበር አክዓብ ወንድሜ ሲል በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ቀበል አድገርው አንተ እንዳልከው ቤን ሀዳድ በእርግጥ ወንድምህ ነው አሉት፡፡ አክዓብም ወደ እኔ አምጡት! አላቸው፡፡ ቤን ሀዳድም በመጣ ጊዜ አክዓብ ወደ ሠረገላው ገብቶ እንዲቀመጥ ቤን ሀዳድን ጋበዘው፡፡
|
|
\v 34 ቤን ሀዳድም አክዓብን አባቴ ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልስልሃለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ የንግድ ማእከል ልታቋቁም ትችላለህ አለው፡፡ አክዓብም እንግዲያውስ በዚህ ስምምነት መሠረት እኔም በነጻ እለቅሃለሁ ሲል መለሰለት፡፡ አክዓብም በዚህ ዓይነት ከእርሱ ጋር የውል ስምምነት አድርጎ በነጻ እንዲሄድ ፈቀደለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 35 የነቢያት ወገን የሆነ አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ታዞ የእርሱ ጓደኛ የሆነውን ሌላ ነቢይ ምታኝ አለው፡፡ ነቢዩ ግን እርሱን ለመምታት እምቢ አለ፡፡
|
|
\v 36 ስለዚህም ያ ነቢይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንበሳ ይገድልሃል አለው፤ ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 37 ከዚህም በኋላ ነቢዩ ወደ ሌላ ሰው ሄዶ ምታኝ አለው፣ ያም ሰው መትቶ አቆሰለው፤
|
|
\v 38 ነቢዩ ማንነቱ እንዳይታወቅ ፊቱን በጨርቅ ሸፈነ፤ ሄዶም በዚያ በኩል የሚያልፈውን የእስራኤል ንጉሥ ለመጠበቅ በመንገድ ዳር ቆመ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 39 ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ ነቢዩ ተጣርቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፡- ንጉሥ ሆይ እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ይህን ሰው ጠብቅ፣ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አንድ መክሊት የሚመዝን ብር መቀጫ ትከፍላለህ አለኝ፡፡
|
|
\v 40 ነገር ግን እኔ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያ ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ፡፡ ንጉሡም በራስህ ላይ ስለ ፈረድህ መቀጣት ይገባሃል አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 ነቢዩ ፊቱ የተሸፈነበትን ጨርቅ ፈጥኖ አወለቀ፤ ንጉሡም ይህ ሰው ከነቢያት ወገን አንዱ መሆኑን ወዲያውኑ አወቀ፡፡
|
|
\v 42 ነቢዩም ንጉሡን እንዲህ አለው፡- እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ እኔ ይገደል ብዬ የፈረድኩበት ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፡፡
|
|
\v 43 ስለዚህ ንጉሡ እያዘነና እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ወደ ሰማርያ ተመልሶ ሄደ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 21
|
|
\p
|
|
\v 1 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ናቡቴ ተብሎ የሚጠራ ሰው በኢይዝራኤል በሚገኘው በንጉሥ አክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ የራሱ ርስት የሆነ አንድ የወይን ተክል ቦታ ነበረው፡፡
|
|
\v 2 አንድ ቀን አክዓብ ናቡቴን የወይን ተክል ቦታህን ስጠኝ፤ በቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ የአትክልት ቦታ ላደርገው እፈልጋለሁ፤ በምትኩ ከእርሱ የተሻለ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ልትሸጠው ብትፈልግም የተሻለ ዋጋ እከፍልሃለሁ አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ናቡቴም ይህንን የወይን ተክል ቦታ የወረስኩት ከቅድም አያቶቼ ነው፤ ለአንተ ከመስጠትስ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! ሲል መለሰለት፡፡
|
|
\v 4 አክዓብ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ ቀርባ እንደዚህ ያበሳጨህ ነገር ምንድን ነው? ስለምንስ ምግብ አትበላም? ስትል ጠየቀችው፡፡
|
|
\v 6 እርሱም እኔን ያበሳጨኝ ከናቡቴ ያገኘሁት መልስ ነው፤ ይኸውም የእርሱን የወይን ተክል ቦታ እንድገዛ ወይም ከፈለገ ልዋጩን እንድሰጠው ብጠይቀው የወይን ተክል ቦታውን አልሰጥህ ብሎ አናደደኝ ሲል መለሰላት፡፡
|
|
\v 7 ኤልዛቤልም እንግዲህ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ሆነህ ሳለህ እንደዚህ መሆን ይገባሃልን? ይልቅስ ተነሥ ተደሰት፤ እህል ውሃም ቅመስ፡፡ እኔ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ እንድታገኝ አደርጋለሁ አለችው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ስለዚህ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋና በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱን ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች፡፡
|
|
\v 9 ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፡- የአንድ ቀን ጾም አውጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰብስቡ፤ ለናቡቴም የክብር ቦታ ስጡት፤
|
|
\v 10 እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያ በኋለ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አወጥታችሁ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ስለዚህ የኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎችም በደብዳቤው እንደተገለጸው ኤልዛቤል ያዘዘቻቸውን አደረጉ፡፡
|
|
\v 12 የአንድ ቀን ጾም አወጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰበሰቡ፤ ለናቡቴም የክብር ቦታ ሰጡት፡፡
|
|
\v 13 ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡
|
|
\v 14 ናቡቴ ተወግሮ ተገድሎአል የሚል መልእክትም ወደ ኤልዛቤል ላኩ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ኤልዛቤልም መልእክቱን እንደ ተቀበለች ወዲያውኑ አክዓብን ናቡቴ ሞቶአል፤ አሁን ተነሥተህ ሂድና ለአንተ ለመሸጥ እምቢ ያለውን የወይን ቦታ ርስት አድርገህ ውሰድ አለችው፡፡
|
|
\v 16 አክዓብም የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውረስ ወዲያውኑ ተነሥቶ ሄደ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡፡
|
|
\v 18 ተነሥተህ ሂድና የእስራኤልን ንጉሥ አከዓብን በሰማርያ አግኘው፤ እርሱ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውረስ ሄዶአል፣ በዚያው ታገኘዋለህ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ መናገር አለብህ፣ ናቡቴን ገድለህ ሀብቱንም ወሰድክበትን? ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የናቡቴን ደም ውሾች በላሱበት ስፍራ የአንተንም ደም እንደዚሁ ይልሱታል።
|
|
\v 20 አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ ጠላቴ ሆይ አገኘኸኝን? አለው፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፣ አዎን አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ለማድረግ ራስህን ሸጠከውን? አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፣ እነሆ በአንተ ላይ መቅሠፍትን አመጣብሃለሁ፤ አንተን ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ ከቤተ ሰብህም ውስጥ ወንድ የሆነውን ሁሉ ባሪያ ሆነ ነጻ ሰው አጠፋለሁ፡፡
|
|
\v 22 እስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራታችሁ ቁጣዬን ስለ አነሣሣህ ቤተ ሰብህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ቤተ ሰብና እንደ አኪያ ልጅ እንደ ንጉሥ ባኦስ ቤተ ሰብ ለጥፋት የተጋለጠ ይሆናል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- በኢይዝራኤል ከተማ ውስጥ ሬሳዋን ውሾች ይበሉታል፡፡
|
|
\v 24 ከአክዓብም የሆነውን ሁሉ በከተማው ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም ሰው ውሾች ይበሉታል፤ በገጠርም በየሜዳው የሚሞተውን ሁሉ የሰማይ አሞራዎች ይበሉታል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ለኤልዛቤል ኃጢአት ራሱን አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚመሰል ማንም አልነበረም፡፡ ይህን ሁሉ ያደረገው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፡፡
|
|
\v 26 አክዓብ ከፈጸመው አሳፋሪ በደል ሁሉ ዋናው እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሞራውያንን ጣዖት ማምለኩ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 አከዓብም ይህንን በሰማ ጊዜ፡- ልብሱን ቀዶ ማቅ ለበሰ፤ ማቁን እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ አዝኖ ነበር፡፡
|
|
\v 28 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ቴስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡-
|
|
\v 29 አክዓብ በእኔ ፊት ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመልክተሃልን? እግዚአብሔርም በፊቴ ራሱን ስላዋረደ በሕይወቱ ዘመን መቅሠፍትን በአክዓብ ቤተ ሰብ ላይ አላመጣበትም፤ የማመጣውም በልጁ ዘመን ይሆናል፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 22
|
|
\p
|
|
\v 1 በእስራኤልና በሶሪያ መካከል ያለ ጦርነት ሦስት ዓመት አለፈ፡፡
|
|
\v 2 ይሁን እንጂ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ለመጎብኘት ሄደ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 የእስራኤል ንጉሥ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፡- በገለዓድ የምትገኘውን ራሞት ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት አላቸው፡፡
|
|
\v 4 ስለዚህ እርሱም ኢዮሣፍጥን ለጦርነት ወደ ራሞት ከእኔ ጋር ትሄዳለህን? ሲል ጠየቀው፡፡ ኢዮሣፍጥም እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ አንተ ሕዝብ ነው፤ ፈረሶቼም እንደ አንተ ፈረሶች ናቸው አለው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ኢዮሳፍጥም፣ ነገር ግን መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቅ ሲል መለሰለት፡፡
|
|
\v 6 ከዚያም አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ ወደ ራሞት ለጦርነት ልውጣ ወይስ ልቅር? ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ሄደህ ተዋጋ፤ እግዚአብሔርም በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣል ሲሉ መለሱለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ኢዮሣፍጥ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቅበት ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ የለምን? ሲል ጠየቀ፡፡
|
|
\v 8 አክዓብም የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይ አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም ሲል መለሰለት፡፡ ኢዮሣፍጥም ይህን ማለት አይገባህም፤ አለው፡፡
|
|
\v 9 ከዚያም አክዓብ ከቤተ መንግሥቱ አገልጋዮች አንዱን ጠርቶ የይምላ ልጅ ሚክያስን ፈልገህ በማግኘት በፍጥነት እንዲመጣ አድርግ ሲል አዘዘው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሁለቱ ነገሥታት ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰው በሰማርያ የቅጥር በር አጠገብ በሚገኘው ሜዳ በየዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፡፡ ነቢያቱም ሁሉ በነገሥታቱ ፊት ቀርበው ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡
|
|
\v 11 ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚ. ጠራው የክንዓና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶች ይዞ አክዓብን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ አለው፡፡
|
|
\v 12 ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ በራሞት ላይ ዝመት፣ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ይሰጥሃል አሉት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህ አንተም እንደእነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል አለው፡፡
|
|
\v 14 ሚክያስ ግን እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! ሲል መለሰለት፡፡
|
|
\v 15 ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ፣ ሚክያስ ሆይ፣ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት ወይስ እንተው? ሲል ጠየቀው፡፡ ሚክያስም ዘምተህ አደጋ ጣልባት ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ ሲል መለሰለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ከዚያም አክዓብ፣ አንተ ግን በእግዚአብሔር ስም የትንቢትን ቃል ስትነግረኝ እውነቱን መግለጥ እንደሚገባህ ስንት ጊዜ እነግርሃለሁ አለው፡፡
|
|
\v 17 ሚክያስም መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ እግዚአብሔርም፣ እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሎአል ሲል መለሰለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 አክዓብም ኢዮሣፍጥን እርሱ ሁልጊዜ ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም ብዬህ አልነበረምን? አለው፡፡
|
|
\v 19 ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለውን ስማ፤ እግዚአብሔር በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፡፡
|
|
\v 20 እግዚአብሔርም አክዓብን ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማን ነው? አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ ሌላ ነገር ሌላውም ሌላ ነገር አለ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 በመጨረሻ ግን አንድ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ እኔ ላሳስተው እችላለሁ አለ፡፡
|
|
\v 22 እግዚአብሔርም እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ? አለው፡፡ መንፈሱም፣ ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው፡፡
|
|
\v 23 ሚክያስም እነሆ እግዚአብሔር እነዚህን የአንተን ነቢያት የሐሰት ቃለ እንዲነግሩህ ያደረገው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ በአንተ ላይ ጥፋት ሊያመጣብህ እግዚአብሔር ራሱ ወስኖአል! ሲል ንግግሩን ደመደመ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀርቦ በጥፊ መታውና ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ? አለው፡፡
|
|
\v 25 ሚክያስም በውስጥ ወዳለው ክፍል ሄደህ በምትሸሽግበት ጊዜ ታውቀዋለህ ሲል መለሰለት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 በዚህን ጊዜ ንጉሥ አክዓብ ከጦር መኮንኖቹ አንዱን ሚክያስን ያዘው፤ ወደ ከተማይቱ ገዢ ወደ አሞንና ወደ ልዑል ኢዮአስ ውሰደው፤
|
|
\v 27 እኔም በደህና እስክመለስ ድረስ እስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቆይ ያድርጉ ሲል አዘዘው፡፡
|
|
\v 28 ሚክያስም አንተ በደህና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነው! አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ አለ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 29 ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ራሞት ከተማ ለመዋጋት ሄዱ፡፡
|
|
\v 30 አክዓብም ኢዮሣፍጥን ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ተራ ልብስ እለብሳለሁ፣ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ አለው፡፡ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 የሶርያ ንጉሥም በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ ብሎ ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትአዛዝ አስተላለፈ፡፡
|
|
\v 32 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ በርግጥ እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው ብለው በእርሱ ላይ አደጋ ሊጥሉበት ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም በጮኸ ጊዜ፣
|
|
\v 33 እርሱ የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በማረጋገጥ በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተመለሱ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 ነገር ግን በአጋጣሚ አንድ የሶርያ ወታደር ፍላጻ በማስፈንጠር ንጉሥ አክዓብን በጦር ልብሱ መገናኛ ላይ ወጋው፤ ንጉሥ አክዓብም የሠረገላ ነጂውን ክፉኛ ቆስያለሁ፤ ስለዚህ ሠረገላውን መልሰህ ከጦር ሜዳው ውጣ! ሲል አዘዘው፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 35 ጦርነቱም በተፋፋመ ጊዜ ንጉሥ አክዓብ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ነበር፤ በዚያውም ቀን ምሽት ሞተ፡፡
|
|
\v 36 ፀሐይ በመጥለቅ ላይ እያለች፣ እያንዳንዱ ሰው ወደየአገሩና ወደየከተማው ይመለስ የሚል ትእዛዝ ከእስራኤል ጦር አዛዦች ተነገረ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 37 ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ ሞተ፤ ሬሳውም ወደ ሰማርያ ተወስዶ ተቀበረ፡፡
|
|
\v 38 ሠረገላውም በሰማርያ ኩሬ ታጠበ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ደሙን ውሾች ላሱት፤ በዚያም ኩሬ ሴተኛ አዳሪዎች ታጠቡበት፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 39 ንጉሥ አክዓብ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ ምን እንደ ሠራና የሠራቸውም ከተሞች ሁኔታ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
\v 40 ንጉሥ አክዓብም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ልጁ አካዝያስ ተተክቶ ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
|
|
\v 42 ኢዮሣፍጥም በሠላሳ አምስት ዓመት ዕድሜው ነግሦ ሃያ አምስት ዓመት በኢየሩሳሌም ገዛ፡፡ እናቱም ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 43 ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አደረገ፡፡ ሆኖም ግን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፡፡
|
|
\v 44 ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላም መሠረተ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 45 ኢዮሣፍጥ ያደረጋቸው ነገሮች፣ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነትም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
|
|
\v 46 ከአባቱ ከአሳ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የተረፉትንና በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የጣዖት አመንዝራዎችን ሁሉ አስወገደ፡፡
|
|
\v 47 በዚያን ዘመን የኤዶም ምድር የራስዋ ንጉሥ አልነበራትም፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ንጉሥ በሚሾመው እንደራሴ ትገዛ ነበር፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 48 ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዓይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም፡፡
|
|
\v 49 ከዚያ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኛች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን አሳቡን አልተቀበለም፡፡
|
|
\v 50 ንጉሥ ኡዮሣፍጥ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አዮራም ነገሠ፡፡
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 51 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ በሰማርያ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡
|
|
\v 52 እርሱም የአባቱን የአክዓብን፣ የእናቱን የኤልዛቤልንና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት በደል ሠራ፡፡
|
|
\v 53 ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ በመስገድና በማገልገል የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡
|